Monday, November 20, 2017

ተከሳሾች ዳኛ ዘርዓይ ወልደሰንበት እንዲነሱላቸው ጥያቄ አቀረቡ

“እሱ ተከራካሪ፣ እሱ መልዕክት አስተላላፉ፣ እሱ ዳኛ ሊሆን አይችልም”  አቶ አታላይ ዛፌ
“የተከሰሳችሁት በወልቃይት አማራ ማንነት ነው ወይስ በሽብርተኝነት የሚለው የሚታይ ይሆናል” ዳኛ ዘርዓይ ወልደሰንበት
“እኚህ ዳኛ  በማህበራዊ ሚዲያ ያቀረቡት የህወሓትን አቋም ነው” ዘመነ ጌቴ
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት የግራ ዳኛ ዘርዓይ ወልደሰንበት ሊዳኙን አይገባም ሲሉ ተከሳሾች ጥያቄ አቅርበዋል። ዛሬ ህዳር 11/2010 ዓም የወልቃይት አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባላት  በአቶ አታላይ ዛፌ አማካኝነት በዳኛው ላይ ተቃውሟቸውን ሲያቀርቡ  በግንቦት 7 እና ኦነግ ክስ የቀረበባቸው ሁሉም ችሎት ውስጥ የነበሩ ተከሳሾች ጥያቄው የሁላችን ነው በማለት ቆመው ተቃውሟቸውን ገልፀዋል።   ወልቃይት አማራ ነው ብለው በህገ መንግስቱ መሰረት ጥያቄያቸውን
በማቅረባቸው መታሰራቸውን የገለፁት አቶ አታላይ ዳኛ ዘርዓይ በማህበራዊ ሚዲያና በቴሌቪዥን ወልቃይት የትግራይ ነው እያሉ አቋማቸውን እየገለፁ ሊዳኙዋቸው እንደማይገባ ተቃውሞ አቅርበዋል። አቶ አታላይ”እሱ ተከራካሪ፣ እሱ መልዕክት አስተላላፉ፣ እሱ ዳኛ ሊሆን አይችልም” ብለዋል።  ዳኛ ዘርዓይ በበኩላቸው “የተከሰሳችሁት በወልቃይት አማራ ማንነት ነው ወይስ በሽብርተኝነት የሚለው የሚታይ ይሆናል” ሲሉ መልሰዋል።
በእነ ክንዱ ዱቤ መዝገብ ስር የተከሰሱትም ተቃውሟቸውን ያቀረቡ ሲሆን 2ኛ ተከሳሽ ዘመነ ጌቴ “ማዕከላዊ የተደበደብኩት ወልቃይት የማን ነው እየተባልኩ ነው። እኚህ ዳኛ  በማህበራዊ ሚዲያ ያቀረቡት የህወሓትን አቋም ነው። የከሰሰኝ ህወሓት ነው። ስለሆነም ግለሰቡ የፖለቲካ ወገንተኝነት አለባቸው። በመሆኑም ጉዳያችንን በገለልተኝነት ሊያዩልን ይችላሉ ብለን አናምንም” የሚል ተቃውሞውን አቅርቧል። በሌሎች መዝገቦችም ዳኛ ዘርዓይ እንዲነሱ ተቃውሟቸውን ያቀረቡ ሲሆን ዳኛው ይነሱልን ያሉበትን ምክንያት በፅሁፍ እንዲያቀርቡ ለህዳር 14፣15 እና 18/2010 ዓም ቀጠሮ ተይዟል።

አቶ ዘመነ ጌቴ ዳኛ ዘርዓይ ወልደሰንበት በማህበራዊ ሚዲያዎች አወጡት ያሉትን ፅሁፍ ይህን ማያያዣ በመጫን ማንበብ ይቻላል፡፡ ( የወልቃይት የማንነት ጥያቄ – በታሪክና በህገ መንግስቱ

No comments:

Post a Comment