Friday, July 8, 2016

መምህር አብረሃ ደስታ ከእስር ተፈታ

ሐም ( አንድ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሃምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ  በሽብር ወንጀል ክስ ተመስርቶበት ላለፉት ሁለት ዓመታት በእስር ሲንገላታ የነበረው የአረና ትግራይ ፓርቲ አባል መምህር አብረሃ ደስታ ከእስር ተፈቷል።

አቶ አብርሃ ደስታ ነሀሴ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. በከፍተኛው ፍርድ ቤት ከተከሰሰበት የሽብር ወንጀል ነጻ የተባለ ቢሆንም፣  ችሎት ተዳፍረሃል ተብሎ ለተጨማሪ ጊዜያት በእስር እንዲቆይ ተደርጓል። አብርሃ ደስታ የህወሃት ኢህአዴግ መንግስት በተለይ በትግራይ ክልል ውስጥ የሚፈጽማቸውን ኢሰብዓዊ ድርጊቶች ሲያጋልጥ ቆይቷል።

No comments:

Post a Comment