Tuesday, September 23, 2014

ኢሕአዴግ ጋዜጠኞችን እና ፀሃፍያንን በገሃድ ማሳደድ ጀምሯል።

በኢትዬ ምህዳር ጋዜጣ እና በጃኖ መፅሄት በሚፅፋቸው ፁሁፎች በመላ ሀገሪቱ ሀገር ወዳድ እና ፀረ ኢህአዴግ አቃሙን ያሳየው ወጣቱ ሰለሞን መንግስ (ሶል ዘባህርዳር) በኢህአዴግ ካድሪዎች ከፍተኛ ክትትል እየተደረገበት እንደሚገኝ ምንጮቻችን ጠቁመዋል። ቀድሞ ይሰራበት ከነበረው ባህርዳር ዩንበርስቲ ስራ ለቆ ወደ ወረታ እና አለምበር ከተማ አምርቶ የነበረው ሰለሞን ከባድ የሆነ የካድሪዎች ክትትል ህይወቱን እንዳመሰቃቀለው ለማወቅ ተችላል። የጥረት ኢንበስትመንት ባለስልጣን የሆነው ታላቅ ወንድሙ አቶ ታደለ መንግስት ከካድሬዎች ጎን ሆኖ ወንድሙ እንዲሰቃይ እያደረገ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የፎገራ ወረዳ ካቢኔዎች እንዴት አድርገው ሊያስሩት እንደሚገባ እየመከሩ እንዳሉ ታውቃል። የሰባዊ መብት ጥሰት ማድረሳቸውን ያጋለጠባቸው በአለምበር ከተማ የሚገኙ አድማ በታኝ ፖሊሶች መስከረም 4ቀን በምሽት ሊደበድቡት ሲሉ ሰለሞን ሮጦ ማምለጡን ምንጮቻችን አረጋግጠዋል። የኢህአዴግን አንባገነናዊ ስርአት በመቃወሙ በ2002 አም ምርጫ በወረዳው ባለስልጣናት ተደብድቦ የነበረ ሲሆን በህዝብ ቁጣ ከእስር መፈታቱ አይዘነጋም።


No comments:

Post a Comment