Thursday, July 14, 2016

በርካታ ቁጥር ያላቸው የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ ጎንደር እያመሩ ነው

ሐምሌ ፯ ( ሰባት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ከወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ህዝባዊ አመጽ ለመቆጣጠር በኦሮምያ፣ በደቡብና መሃል አዲስ አበባ ያሰፈራቸውን የአጋዚ ጦር አባላትንና ወታደሮችን ወደ ሰሜን በማጓጓዝ ላይ ይገኛል።

ሰላማዊ ትግሉን በሃይል ለመጨፍለቅ የወሰነ የሚመስለው ስርዓቱ፣ በተመሳሳይ መልኩ ከታጠቁት የክልሉ ታጣቂዎች ተቃውሞ ይገጥመዋል ተብሎ ይጠበቃል። የክልሉ ነዋሪዎች በጎንደር የተወሰደውን እርምጃ እያወገዙ ሲሆን፣ በአንዳንድ ከተሞች ተቃውሞ ይነሳል በሚል ጥበቃው ተጠናክሯል።

No comments:

Post a Comment