Monday, July 4, 2016

የኮንሶ ህዝብ ጥያቄ ውድቅ መደረጉን ተከትሎ በአካባቢው ውጥረት ሰፍኗል

የደቡብ ክልል የብሄረሰቦች ምክር ቤት ሰኔ 23 ቀን 2008 ዓም የኮንሶ ህዝብ የራስ አስተዳደር ጥያቄ ውድቅ መደረጉን የሚግልጽ ደብዳቤ መጻፉን ተከትሎ በአካባቢው ውጥረት መንገሱን ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።

ምክር ቤቱ በደብዳቤው “ የክልሉ ህገመንግስት አንቀጽ 59 ንኡስ አንቀጽ 3 እና የብሄረሰቦች ምክር ቤትን ለማጠናከር ስልጣንና ተግባሩን ለመዘርዘር የወጣው አዋጅ ቁጥር 60/95 መሰረት አጠቃላይ የጥያቄው ይዘትና ምክንያቶችን መርምሮ በማየት የኮንሶ ህዝብ መሰረታዊና ቀጥተኛ ጥቅሞችንና ሌሎች ህገመንግስታዊ አላማዎችን ለማሳካት እንዲቻል ህዝቡ አሁን ባለበት በሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን እንዲቀጥልና  ለብቻው ለብቻው በዞን ለመደራጀት ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት እንደሌለው በሰኔ 20/2008 ዓም በሃዋሳ የተካሄደው 3ኛው ዙር 3ኛ የስራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔውን አሳልፏል፡” ሲል ጥያቄውን ላቀረቡት የኮንሶ ተወላጆች ገልጿል።

የጥያቄው አቅራቢዎች ውሳኔው ከህገመንግስቱ ጋር የሚላተም በመሆኑ እንደማይቀበሉት ይገልጻሉ። ምክር ቤቱ የኮንሶ ጥያቄ መልስ ካገኘ እስካሁን ድረስ መልስ ያላገኙ ሌሎችም የአስተዳደርና የማንነት ጥያቄ አቅራቢዎችም በተመሳሳይ መንገድ “ የእኛስ ጥያቄ ምን ደረሰ?” የሚል ጥያቄ ሊያነሱ ይችላሉ በሚል ፍራቻ መወሰናቸውን ተናግረዋል
ውሳኔውን ተከትሎ ፌደራል ፖሊስ ከተማውን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠረ ሲሆን፣ በርካታ ወጣቶችም ተይዘው ታስረዋል።
ለወራት የመንግስት ሰራተኞች ስራ አቁመው ደሞዝ ሲከፈላቸው ቢቆይም ፣ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ክፍያ የተቋረጠ በመሆኑ ለችግር ሰራተኞች ለችግር መዳረጋቸውንም ተናግረዋል። ከወራት በፊት የተዘጉት ትምህርት ቤቶች አሁንም አልተከፈቱም።

No comments:

Post a Comment