Monday, September 3, 2018

በቴፒ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የተቃውወሞ ሰልፍ አደረጉ

 ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 28 ቀን 2010 ዓ/ም ) ከመልካም አስተዳደር፣ ከሙስናና ከዘረኝነት ጋር በተያያዘ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች የመንግስት ባለስልጣናት ተገቢውን መልስ አልሰጡንም በሚል ዛሬ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ወደ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞአቸውን ሲገልጹ ውለዋል። ከአስተባባሪዎች መካከል አንዱ የሆነው አቶ ሚስጢሩ ሲሳይ እንደገለጸው ሰልፉ የተደረገው እስካሁን ሲንከባለሉ የነበሩ ጥያቄዎች እንዲመለሱ ለመጠየቅ ነው ብለዋል። በጉዳዩ ዙሪያ የክልሉን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

No comments:

Post a Comment