Wednesday, September 13, 2017

ኢትዮጵያ በሰው ሃብት ልማት ከአለም አገራት የመጨረሻውን ደረጃ ያዘች

(ኢሳት ዜና፣ መስከረም 3 ቀን 2009 ዓም) 
የአለም የኢኮኖሚ ፎረም 130 አገራትን በማወዳደር ባወጣው ሪፖርት፣ ዜጎቻቸውን በትምህርት በማነጽና እውቀታቸውን በመጠቀም ደካማ ስራ ከሰሩት አገራት መካከል ኢትዮጵያን በግንባር ቀደምነት ጠቅሷል። በአፍሪካ ሩዋንዳ፣ ጋና፣ ካሜሩን እና ሞሪሺየስ በተከታታይ 71፣72፣ 73 እና 74 ኛ ደረጃ በመያዝ የተሻለ ስራ የሰሩ አገራት ተብለው ሲወደሱ፣ ኢትዮጵያ ዝቅተኛ ስራ ከሰሩ የአፍሪካ አገራት መካከል 127ኛ ደረጃ በመያዝ ደካማዋ አገር ተብላለች። 
በስልጣን ላይ ያለው ገዢ ቡድን አገሪቱ በትምህርቱ ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት እንዳስመዘገበች በተደጋጋሚ በመገናኛ ብዙሃን ቢናገርም ፣ የአለም የኢኮኖሚ ፎረም ግን ከትምህርት ጥራት ጀምሮ ያሉ መስፈርቶችን በመጠቀም ባደረገው ምርመራ ኢትዮጵያ እጅግ ደካማ አፈጻጸም የታየባት አገር ናት ሲል ገልጿል።

No comments:

Post a Comment