Tuesday, November 28, 2017

ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚዓብሄር ህወሃትን እንዲመሩ መመረጣቸው በስፋት እየተነገረ ነው

በከፍተኛ ወታደራዊ ጥበቃ ስር ሆኖ ግምገማ እያደረገ የሚገኘው ህወሃት የድርጅቱን ሊቀመንበርና የክልሉን ርዕሰ መስተዳደር አቶ አባይ ወልዱን ከስልጣን ካነሳ በሁዋላ፣ የድርጅቱን ሊቀመንበርነት ቦታ ለወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሄር የክልሉን መስተዳደርነት ቦታ ደግሞ ለአቶ አለም ገብረዋህድ እንደተሰጡ ለድርጅቱ ቅርበት ያላቸው ሰዎች እየገለጹ ነው።

እጅግ ሚስጢራዊ ሆኖ በሚካሄደው ግምገማ አቶ አለም ገብረዋህድና ዶ/ር አዲስ አሌም ባሌማ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። ነባር የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት የሆኑትን አቶ ጎበዛይ ወ/አረጋይ እና ቅዱሳን ነጋን ጨምሮ በርካታ አባላቱ ከማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት እንደሚሰናበቱ ለድርጅቱ ቅርበት አለን የሚሉ ወገኖች እይገለጹ ነው። 
ህወሃት የቀድሞውን ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለቤት እና የኢፈርት ሃላፊ የሆኑትን ወ/ሮ አዜብ መስፍንን ከማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ማገዱን አስታውቋል። ወ/ሮ አዜብ ግምገማ ረግጠው መውጣታቸው በመገናኛ ብዙሃን በስፋት ሲዘገብ ቆይቷል። ወ/ሮ አዜብ ግምገማ አቋርጠው ሲመለሱ በተቀሩት የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ላይ ዛቻ ማሰማታቸው እየተነገረ ነው።

No comments:

Post a Comment