Wednesday, September 20, 2017

የጸጥታ አካላት በዝርፊያ ላይ ተሰማርተዋል ሲሉ ነዋሪዎች አማረሩ

(ኢሳት ዜና መስከረም 10 ቀን 2010 ዓም) የጸጥታ አካላት በዝርፊያ ላይ ተሰማርተዋል ሲሉ ነዋሪዎች አማረሩ
በደብረታቦር ከተማ የጸጥታ አካላት በምሽት ነዋሪዎችን በመደብደብ ንብረት እንደሚዘርፉ የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ሰሞኑን በከተማው በተደረገ ስብሰባ ላይ ነዋሪዎች እንደተናገሩት በከተማዋ በህገመንግስቱ የተቀመጠው የሃያ አራት ሰዓት የመንቀሳቀስ መብት የለም፡፡
ከምሽቱ ሁለት ሰዓት በኋላ የሚገኝ የከተማዋ ነዋሪም ሆነ እንግዳ በከተማዋ ሲንቀሳቀስ ከተገኘ በታጠቁ ወታደሮች እንደሚደበደብ፣ ከዚያም አልፎ ንብረቱን እንደሚዘረፍ ገልጸዋል፡፡

“በከተማዋ ምንም ዓይነት የመናገር ነጻነት የለም” የሚሉት አንድ ቅሬታ አቅራቢ፣ በየትኛውም አካባቢ የመልካም አስተዳደር ችግር አለ ብሎ የሚናገር ሰው እንደሚታሰርና እንደሚደበደብ ተናግረዋል፡፡
የዚህ ዓይነት ሰቆቃ በየዕለቱ የሚከናወን ድርጊት በመሆኑ ሁሉም የከተማ ነዋሪ በግልጽ የሚመሰክረው የአደባባይ ሚስጢር እንደሆነ የተናገሩት ነዋሪ፣ “በአደባባይ ህዝብ እየተደበደበ ነው ሲል አክለዋል።

No comments:

Post a Comment