Tuesday, September 4, 2018

በሃረሪ ክልል የህግ የበላይነት እንዲከበር ተጠየቀ

 ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 29 ቀን 2010 ዓ/ም ) የክልሉ ም/ል ፕሬዚዳንት አቶ ጋዲሳ ተስፋዬ፣ የደቡብ ምስራቅ እዝ ምክትል አዛዥ፣ ጄ/ል ዱባለ አብዲ፣ የክልሉ ፍትህና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ በመሩት ስብሰባ የክልሉ የጸጥታ ችግር እየተባባሰ መምጣቱን ተናግረዋል። ምክንያቱ ደግሞ ከአጎራባች ክልሎች ተደራጅተው የሚመጡ እና በተለያዩ ሰዎች በግልጽም በስወርም ድጋፍ የሚደረግላቸው ሃይሎች ናቸው ብለዋል። የእነዚህ ሰዎች ዋና አላማ የሃይማኖት እና የብሄር ግጭት በመፍጠር የተጀመረውን የለውጥ ሂደት ማደናቀፍ ነው ያሉት የፍትህ ቢሮ ሃላፊው አቶ አበበ፣ ክልሉ በሳለም የቆየው ህዝቡ በሰላምና በፍቅር ተቻችሎ የመኖር ባህሉ ስላለው እንጅ ክልሉን በድሬዳዋና በጅግጅጋ እንተፈጠረው የችግር ቀጠና ለማድረግ አስበው ነበር ብለዋል። የደቡብ ምስራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ዱባለ አብዲ በበኩላቸው ወጣቶች “ አባገዳዎችና ቄሮዎች የመንግስትን ስራ መተካት የለባቸውም፣ የሰላም አጋዥ መሆን አለባቸው፣ መንግስት ግንዛቤ ይሰጥ በሚ እስካሁን ታግሶ ቆይቷል” ብለዋል። ከተሰብሳቢዎች መካከል 3 ዓይነት ቄሮዎች መኖራቸውን የተናገሩ አሉ። አንደኛው አሁንም ለውጡን ለማስቀጠል የሚፈልጉ ሲሆኑ፣ ሌሎች ደግሞ በገንዘብ እየተገዙ የመጣውን ለውጥ ለመቀልበስ የሚሞክሩ በብሄርና ሃይማኖት ለማጋጨት የሚመክሩ ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ችግር ሲፈጠር ጠብቀው የሚዘርፉ ናቸው ብለዋል። መንግስት ተቃዋሚዎችንና የመብት ተሟጋቾችን እያሳተፈ የዜጎችን ደህንነትና ሰላም ያስጠብቅ ብለዋል። አንዳንዶች በህዝቡ መካከል ችግር የለም፣ ችግር የሚፈጥሩት ላለፉት 27 አመታት ስልጣናቸውን ተገን አድርገው በሃይማኖትና በብሄር ሲያገጩ የነበሩ ናቸው ፣ እነዚህ ሰዎች አሁንም ስልጣን ላይ ናቸው፣ እነሱ እስካሉ ድረስ ሰላም አይኖርም ብለዋል። ብክልሉ የሁሉንም ህዝብ ጥቅም እኩል የሚያስከብሩ አስተዳደሪዎች እንዲሾሙላቸው ጠይቀዋል።

No comments:

Post a Comment