Thursday, September 20, 2018

ከቡራዩና አካባቢው ለተፈናቀሉ ዜጎች እርዳታ የማሰባሰብ ዘመቻ ተጀመረ

( ኢሳት ዜና መስከረም 10 ቀን 2011 ዓ/ም ) ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት በቡራዮ ከተማ ለደረስው አስከፊ ጭፍጨፋ ስለባ ለሆኑ ወገኖቻችን የገንዘብ ማስባስብ ዘመቻ ጀምሯል። የድርጅቱ ሊቀመንበር የሆኑት የሰብ ዓዊ መብት ተሟጋች አርቲስት ታማኝ በየነ ጉዳተኞቹን ስፍራው ድረስ በመሄድ ከጎበኙ በኋላ ጎፈንድ አካውንት በመክፈት በአፋጣኝ ዜጎችን ለመታደግ የገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻውን አስጀምረዋል። ግሎባል አሊያንስ የጠየቀውን የእርዳታ ጥሪ ተከትሎ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ፈጣን ምላሻቸውን እየሰጡ ነው። እሳክሁንም ከሁለት መቶ ሽህ ዶላር በላይ ተሰብስቧል። ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት ”Global Alliance for the Rights of Ethiopians” በተለያዩ የዓለማችን ክፍል በሚኖሩ ስደተኛ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ጉዳት ሲደርስባቸው እገዛ ያደርጋል። በተጨማሪም በአገራቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ለተፈጸሙባቸው፤ በሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ከአማካኝነት ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው ጉዳት የደረሰባቸውን ኢትዮጵያዊያንም ሲረዳ ቆይቷል። የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሰራተኞች፤ የጋሞ ጎፋ ዞን አስተዳደርን ጨምሮ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የገንዘብና የቁሳቁስ አስተዋጾ በማድረግ አጋርነታቸውን አሳይተዋል። ታዋቂው የኪነጥበብ ባለሙያው ቴዎድሮስ ከሳሁን ከቡራዩና አካባቢው ለተፈናቀሉ ዜጎች የገንዘብ ልገሳ አድርጓል ።

No comments:

Post a Comment