Friday, July 22, 2016

ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሄሊኮፕተሮች ተጭነው ወደ ደብረዘይት እየተወሰዱ ነው

ሐምሌ  ፲፭ ( አሥራ አምስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰኔ 7 ቀን 2008 ዓም በኢትዮጵያ አየር ሃይል የድሬዳዋ ምድብ ውስጥ ሄሊኮፕተርን በመሬት ላይ የማሮጥ ስራ ወይንም ኢንጅን ቴስት ረንአፕ (Engine Test Runup) ሲያደርጉ የነበሩት ሌ/ኮሎኔል ፀጋዘዓብ ካሳ ሌሎች ሁለት የቆሙ ሄሊኮፕተሮችን በመግጨታቸው ሶስቱም ሄሊኮፕተሮች ከጥቅም ውጭ ሆነው የቆዩ ሲሆን፣  ሄሊኮፕተሮቹ በከባድ መኪና ተጭነው  ወደ ደብረዘይት አየር ሃይል ምድብ በመጓጓዝ ላይ ናቸው።

በሄሊኮፕተሮቹ ላይ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ሲሆን፣ አየር ሃይሉ አሉኝ ከሚላቸው ውስን ሄሊኮፕተሮች ውስጥ ይመደባሉ። ነባር የህወሃት ታጋይ የሆኑት ባደረሱት ጥፋት የተወሰደባቸው የዲስፒሊን እርምጃ የለም። ከህወሃት ውጭ ያሉ የሰራዊቱ አባላት ጉዳት አድርሰው ቢሆን ኖሮ “ሆን ብለው ያደረጉት ነው” በሚል ከፍተኛ ምርመራ ይደርስባቸው እንደነበር አብራሪዎች አስተያየታቸውን ሰጥዋል።
በሌላ በኩል በአነስተኛ እና ጥቃቅን ስራ እድል ስም የሰራዊት ምዝገባ እየተካሄደ ነው ።  በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ወጣቶች ለአነስተኛ እና ጥቃቅን የስራ እድል እንዲመዘገቡ በማስታወቂያ ተጠርተው ከሄዱ በሁዋላ፣ ስለመከላከያ ሰራዊት ገለጻ ተደርጎላቸው እንዲመዘገቡ ለማድርግ እየሞከሩ መሆኑን ለስራ ምዝገባ የሄዱ ወጣቶች ገጠመኛቸውን ለኢሳት ተናግረዋል።
በአንድ ወረዳ ውስጥ ለስራ ምዝገባ በቡድን የሄዱ ወጣቶች ሁሉም የትምህርት ማስረጃቸውን እንዲያስገቡ ከተነገራቸው በሁዋላ፣ በቀጥታ ስለመከላከያ ሰራዊት ጥንካሬ ገለጻ የተሰጣቸው ሲሆን፣ ወጣቶቹ የትምህርት ማስረጃ ሰነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒ አድርገው እንዲመጡ በነፍስ ወከፍ 50 ብር ተሰጥቷቸዋል።
ያልጠበቁት ነገር ያጋጠማቸው ወጣቶች በማግስቱ እንዲቀርቡ ተነግሮአቸው የነበረ ቢሆንም፣ ሁሉም ወጣቶች ተመልሰው ሳይሄዱ ቀርተዋል። የወጣቶች ድርጊት ያበሳጫቸው ካድሬዎች፣ ልጆቹ እንዳይመጡ ያደረከው አንተነህ በሚል አንደኛውን ወጣት በምሽት አፍነው በመውሰድ ክፉኛ ደብድበው የፊት ጥርሱን አውልቀው ለቀውታል። ያስገቡት የትምህርት ማስረጃም እንደማይሰጣቸው ተነግሯቸዋል ።
በተለያዩ አካባቢዎች የመከላከያ ሰራዊት ለመመልመል የተደረገው ሙከራ አለመሳካቱን

No comments:

Post a Comment