Wednesday, September 26, 2018

ብርሃኑ ተክለያሬድና መኮንን ለገሰ ተፈቱ


(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 16/2011) በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ ከተከሰተው አልመረጋጋት ጋር በተያያዘ የታሰሩት ብርሃኑ ተክለያሬድና መኮንን ለገሰ ዛሬ ከእስር ተለቀቁ።

የአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮችና አባላት ወደ ኢትዮጵያ በገቡበት ወቅት አስተባባሪ በመሆን ሲሰሩ የነበሩት ሁለቱ ወጣቶች የታሰሩት በርካታ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች በታፈሱበት ወቅት እንደነበርም ይታወሳል።

ሁለቱ ወጣቶች ዛሬ ከወህኒ ወጥተው ቤተሰባቸውን መቀላቀላቸው ተረጋግጧል።

No comments:

Post a Comment