Wednesday, November 15, 2017

በህወሀት መንግስት የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት የወጣው ዕቅድ የስርዓቱ የመጨረሻው ሙከራ በመሆኑ ህዝቡ ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል አርበኞች ግንቦት ሰባት ጥሪ አቀረበ

በህወሀት መንግስት የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት የወጣው ዕቅድ የስርዓቱ የመጨረሻው ሙከራ በመሆኑ ህዝቡ ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል አርበኞች ግንቦት ሰባት ጥሪ አቀረበ። ንቅናቄው ለኢሳት እንደገለጸው በስልጣን ላይ ያለው ስርዓት በውድቀት አፋፍ ላይ የሚገኝ በመሆኑ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚደረጉት ሁለገብ ትግሎችን ለማፋፋም ተዘጋጅቷል። የህወሀት መንግስት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በጸጥታና ደህንነት የገጠሙ አደጋዎች ህዝቡን ተስፋ እንዳስቆረጡት የገለጸበት ዕቅድ ግብጽንና ኤርትራን ድጋፍ በመስጠት የሚከስ ነው። አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄንና የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን በሀገሪቱ ለተፈጠሩት ቀውሶች ዋነና ተጠያቂ ያደርጋል።የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ እያደረገ ያለውን ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥልና የኢትዮጵያ ህዝብ በውድቀት አፋፍ ላይ ያለውን ስርዓት ነቅሎ ለመጣል እንዲዘጋጅም ጥሪ አቅርቧል።

No comments:

Post a Comment