Monday, September 25, 2017

የአማራ ክልል የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ ስልጣን እለቃለሁ በማለት ተናገሩ

(ኢሳት ዜና መስከረም 15 ቀን 2010 ዓም) የአማራ ክልል የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ ስልጣን እለቃለሁ በማለት ተናገሩ
ምንጮች እንደገለጹት የጸጥታ ዘርፍ ሃፊው አቶ ፍሰሃ ወ/ሰንበት ፣ በብአዴን አባላት ሳይቀር መገለላቸውን፣ ያራሳቸውን ወገን እንደሚያሳፍኑ እንዲሁም በክልሉ ህዝብ ላይ በደል እንደሚፈጽሙ ተደርጎ እንደሚነገርባቸው፣ በክልሉ ህዝብ ዘንድም እንደ አማራ እንደማይታዩ በምሬት ተናግረዋል።
ሃላፊው ይህን የተናገሩት ከሃላፊነት የሚነሱ እና በምትካቸው የሚሾሙትን የክልሉን ባለስልጣናት ለመለየት ኮሚቴ መቋቋሙን ተከትሎ፣ ከሃላፊነት እነሳለሁ በሚል ስጋት ስለገባቸው ሊሆን እንደሚችል ታዛቢዎች ይናገራሉ። ፍሰሃ ወልደሰንበት ከሙስና ጋር በተያያዘ የእስር ፍርድ የተወሰነባትን የህወሃት የደህንነት አባል የሆነቸውን ሰላም በሪሁን በልዩ ትእዛዝ ከእስር በመፍታት ወደ ስራዋ እንድተመለስ በማድረጉ ተገምግሞ ነበር።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ በቅርቡ ወደ ትግራይ ለእርቅ የሄዱትን የብአዴን ባለስልጣናት እና የአገር ሽማግሌ የተባሉትን ግለሰቦች፣ “ፈሪዎች “ብለው ተችተዋል የተባሉት የፕሬዚዳንቱ ልዩ አማካሪን አቶ ሰማ ጥሩነህንና ምክትል ፕሬዚዳንቱን አቶ ተስፋዬን ከስልጣን ለማንሳት እና እርምጃ ለመውሰድ እንቅስቃሴ መጀመሩን ምንጮች ተናግረዋል:፡

No comments:

Post a Comment