Saturday, September 20, 2014

CPJ- ባለፉት ዘጠኝ ወራት አገር ጥለው የተሰደዱት ጋዜጠኞች ቁጥር 34 ደርሷል

CPJ-የተባለው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ባለፈው ሳምንት በለቀቀው ሪፖርት በአለፉት አስር አመታት ለስደት የሚዳረጉ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ቁጥር ከአለም አንደኛ ነው ብሏል።  የኢትዮጵያዉን ጋዜጠኞች መሰደድ CPJ በሚል ምፃረ-ቃል የሚጠራዉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት እንዳስታወቀዉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ሐገር ጥለዉ የተሰደዱት ኢትዮጵያዉን ጋዜጠኞች ቁጥር ከሠላሳ በልጧል።ሰሞኑንም ሰዎስት ጋጠኞችና አሳታሚዎች ተሰደዋል በተደጋጋሚ ተነግሯል።ዛሬም እንደግመዋል።የኢትዮጵያ መንግሥት የሚደርስባቸዉን ጫና ሽሽት ሐገር ጥለዉ የሚሰደዱት የነፃ ወይም የግል ጋዜጠኞች ቁጥር እያሻቀበ ነዉ።CPJ በሚል ምፃረ-ቃል የሚጠራዉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት እንዳስታወቀዉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ሐገር ጥለዉ የተሰደዱት ኢትዮጵያዉን ጋዜጠኞች ቁጥር ከሠላሳ በልጧል።ሰሞኑንም ሰዎስት ጋጠኞችና አሳታሚዎች ተሰደዋል።በመሆኑም አገር ጥለው የተሰደዱት ጋዜጠኞች ቁጥር 34 ደርሷል፡፡ በአሁኑ ወቅት ገዥው ፓርቲ ከሚወስደው አፈና፣ የማተሚያ ቤትና ሌሎችም ችግሮች ተዳምረው የስደተኛ ጋዜጠኞች ቁጥር ከዚህም እንደሚያሻቅብ ይጠበቃል፡፡ በቅርብ የተሰደዱት ጋዜጠኞች የደህንነት ሁኔታ አንጻር ስማቸውን መጥቀስ አልፈለኩም፡፡ እስካሁን አገር ጥለው የተሰደዱ ጋዜጠኞች ስም ዝርዝር

1.  ጋዜጠኛ በትረ ያቆብ (የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ ፕሬዝደንት፣ የኢቦኒ መጽሄት አምደኛ፣ የአሳማን መጽሄት ኮረስፖንዳንት፣ የዳይሊ ጆርናሊስት ቋሚ ጸሃፊ፣ የኢካድፍ         ፎረም ጸሃፊ፣ የኢትዮጵያ ሆት ክለብ ብሎገር)
2.  ጋዜጠኛ ተሰማ ደሳለኝ (የኢቦኒ መጽሄት ማኔጅንግ ኢዲተር)
3.  ጋዜጠኛ ዘሪሁን ሙሉጌታ (የሰንደቅ ጋዜጣ ከፍተኛ ሪፖርተር፣ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ የህዝብ ግንኙነት)
4.  መላኩ አማረ (የሊያ መጽሄት ማኔጅንግ ኢዲተርና ባለቤት)
5.  ጋዜጠኛ ግዛው ታዬ (የሎሚ መጽሄት ማኔጂንግ ዳይሬክተር)
6.  ጋዜጠኛ ቶማስ አያሌው (የአፍሮ ታይምስ ማኔጅንግ ዳይሬክተር)
7.  ጋዜጠኛ ሰብለወርቅ መከተ (የሎሚ መጽሄት ከፍተኛ ሪፖርተር)
8.   ጋዜጠኛ አቦነሽ አበራ (የሎሚ መጽሄት ከፍተኛ ሪፖርተር)
9.   ጋዜጠኛ ሰናይ አባተ (የሎሚ መጽሄት ዋና አዘጋጅ)
10.  ጋዜጠኛ አስናቀ ልባዊ (የጃኖ መጽሄት ማኔጂንግ ዳይሬክተር)
11.  ጋዜጠኛ ሲሳይ ሳይሌ (የፒያሳ መጽሄት ማኔጂንግ ዳይሬክተርና ባለቤት)
12.  ጋዜጠኛ ሐብታሙ ቦጋለ (የቀድሞ ፍትህ ጋዜጣ ሪፖርተር እና የአንድነት ፓርቲ ሚዲያ ዳይሬክተር)
13.  ጋዜጠኛ እንዳልካቸው ተስፋዬ (የአዲስ ጉዳይ መጽሄት ማኔጂንግ ዳይሬክተርና የሮዝ አሳታሚ ድርጅት ስራ አስኪያጅ)
14. ጋዜጠኛ ኢብራሂም ሻፊ (የአዲስ ጉዳይ መጽሄት ምክልት ዋና አዘጋጅ)
15. ጋዜጠኛ እንዳለ ተሺ (የአዲስ ጉዳይ መጽሄት ከፍተኛ አዘጋጅ)
16. ጋዜጠኛ ሀብታሙ ስዩም (የአዲስ ጉዳይ መጽሄት አምደኛ፣ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ ገንዘብ ያዥ)
17. ጋዜጠኛ ዳዊት ሶሎሞን (የፍኖተ ነጻነት አዘጋጅ፣ የላይፍ መጽሄት ዋና አዘጋጅ፣ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ አመቻች ኮሚቴ አባል)
18. ጋዜጠኛ ዳንኤል ድርሻ (የሎሚ መጽሄት ሚዲያ ዳይሬክተር)
19. ጋዜጠኛ ብስራት ወ/ሚካኤል (በተለያዩ ጋዜጦች፣ መፅሔቶች የራሱ “አዲስሚዲያ” ብሎግን ጨምሮ በተለያዩ ድህረ-ገፆች አዘጋጅ እና ፀሐፊ
20. በቅርቡ የተሰደዱት አስራ አምስት(15) ጋዜጠኞች የደህንነት ሁኔታ አንጻር ስማቸውን መጥቀስ አልፈለኩም፡፡ እነዚህ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች የጋዜጠኛ ሞያ ስነምግባሩን በመጠቀም የተለያዩ የፖለቲካ፣ ሰብዓዊ መብት ጥሰትና ማኀበራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው በራሳቸውና በተለያየ የብዕር ስሞች እንደሚፅፉ ይታወቃል፡፡ ጋዜጠኞቹ ከዚህ በፊትም በመንግስት ደህንነት ኃይሎች በተለያየ ስፍራዎች እገታ አልፎ ተርፎም ዕስር ድብደባና እንዲውም (በተመሳሳይ ፆታ) ኢፆታዊ ጥቃት፣ ከስልክ ጠለፋ እስከ ዛቻና ማስፈራራት ይደርስባቸው እንደነበር ከዚህ ቀደም የወጡ መረጃዎች ቢያመለክቱም፤በተለይ ከጥቅምት 2006  ዓ.ም. ከአዲሱ ጋዜጠኞች ማኀበር መመስረት ሂደት ጀምሮ እና በሚያዚያ ወር 2006 ዓ.ም. 3 ጋዜጠኞችን እና 6 የዞን 9  ብሎገሮች በመንግስት ከታሰሩ በኋላ የመንግስት ደህንነቶች ክትትል ከበፊቱ በበለጠ ሁኔታ ተጠናክሮ መቀጠሉንና ቀጣዩ እስረኞች እነሱ እንደሚ ሆኑ በግልፅ ይነገራቸው ነበር በቅርቡ ከታሰሩት ጋዜጠኞችና ብሎገሮች የእስር ስም ዝርዝር ውስጥ ስማቸው በግንባር
ቀደምነት እንደሰፈረና በዕነርሱም ዙሪያ መረጃ እየሰበሰበ መሆኑ ምንጮች አረጋግጠው እንደነበረ ይታወቃል፡፡ ቀደም ሲል የማኀበሩ ፕሬዘዳንት ጋዜጠኛ በትረ ያዕቆብ፣ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ጋዜጠኛ ዘሪሁን ሙሉጌታ፣የህዝብ ግንኙነት ምክትል ኃላፊው ጋዜጠኛ ሐብታሙ ቦጋለ እንዲሁም የአንድነት ገንዘብ ያዥ ማይክል ጌታሁን እና መስራች አባል ጋዜጠኛ ተሰማ ደሳለኝ መሰደዳቸው አይዘነጋም፡፡ በአጠቃላይ ጋዜጠኛ ብስራት ወ/ሚካኤልን ጨምሮ በ2006 ዓ.ም. ብቻ 34 የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ሲሰደዱ፤3 የውጭ ዜጎች ጋዜጠኞችን ጨምሮ 20 ጋዜጠኞችና ብሎገሮች ደግሞ በእስር ላይ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ በኢትዮጵያ ፍትሕ ሚኒስቴር መከሰሳቸውን ተከትሎ ሀገር ጥለው የተሰደዱ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች የደኅንነት ስጋት ገጥሞናል ይላሉ። የጋዜጠኞቹ የደኅንነት ስጋት ተዓማኒ ከሆነ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት የኬንያ ፅ/ቤት ተናግሯል። አቶ ግዛው ታዬ የሎሚ መጽሔት ስራ አስኪያጅ ነበሩ። በመጽሔታቸው በወጡ ጽሁፎች ድርጅቱና ሥራ አስኪያጆቹ ሐሰተኛ ወሬ አትሞ በማውጣትና ሕዝብን በማነሳሳት ወንጀል’ በሚሉ ሁለት ክሶች ሰኔ 6 ቀን 2006 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፍትሕ ሚኒስቴር መከሰሳቸውን ተከትሎ ፍርድ ቤት ቆመውም ነበር። አቶ ግዛው ታዬ በመጀመሪያው የፍርድ ቤት ውሎ የተጠየቁትን የ50 ሺህ ብር ዋስትና አስይዘው ሌላ ቀጠሮ ከተቀበሉ በኋላ ግን በኢትዮጵያ አልቆዩም። እርሳቸው የኢትዮጵያ መንግስት ያስረኛል ወይም ሌላ ጠንካራ እርምጃ ይወስድብኛል በሚል ስጋት ከሃገር ለመውጣት ቢችሉም አሁን ባሉበት ሃገር የደህንነት ስጋት ተሰምቶኛል ይላሉ። የአፍሮ ታይምስ ጋዜጣ ስራ አስኪያጅ አቶ ቶማስ አያሌው ና የጃኖ መጽሄት ስራ አስኪያጅ አቶ አስናቀ ልባዊም ከኢትዮጵያ ከተሰደዱ ጋዜጠኞች መካከል ይገኙበታል።አቶ ግዛው ታዬ እንዲሁም ጋዜጠኛ ሐብታሙ ቦጋለን ጨምሮ አሁን በጎረቤት ሃገር በአብሮነት የሚኖሩት ሶስቱ የግል-ፕሬስ ባለሙያዎች የደህንነት ስጋት ተደቅኖብናል ይላሉ። የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት የኬንያ ቢሮ ቃል አቀባይ ኢማኑኤል ኒያቤራ የደህንነት ስጋትን ጨምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ከ14 የተለያዩ ሃገራት የመጡ ስደተኞች መኖራቸውንና ይናገራሉ። የሶስቱን ጋዜጠኞች የደህንነት ጉዳይ ተጠይቀው ሃሳብ ከመስጠት የተቆጠቡት ቃል አቀባዩ የተለያዩ ድጋፎች እንደሚያደርጉ ግን ተናግረዋል። ”የመጡት በተለያዩ ፈተናዎች ምክንያት ነው። ይህ የደህንነት ስጋትን ይጨምራል።ለምሳሌ የኢትዮጵያውያኑ ጉዳይ ተዓማኒ መሆኑን ለማረጋገጥ ቃለ-መጠይቅ እናደርግላቸዋለን። ጉዳያቸው ተዓማኒ ሆኖ ስናገኘው ደህነታቸው ሊጠበቅ የሚችልበትን እርምጃ እንወስዳለን። ለፖሊስ ጣቢያዎች በቀረቡና ደህንነታቸው የተጠበቀ አካባቢዎች እናስቀምጣቸዋለን። ልዩ ትኩረት እንዲያገኙም እናደርነጋለን። ለምሳሌ አንዳንዶቹ ያለባቸው የደህንነት ስጋት በቋሚነት እስኪቀረፍ ድረስ ወደ አደባባይ መውጣት ስለማይችሉ የሚፈልጉትን አግልግሎት እና ምግብ እናቀርባለን።” በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት ድረ-ገጽ መረጃ መሰረት 19,920 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በኬንያ የሚገኙ ሲሆን 11,670ው ጥገኝነት ፈላጊዎች ናቸው እንዲሁም በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት ድረ-ገጽ መረጃ መሰረት 16,200 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በግብፅ ካይሮ የሚገኙ ሲሆን 16,200ው ጥገኝነት ፈላጊዎች ናቸው ፍርድ ቤት የተሰደዱ ጋዜጠኞችን ጉዳይ በሌሉበት ማየቱን ቀጥሏል

ጳጉሜን ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት በመግለጫ የከሰሳቸው ጋዜጠኞች አግር ጥለው ከወጡ በሁዋላ ጉዳያቸው በሌሉበት እየታየ ነው። ከሳምንት በፊት ጥሪ ተደርጎላቸው እንዲቀርቡ የታዘዙት የፋክት፣ አዲስ ጉዳይ እና ሎሚ መጽሄት አዘጋጆችና ባለቤቶች ፍርድ ቤት ለመቅረብ ባለመቻላቸው 17ኛው ወንጀል ችሎት ጉዳያቸውን በሌሉበት ለማየት ተጨማሪ ቀጠሮ ሰጥቷል። ተከሳሾቹ የመንግስታዊ ስርዓቱን በአመጽ ለማፍረስ አስበዋል የሚል ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን፣ እንደማስረጃም የቀረበው ህዝቡን ለአመጽ የሚያነሳሱ ጽሁፎችን አትመው አሰራጭተዋል የሚል ነው። የሎሚ መፅሄት ስራ አስኪያጅ አቶ ግዛው ታዬ ቀድም ብሎ ፍርድ ቤት በቀረሩበት ወቅት በ50 ሺ ብር ቢለቀቁም ከዚያ በሁዋላ በነበሩት ችሎቶች ባለመገኘታቸው ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ፍርድ ቤት ወስኗል። ባለፉት ጥቂት ቀናት የወጡትን የማራኪ መጽሄት ባለቤትና አዘጋጅ ሚሊዮን፣ የቃል ኪዳን መጽሄት አዘጋጅ ኤለያስ ጉዲሳ እና የአዲስ ጉዳይ ዘጋቢ መድሃኒት ረዳን ጨምሮ የተሰደዱት ጋዜጠኞች ቁጥር 34 ደርሷል። ኢትዮጵያ በሚሰደዱ ጋዜጠኞች ቁጥር በአለም ላይ የመጀመሪያውን ደረጃ ይዛ ትገኛለች ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ ባለፉት አስር አመታት ለስደት የዳረጋቸው ጋዜጠኞች ቁጥር ከአለም አንደኛው ነው ተባለ June 25, 2010 | Filed underዜና | Posted by admin ሲ.ፒ.ጄ. የተባለው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ባለፈው ሐሙስ በለቀቀው ሪፖርት በአለፉት አስር አመታት ለስደት የሚዳረጉ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ቁጥር ከአለም አንደኛ ነው ብሏል። በነዚህ አስር አመታት ስልሳ ሁለት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች አገራቸውን ጥለው የተሰደዱ ሲሆን፤ ይህም እስርን፣ ጥቃትን እና ማስፈራራትን ሽሽት እንደሆነ ታውቋል። ባለፈው አመት ብቻ አስራ አምስት ጋዜጠኞች ከኢትዮጵያ እንደሸሹ እና ይህም ነፃው ፕሬስ ያለበት ሁኔታ እየከፋ ስለመሄዱ ማስረጃ ነው ሲል ሪፖርቱ ገልጿል። የወያኔ አገዛዝ የግል መገናኛ ብዙሃንን ነፃነት የሚገድብ ህግ ከማውጣት አንስቶ ጋዜጠኞችን እንዳሻው በማሰር፤ በመክሰስ እና በማስፈራራት ከሞላ ጎደል ነፃውን ፕሬስ መዝጋቱ ይታወቃል። ከኢትዮጵያ ውጭ የሚገኙ ገለልተኛ እና ተቃዋሚ መገናኛ ብዙሃንም ለኢትዮጵያውያን እንዳይተላለፉ ከፍተኛ የአፈና ዘመቻ ያካሂዳል። በተያያዘ ዜና አገዛዙ ሄዘር መርዶክ የተባለችን የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢ ከአገር ማስወጣቱ ታውቋል።
የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር ወይም ኦብነግ የወያኔ ጦር በኦጋዴን 71 ንጹሃን ዜጎችን ገድሏል በሚል በመግለጫው ያወጣውን ክስ ለመመርመር ምስራቅ ኢትዮጵያ የተጓዘችው ሄዘር መርዶክ ባቢሌ ከተማ አካባቢ ለሁለት ቀናት መታሰሯን ብሉምበርግ የዜና አውታር ዘግቧል። ስለጉዳዩ የተጠየቀው በረከት ስምኦን ጋዜጠኛዋ “የኦብነግን ሰዎች ስትፈልግ” ነበር ያለ ሲሆን፤ እሷም በበኩሏ “ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎችን ማናገር ወንጀል መሆኑን አላውቅም ነበር” ብላለች። ጋዜጠኛዋ ሐሙስ እለት ከኢትዮጵያ እንድትወጣ መደረጉ ታውቋል።

ባለፈው የፈረንጆች አመት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ አገራት የፖለቲካ ጥገኝነት መጠየቃቸው ታወቀ እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር በ2009 አመተ ምህረት 42500 ኢትዮጵያውያን በተለያዩ አገራት የፖለቲካ ጥገኝነት መጠየቃቸውን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን በሰጠው መግለጫ አስታወቀ። ይህ ቁጥር በእርስ በርስ ጦርነት የምትታመሰውን ሶማሊያ በዛው አመት ከሸሹት ሰዎች ቁጥር በአራት ሺህ ስድስት መቶ እንደሚበልጥ ታውቋል። ከነዚህ ኢትዮጵያውያን ውስጥ 84 በመቶ የሚሆኑት ወደ ሶማሊያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ግብፅ እና ኬንያ ሄደዋል። ይህ ቁጥር የተሰበሰበው ስደተኞቹ ለየሄዱባቸው አገራት መንግስታት እና ለስደተኛ ድርጅቱ የፖለቲካ ጥገኝነት ለማግኘት ባቀረቧቸው ማመልከቻዎች አማካኝነት ስለሆነ የአጠቃላይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ቁጥር አይወክልም። በያመቱ አገራቸውን ጥለው የሚሰደዱ ቁጥራቸው የማይታወቅ ኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ጥገኝነት እናገኛለን ብለው ስለማይገምቱ በተለያዩ ሃገራት በህገወጥነት እንደሚኖሩ ይታወቃል። በተጨማሪም፥ ቁጥሩ የጉልበት ስራ ፍለጋ ወደ መካከለኛው ምስራቅ እና ሌሎች አገራት በህጋዊ መንገድ የሚሄዱትን የኢኮኖሚ ስደተኞች አያካትትም። የወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያ ያለው የኢኮኖሚ ሁኔታ እየተሻሻለ እና አገሪቱ ወደ ዴሞክራሲ እየሄደች መሆኑን ደጋግሞ ቢናገርም፤ በአስርት ሺሆች የሚቆጠሩ ዜጎች በየአመቱ አገራቸውን እየጣሉ መሰደዳቸው አገዛዙ የሚለው ተቃራኒ እውነት ለመሆኑ ምስክር ነው ሲሉ የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ።


No comments:

Post a Comment