Monday, November 27, 2017

የኮካ ኮላ ፋብሪካ ንብረት የሆነ ስኳር ተወርሶ ከሶማሊ ክልል ለተፈናቀሉት እንዲውል ተወሰነ

(ኢሳት ዜና ህዳር 18 ቀን 2010 ዓም)
ጠቅምት 29 ቀን 2010 ዓም ከአዳማ ተነስቶ ወደ ባህርዳር ይጓዝ የነበረ በ8 ተሽከርካሪዎች የተጫነ 720 ኩንታል ስኳር ጎሃ ጽዮን ከተማ ላይ በኦሮምያ ፖሊስ ከተያዘ በሁዋላ፣ የከተማው ፍርድ ቤት ስኳሩ ከሶማሊ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች እንዲከፋፈል ውሳኔ አሳልፏል። ከ8ቱ መኪኖች መካከል በአንደኛው መኪና ላይ የነበረው ስኳር በገበያ ቀን ለህዝቡ አከፋፍለውታል።
የኮካ ኮላ አምራች ኩባንያ ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ስኳሩን በህጋዊ መንገድ እንደገዛው ከኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን የአዳማ መጋዘን ክፍያ ፈጽሞ እንደተረከበ ገልጿል።
የኦሮምያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የግዢ ሰነዱን በማዬት ስኳሩ እንዲመለስ ለወረጃርሶ ወረዳ ፖሊስ መምሪያ ጽ/ቤት ደብዳቤ የጻፈ ቢሆንም፣ የ6 መኪኖች ጭነት ስኳር አስቀድሞ ለህዝቡ የተከፋፈለ በመሆኑ ኩባንያው ስኳሩን መልሶ የማግኘቱ እድል ተሟጧል

No comments:

Post a Comment