Thursday, November 2, 2017

አዲሱ የአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ “ የባርነት አዋጅ ነው” ሲሉ በውጭ የሚገኙ መሪዎች ገለጹ

በስደት የሚገኙ የሠራተኛ መሪዎች ባወጡት መግለጫ፣ በአዲስ የሠራተኛ አዋጅ ሥም በሃይል ሊጫን የታሰበው የባርነት አዋጅ ነው ብለዋል። ሰራተኛው አዲሱን አዋጅ ለመቃወም የስራ ማቆም አድማ ማድረግ አለማቀፍ መብቱ ቢሆንም፣ በስልጣን ላይ ያሉት የሰራተኛ መሪዎቹ የሠራተኛውን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚበቃ ሰብዕናም ሆነ ታሪክ የሌላቸው በሕወሃት የተሾሙ ናቸው ሲል መግለጫው ያትታል። ሰራተኛው በሥርዓቱ ላይ እንዳያምጽ ከማባበልና ለሥርዓቱ የመተንፈሻ ጊዜ ለማስገኘት የይስሙላ መግለጫ ከማውጣት አልፈው አሁን በኮንፌዴሬሽኑ አመራር ላይ ያሉት የሕወሃት ተሹዋሚዎች ከፈጣሪያቸው ሕወሃት ጋር በቁርጠኝነት ይታገላሉ ብሎ ሰራተኛው እንዳይታለል ምክራቸውን ለግሰዋል። ሰራተኛው በዘር፣ ሃይማኖትና ቋንቋ መስመር ሳይከፋፈል በጋራ በመቆም መደባዊ ጥቅሙን ለማስከበር ትግሉን እንዲያጠናክር መሪዎቹ ጥሪ ያቀርባሉ።፡

No comments:

Post a Comment