Thursday, September 21, 2017

የደረጃ “ለ” ነጋዴዎች የተጣለባቸውን ግብር እንደማይከፍሉ አስታወቁ

(ኢሳት ዜና መስከረም 11 ቀን 2010ዓም) የደረጃ “ለ” ነጋዴዎች የተጣለባቸውን ግብር እንደማይከፍሉ አስታወቁ
በመላ አገሪቱ የሚገኙ የደረጃ “ሐ” ነጋዴዎች በዘፈቀደ የተጣለባቸውን ግብር በመቃወም አድማ ካደረጉ በሁዋላ፣ አሁን ደግሞ ለደረጃ “ለ” ነጋዴዎች የግብር ውሳኔ እየደረሳቸው ሲሆን፣ አሁን አዲሱ ተመን የደረሳቸው ነጋዴዎች እንደማይከፍሉ እያስታወቁ ነው። 
በወልድያ የደረጃ “ለ” ነጋዴዎች ከዚህ በፊት ይከፍሉ ከነበረው ግብር በ10 እጥፍ ጨማሪ ተደርጎባቸው እንዲከፍሉ ተጠይቀዋል። ቀድሞ 10 ሺ ብር ግብር ይከፍል የነበረ አንድ ነጋዴ፣ አሁን 100 ሺ ብር ክፈል መባሉን፣ አንድ ጓደኛው ቀድሞ 6 ሺ ብር ሲከፍል ቆይቶ አሁን 80 ሺ ብር ክፈል መባሉን ተናገሯል። ከአግልግሎት ሰጪ ተቋማት ውጭ ያሉ ነጋዴዎች ደግሞ ከ100 ሺ እስከ 2000 ሺ ግብር ተጥሎባቸዋል። 
ህዝቡ ምንም አይነት ግብር አንከፍልም በማለት እንደ ደረጃ “ሐ” ሁሉ ቅሬታ እያቀረበ መሆኑን ነጋዴዎች ተናግረዋል።
በተለያዪ አካባቢዎች የሚገኙ በርካታ የደረጃ “ሐ” ነጋዴዎች ግብራቸውን አለመክፈላቸውን ሰመጉ ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል።

No comments:

Post a Comment