Monday, July 4, 2016

በገላና ወረዳ አንድ የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪ ተደበደበ

በሁሌ ቦራ ዞን በገላና ወረዳ ሜጄ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑትና ሰማያዊ ፓርቲን በመወከል ባለፈው ግንቦት ወር ምርጫ እጩ ተወዳዳሪ የነበሩት  አቶ ደስታ ቁጤ ከምሽቱ አንድ ሰአት ላይ በተፈጸመባቸው ድብደባ በእግሮቻቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶአቸው በህክምና እየተረዱ ነው።

ማንነታቸው ያልታወቁት ግለሰቦች ጨለማን ተገን አድርገው ግለሰቡን መደብዳበቸውንና ከዚህ ቀደም ከደህንነቶች ማስፈራሪያ ሲደርሰው እንደነበር እንደነገሯቸው የዞኑ የሰማያዊ ፓርቲ ተወካይ አቶ ጌታቸው በቀለ ለኢሳት ተናግረዋል

No comments:

Post a Comment