Tuesday, September 18, 2018

አቶ ለማ መገርሳ የኢሳት የዓመቱ ምርጥ ሰው ተሸላሚ ሆኑ

Bildergebnis für ለማ መገርሳ(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 8/2011) ኢሳት በየዓመቱ በሚያዘጋጀው የዓመቱ ምርጥ ሰው ሽልማት አቶ ለማ መገርሳ የ2010 አሸናፊ ሆኑ።
በህዝብ ድምጽ የሚካሄደውንና በአንጋፋው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ ስም የተሰየመውን የዓመቱ ምርጥ ሰው ሽልማት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ማሸነፋቸው የተገለጸው ዕሁድ ዕለት በዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በተካሄደ ስነ-ስርዓት ነው።
መስከረም 6/2011 በተካሄደው በዚህ በኢሳት የአዲስ ዓመት ዝግጅት ላይ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ስራዎቻቸውን አቅርበዋል።
የኢሳትን የ8 ዓመታት ጉዞ የሚያሳይ ስዕል ለጨረታ ቀርቦ በ30ሺህ የአሜሪካን ዶላር ተሽጧል።

ለ7ኛ ጊዜ በተካሄደው የኢሳት የዓመቱ ምርጥ ሰው ሽልማት የ2011 አሸናፊ የሆኑት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ ከመራጮቹ ውስጥ ከፍተኛ ድምጽ በማግኘት ያሸነፉ ሲሆን ቅዳሜ ዕለት ዋሽንግተን በተካሄደው በኢሳት ዓመታዊ ዝግጅት ላይም አሸናፊነታቸው በይፋ ታውጇል።
በአንጋፋው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ ስም የተሰየመው የኢሳትን ዓመታዊ የምርጥ ሰው ሽልማት አምና ያሸነፈው ዝነኛው ድምጻሚ ቴዎድሮስ ካሳሁን/ቴዲ አፍሮ/ እንደነበርም ማስታወስ ተችሏል።
አቶ አንዱዓለም አራጌ፣ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳና ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ እንዲሁም ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ቀደም ሲል የኢሳትን የሙሉጌታ ሉሌ መታሰቢያ ሽልማትን አግኝተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም የሽልማት ስነ-ስርዓቱ በተካሄደበት የኢሳት አዲስ ዓመት ዝግጅት በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ቁጥር የተጀመረ ሲሆን ኮሜዲያን መስከረም በቀለ ስራዎቹን በማቅረብ ታዳሚውን አዝናንቷል።
የኢሳትን የ8 ዓመታት ጉዞ የሚያሳይ ምስል ለጨረታ ቀርቦ የማያ ሪልስቴት ብሮከሬጅ ባለቤት አቶ አሌክ መካንንት ታረቀኝ 6ሺህ 500 የአሜሪካን ዶላር በመክፈል በአጠቃላይ በ30ሺህ ዶላር አሸናፊ በመሆን ወስደውታል።
ለኢሳት የ8 ዓመታት ጉዞ አስተዋጽኦ ላደረጉ ግለሰቦችና ድርጅቶች የምስጋና ሰርተፊኬት ተበርክቷል።

No comments:

Post a Comment