Wednesday, September 27, 2017

መንግስት የውጭ እዳውን እንዲቀንስ አይኤም ኤፍ ገለጸ

(ኢሳት ዜና መስከረም 17 ቀን 2010 ዓም) መንግስት የውጭ እዳውን እንዲቀንስ አይኤም ኤፍ ገለጸ
የአለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት ባወጣው ሪፖርት ምንም እንኳ የመካከለኛ ጊዜ እድገቱ አወንታዊ ገጽታ የሚኖረው ቢሆንም፣ በአሁኑ ሰአት የሚታየው የበጀት ክፍተት መስተካከል እንዳለበት እንዲሁም ከብድር ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች ን ለመቅረፍ እርምጃ መወሰድ እንዳለበት ገልጿል። የመንግስት የገንዘብ ፖሊሶች የበጀት ክፍተቱንና የውጭ እዳውን በመቀነስ በኩል ትኩረት ማድረግ አለበት ያለው የገንዘብ ተቋሙ፣ ይህን ለማድረግ በመንግስት የሚገነቡና ከፍተኛ ብድር የሚጠይቁ ፕሮጀክቶች እንዲቀንሱ መክሯል። 
አሁንም የማህበራዊ አገልግሎት ፍላጎቱ ከፍተኛ መሆኑን የጠቀሰው አይ ኤም ኤፍ፣ ይሁን እንጅ የግል ባለሀብቶችን በማሳተፍ ችግሩን መቅረፍ እንደሚቻል አመልክቷል። የገንዘብ ፖሊሲው መጥበቅ እንዳለበትም ድርጅቱ መክሯል። 
አይ ኤም ኤፍ አሁን ያለው አወንታዊ የኢንቨስትመንት ከባቢ መሰረታዊ የሚባሉ ለውጦችን በመውሰድ ሊሻሻል እንደሚገባው የገለጸው አይ ኤም ኤፍ፣ በተለይ የገንዘብ ምንዛሬው ከገባያ ለውጡ ጋር ተያይዞ እንዲሄድ መደረጉ ፉክክር እንዲኖር እንደሚያደርግና ኢኮኖሚውን እንደሚጠቅመው ገልጿል። የአገሪቱ ኢኮኖሚ 9 በመቶ ማደጉንም ድርጅቱ አስታውቋል።

No comments:

Post a Comment