Tuesday, September 9, 2014

ፍርድ ቤት የተሰደዱ ጋዜጠኞችን ጉዳይ በሌሉበት ማየቱን ቀጥሏል

ኢሳት ዜና :-መንግስት በመግለጫ የከሰሳቸው ጋዜጠኞች አግር ጥለው ከወጡ በሁዋላ ጉዳያቸው
በሌሉበት እየታየ ነው።
ከሳምንት በፊት ጥሪ ተደርጎላቸው እኢነዲቀርቡ የታዘዙት የፋክት፣ አዲስ ጉዳይ እና ሎሚ መጽሄት አዘጋጆችና ባለቤቶች ፍርድ ቤት
ለመቅረብ ባለመቻላቸው 17ኛው ወንጀል ችሎት ጉዳያቸውን በሌሉበት ለማየት ተጨማሪ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ተከሳሾቹ ህመንግስታዊ ስርዓቱን በአመጽ ለማፍረስ አስበዋል የሚል ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን፣ እንደማስረጃም የቀረበው ህዝቡን ለአመጽ
የሚያነሳሱ ጽሁፎችን አትመው አሰራጭተዋል የሚል ነው።
የሎሚመፅሄትስራአስኪያጅአቶግዝውታዬ ቀድም ብሎ ፍርድ ቤት በቀረሩበት ወቅት በ50 ሺ ብር ቢለቀቁም ከዚያ በሁዋላ በነበሩት ችሎቶች
ባለመገኘታቸው ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ፍርድ ቤት ወስኗል።
ባለፉት ጥቂት ቀናት የወጡትን የማራኪ መጽሄት ባለቤትና አዘጋጅ ሚሊዮን፣ የቃል ኪዳን መጽሄት አዘጋጅ ኤለያስ ጉዲሳ እና የአዲስ ጉዳይ ዘጋቢ
መድሃኒት ረዳን ጨምሮ የተሰደዱት ጋዜጠኞች ቁጥር 20 ደርሷል። ኢትዮጵያ በሚሰደዱ ጋዜጠኞች ቁጥር በአለም ላይ የመጀመሪያውን ደረጃ ይዛ ትገኛለች።


No comments:

Post a Comment