Monday, November 20, 2017

የሁሌ ቦራ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ወጡ

ለሳምንታት ትምህርታቸውን አቋርጠው የቆዩ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ለጥያቄያቸው መልስ የሚሰጣቸው አካል ማጣታቸውን ተከትሎ ዛሬ ህዳር 11 ቀን 2010 ዓም ዩኒቨርስቲውን ለቀው ወጥተዋል፡
ተማሪዎቹ አቶ ለማ መገርሳ መጥቶ እንዲያነጋግራቸው ጥያቄ አቅርበው ነበር። ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ከሌሊቱ 7 ሰዓት ላይ የመከላከያ አባላት ወደ ግቢያቸው ገብተው ደብደብዋቸው ነበር። ይህን ተከትሎ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችም ትምህርት በማቆም ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ድጋፋቸውን ገልጸዋል።
ተማሪዎች ትምህርት እንዲጀምሩ ለማድረግ የተደረገው ሙከራ ባለመሳካቱ ዛሬ ዩኒቨርስቲውን ለቀው ወጥተዋል።

ለሳምንታት ትምህርት አቋርጠው የቆዩት የሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በአባገዳዎች ጥረት ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ላይ ትምህርታቸውን ጀምረዋል። አባ ገዳዎቹ ተማሪዎች ያነሱዋቸው ጥያቄዎች አንድ በአንድ እንደሚፈቱላቸው ቃል በመግባት ለሳምንታት ሲካሄድ የነበረው የትምህርት ማቆም አድማ እንዲቋረጥ አድርገዋል። ተማሪዎቹ መከላከያ ከግቢያቸው እንዲወጣ፣ “ፒስ ፎረም” ወይም የሰላም ፎረም የሚባለው የህወሃት የስለላ መዋቅር እንዲፈርስ ጥያቄ አቅርበው ነበር። መከላከያም ከግቢው እንዲወጣ እንዲሁም ፒስ ፎረም የሚባለውም እንደሚፈርስ ቃል ተገብቶላቸዋል።

No comments:

Post a Comment