Friday, September 12, 2014

የትግል ምቀኝነት ወይንስ ሰርጎ ገብነት? ስለ ኤልያስ ክፍሌ የማውቀው በፈቃዱ ጌታቸው

ስለ ኤልያስ ክፍሌ የማውቀው—-

ይህ ጽሁፍ የመጨረሻዬ ነው፡፡ እስከሚቀጥለው ስድስት ወር ድረስ፡፡ ለአሁን እስቲ ሰዎችዬ አንድ ነገር ልበላችሁ፡፡ ስለኤልያስ ክፍሌ፡፡እውነት ለመናገር ይህንን ሰው በፎቶ፣በሚጽፋቸው ነገሮችና ከጥቂት አመታት በፊት በእሱ አመራር በከተማ ውስጥ ይበተኑ በነበሩ በራሪ ወረቀቶች ነው የማውቀው፡፡ቅንጅቶች የታሰሩ ጊዜ፡፡ያኔ በጩጬነታችን፡፡ተግባር ሊግ በሚባል እንቅስቃሴ ውስጥ የታቀፉ አንዳንድ ወጣቶች በየትምህርት ቤቱ ፣በማታ ተደብቀው በየመንገዱ ህዝቡን ለትግል ይቀሰቅሱ ነበር፡፡ያኔ Ethiopianreview.com እና Tegbarleague.org በሀገር ቤት አልታፈኑም ነበር፡፡ሌሎችም እነዚህን የመሰሉ የወሬ ምንጮች የተፈቀዱ ነበሩ፡፡ከሰፈር ልጆች ጋር እየተጠራራን በየኢንተርኔት ቤቱ እየሄድን በየቀኑ ምን ተባለ ብለን የምናው በዋናነት የእሱን ገጾች ነበሩ፡፡ያኔ ምንሊክ ሳልሳዊ ምናምን የሚባል ነገር አልነበረም፡፡እንዳውም አንድ ጊዜ የአርበኞች ግንባር ተብሎ ለሚጠራው ታጣቂ ሀይል(በፕሮፌሰር ሙሴ ይመራ ለነበረው) የተለያዩ ቁሳቁሶችንና አልባሳት ይዞ ወደ ኤርትራ እንደሄደም በራሱ ገጽ ላይ ለጥፎ አንብበናል፡፡ስለኤልያስ ጥሩ አመለካከት ስለነበረንም በየመንገዱ በኢትዮጵያን ሪቪው ስም የታተሙ መጽሄቶችን ሳይቀር መማሪያ ይሆኑናል፣ ቅርስም ናቸው ብለን እየገዛን ወደ ቤታችን እንገባ ነበር፡፡ገና ህወአትእንዲህ መሰረት ሳይዝ በፊት የገባ ሰሞን የተለያዩ ሀተታዎችን ይዘው ይወጡ የነበሩ መጽሄቶች፡፡በሀገር ጉዳይ ጥብቅና በመቆም ያቀረባቸው የተለያዩ ጽሁፎች ማየት ልምዳችን ነበር፡፡ምናልባት ኢትዮጵያን ሪቪው ስናነብ እንዳያመልጠን ብለን እናየው የነበረው ኢትዮሚዲያ ብቻ ነበረ፡፡



ኤልያስ ክፍሌ እንዲህ አይነት ጥንካሬና ለሀገር አለኝታ የመሆን ጥረቱን ለማሳየት የሚያስችሉ ብዙ ነገሮች ቢኖሩም ችግር አለበት፡፡ከችግሩ አንዱ ከሌሎች ጋር መስራት አይፈልግም፡፡አሰናካይ ነው፡፡ በእኔ እጅ ከሌለ አንተም ሊኖርህ አይገባም ብሎ በሌላው እጅ ያለን ቆሎ እጅ በመምታት ለማስደፋት የሚፈልግ አይነት ሰው፡፡እንዳንዳንድ የመንደር ምቀኛ ልጆች፡፡ከሌሎች ጋር ቢሰራ ጀግንነት የሚሻሙት ይመስለዋል፡፡ይህንን የታዘብኩት ዛሬ አይደለም፡፡ያኔ ቅንጅቶች የታሰሩ ጊዜ ነው፡፡እንደሚታወቀው በወቅቱ የትግል ምቀኝነት ይፈጽሙ ከነበሩ ሰዎች አንዱ ልደቱ አያሌው ነው፡፡ኤልያስ ክፍሌ በአብዛኛው የቅንጅት አመራር ላይ በነበረው ያልተገባ መንፈስ በየጊዘው የልደቱ አያሌውን አፍራሽ ሀሳብ እየጻፈ ያስነብብ ነበረ፡፡ በተለይ ዶ/ር ብርሀኑን ለማብጠልጠል ከልደቱ አያሌው ጋር እጅና ጓንት ሆነው ነበር ብል ውሸት አይሆንም፡፡ይህ የምለው ነገር ውሸት ነው የሚል ካለ የነበረውን ዞርብሎ እየበረበሩ ማጣቀስ ይቻላል፡፡ትንሽ ግንቦት 7 ሲመሰረት አካባቢ ያሳይ በነበረው ነገር ልብ የገዛ መስሎ ነበር፡፡በተለይ በሼህ አላሙዲን ከተከሰሰ በኋላ ምን እንደነካው አላውቅም አንድ ከግንቦት7 ጋር ያለው ግንኙነት ለትግሉ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቅ የነበረው አይነት መሆን አልቻለም፡፡ የሚያሰረራጫቸው ወሬዎች እንደእሱ አንጋፋና ብዙ ልምድ ካካበተ ሰው የሚጠበቅ አልሆነም፡፡በተለይ ርእዮት አለሙ ከታሰረች በኋላ ምስቅልቅሉ የወጣ መንደርተኛና የምቀኛ ወሬ ማውራት ሆኗል ስራው፡፡በተለይ ከምንሊክ ሳልሳዊ ጋር መስራት ከጀመረ በኋላ፡፡

ኤልያስ ክፍሌ ከዚህ በፊት ከምንሊክ ሳልሳዊ ጋር ስለመስራቱ የሚያሳዩ ምልክቶች የሉም፡፡በሙስሊሞች ትግል ዙሪያ የሚላቸው እንዳንድ ወሬዎች ጥመውት የተወዳጀው የቅርብ ጊዜ ሰራተኛው ይመስለኛል፡፡እኔ የምንሊክ ሳልሳዊ ጽሁፎችን ከአምስት አመት በላይ አውቃቸዋለሁ፡፡እንደዚህ እንደአሁኑ እንዴ እስራኤል፣ ሌላጊዜ ኢራን፣በምስራቅ በምእራብ እያለ በመንፈስ የሚኖር ይመስል ሁሉን አወቅ የወሬ አጠናቃሪ ሆኖ ሲሰራ አላውቀውም፡፡በሆነ ርእስ ዙሪያ ሀሳቡን የሚያሰፍር፣የግል አስተያየቱን በተለያዩ ነገሮች ዙሪያ እየሰጠ ሲጽፍ እንጂ እንደአሁኑ አላውቀውም፡፡ልብ ብሎ ይከታተለው የነበረ ሰው ካለ አባባሌን ይቀበለዋል፡፡አሁን ያለው ምንሊክ ሳልሳዊ የእነማን ስም እንደሆነም መለየት ይከብዳል፡፡ለኤልያስ ክፍሌም ሳይቀር በብእር ስምነት አያገለግልም ማለት አይቻልም፡፡ከዚህ ሰው ጋር ከዚህ በፊት ብዙ ስላልኩኝ ጊዜ ባላጠፋበት ይሻላል፡፡አሁን ላነሳ የፈለኩት ያኔ ከወር በፊት …ከ.ምንሊክ ሳልሳዊያን ተጠንቀቁ….የሚለው ማሳሰቢያዬን ደግሜ ለማስታወስ ግድ የሚል ነገር ስለተከሰተ ነው፡፡ የነገሩ ዋና ጉዳይ ከግንቦት7 ጋር የተያያዘና በተለይም የአንዳርጋቸው ጽጌን እገታ እንደሽፋን በመጠቀም መስራት ስለሚፈለገው ሴራ ነው፡፡ ወደዛ ከመግባቴ በፊት ስለሁለት ነገሮች ሀሳቤን ልግለጽ፡ስለ ኤርትራና ስለግንቦት7 ምን አይነት ሀሳብ እንዳለኝ፡፡

—– ኤርትራና ትግሉ—-

በዚህ ጉዳይ ላይ አንዳንዶቻችሁ አሉባልታ ካልመሰላችሁ በስተቀር አዲስአበባ ውስጥ ከህወአት አፍቃሪያን እንዳውም በከፍተኛ አመራር ላይ ካሉ የኤርትራ ትውልዶች ሳይቀር የሚባለውን ነገር…የክፉ ቀን ወዳጃችን..በሚል ርእስ አካፍያችዋለሁ፡፡እውን ኢሳያስ ወዳጃችን ነው? አይደለም ሊያስብል የሚያስችል ነገር የለም፡፡ የኢሳያስ ወዳጅነት በእኛ መታፈን፣ መሰደድ፣መጎሳቆል ፣በጥቂቶች መረገጥ የመሳሰሉ አሁን እያነሳናቸው ያሉ ሰብአዊና ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን በማየት ከዛ የመገላገል ወዳጅነት ላይሆን ይችላል፡፡ነጻ ላውጣቸው ልገላግላቸው የሚል ወዳጅነት መጠበቅ የለብንም፡፡ይህ የእኛ ስራ እንጂ የእሱ ስራ አይደለምና፡፡መጠየቅ ያለበት ለኢትዮጵያዊያን የትግል እድል ሰጥቷል ወይ ተብሎ ነው፡፡ለምን ሰጠ በምንስ መርህ ነውም ይባላል፡፡ሰጥቶ በመቀበል መርህ? ምን ሰጥተነው ምን እንዲሰጠን?ያንን መርህ የማያከብር ታጋይ ቢኖርስ ይታሰራል?ይገደላል? ይሰደዳል? በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ስለተነሱ የተለያዩ የተቃዋሚ ሀይሎች ብሎ ኢሳያስ ይህን ያህል መስዋእትነት የሚከፍለው ለምንድነው? የፈለከው ነገር ይደረግልህ ፣ከፈለክ ባድመ ያለቅድመ ሁኔታ ውሰድ፣ ወዳጅነታችን ብቻ እንደቀደመው ይሁን ሲባል እምቢ ለምን አለ? ኢትዮጵያ የነጻ ለማውጣት ወይንስ ኤርትራን ነጻ ለማውጣት? ጥያቄው መሆን ያለበት እንዲህ ነው፡፡

ከዚህ በፊት ያልኩትን አሁንም ደግሜ እናገራለሁ በኤርትራ መንግስት አስተሳሰብ ሀገሪቷ(ኤርትራ) አሁን ላለችበት ውድቀት የዳረጋት ህወአት ነው ብሎ ያምናል፣በሁለንተኛ ጥንካሬ የገዘፈ የህወአት አገዛዝ በምስራቅ አፍሪካ መኖር ለኤርትራ አደጋ ነው ብሎ ያምናል፣ከህወአት ጋር ባለው ቅድመታሪክ ብዙ ያልተፈታ ቂም አለ በህወአትና በኢሳያስ መሀል፡፡ስለዘህ የኤርትራን አፍንጫ ከኤርትራ ጠላት ነጻ ማድረግ ይፈልጋል፡፡ከህወአት፡፡የኢሳያስ ስራ ህወአትን መጣል ብቻ ሳይሆን ከህወአት በኋላ ስለሚመጣው ስርአትም ማሰብ ነው፡፡ህወአት ቢወድቅ ኢትዮጵያ ምን መምሰል አለባት ብሎ ያስባል፣በኤርትራ ውስጥ የሚታገሉ ሀይሎች በኢሳያስ መንግስት ላይ ለሚያነሱት ወቀሳና ጥርጣሬ ምንጩ ይሄ ነው፡፡ መቼም ኤርትራ ኢትዮጵያ እንድትተራመስ ይፈልጋል ብሎ ማሰብ ይከብዳል፣ከሰውዬው የትግል እድሜ አንጻር፡፡የተበታተነች ፣የተተራመሰች ኢትዮጵያ ለኤርትራ ህልውና እድገት ማረጋገጫ የሆናል ብሎ አያምንም፡፡ለዚህም ይሰራል አይባልም፡፡ችግሩ ሌላ ነው፡፡አንድ በተቃዋሚው ውስጥ ያሉ ሀይሎች አሁንም ለኤርትራ ነጻነት እውቅና ለመስጠት ያንገራግራሉ፣የድሮ የኢትዮጵያ ካርታ ያለበት ቲሸርት ለብሰው ኢሳያስን አታግለን እንታገላለን እያሉ ይጠይቃሉ፡፡እንደዚህ አይነት ጥያቄ አለ እንዴ? ወያኔ አጣልቶን ነው እንጂ እኛ እኮ አንድ ህዝብ ነን ብሎ ከኢሳያስ ጋር መነጋገር በፍጹም ከጥፋት ነጻ ሊያደርግ አይችልም፡፡አንድ ህዝብ ለመሆን ግዴታ በአንድ ሀገር መሆን የለበትም፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ኤርትራ ከእኛ ምንድን ነው የሚፈልገው ብለው አያስቡም፣ለእነሱ ስለሚደረግላቸው ነገር ብቻ ነው የሚያስቡት፡፡እንደወፍ መሆን ካማራቸው በቃ ወፍ እንሁን ልቀቅን አይነት ነገር ይላሉ፡፡እውነት ለመናገር ኤርትራ ከቁጥጥሯ ውጪ የሆኑ፣በራሳቸው ፈቃድ የሚወጡና የሚገቡ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሀይሎችን አትፈልግም፡፡ለምሳሌ ብንወስድ የኢትዮጵያ መንግስት ካንዱ ኤርትራ ውስጥ ካለ አማጺ ጋር መደራደር እፈልጋለሁ ቢል ወሳኙ የኤርትራ መንግስት እንጂ፣አማጺው ቡድን አይደለም፡፡አሁን ባለው ሁኔታ በኤርትራ ውስጥ ያሉ የተቃዋሚ ሀይሎች ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር እንዲዋጉ እንጂ እንዲደራደሩ አይፈለግም፡፡ስለዚህ እንዳልኩሽ ትሆኛለሽ …የሚለው ነገር እዛ እስካሉ ድረስ ማሰብ ግድ ነው፡፡እንዲህማ ካልሆነ ለምሳሌ ትህዴን (የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት) ከመንግስት ጋር ተደራድሬ ችግሬን እፈታለሁ ቢል ከባድ ነገር ነው፡፡ኤርትራ እሺ አትልም፡፡ስለዘህ ኤርትራ ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎች ልክ እንደ አባባሉ…ዶሮ አስረዝመው ሲያስሯት የፈቷት ይመስላታል…እንደሚባለው ነው፣ከኢሳያስ መመሪያ መውጣት አይቻልም፡፡ይሄ እውነት ነው፡፡እንዲህ በማድረጓም ተሳስታለች ማለት አይቻልም፣ እዋጋለሁ እድል ይሰጠኝ ብሎ ሲያበቃ በመሀል ደግሞ የድርድር ባስ መጥቷልና መሄድ መብታችን ነው በማለት ኤርትራ በአሁን ሰአት በኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ምክንያት እየደረሰባት ያለውን የበደል ሂሳብ ማወራረድ አይቻልም፡፡የኤርትራ መንግስት ህወአት እንዲለወጥ ይፈልጋል፣ተቃዋሚዎችም እንደዛ ማሰብ አለባቸው፣የኤርትራ መንግስት ህወአት ድርድር አይገባውም ብሎ ያምናል፣ተቃዋሚውም ማመን አለበት፡፡ለመዋጋት ነው የመጣኸው ተዋጋ ነው፡፡ከዚህ ውጪ ያሉ ድርጊቶች ወደ አለመተማመን የሚያደርሱ ነገሮችን ይወልዳሉ፡፡ በእርግጥ ይህ አሰራር ጥሩ ነው አይባልም ከኤርትራ ፍላጎት አንጻር ካልታየ በስተቀር፣የኤርትራ መንግስት እዛ በሀገሩ ለሚታገሉ ሀይሎች እንደፈለጋችሁ ብሎ ነጻነት ቢሰጣቸው በኢትዮጵያ እያየን ካለው የተለያየ የፖለቲካ ድርጅቶች አሰራር ውጤት ያለው ስራ ለመስራት ችግር ፈጣሪ ቢሆንም እንደ ግንቦት7 ላለ በሁሉ ነገሩ አልሞና አስቦ ለሚራመድ ድርጅት ግን በኤርትራ ውስጥ በነጻነት የመስራትና የማሰብ መብቱ ያለገደብ ሊፈቀድለት ይገባል፡፡ምክንያቱም ኤርትራ እነዚህ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ችግር አለባቸው እዚህ ጋ ያዝ ካላረግናቸው ለስራው አይመጥኑም እንደሚባለው አይደለም ግንቦት 7፡፡ለምስራቅ አፍሪካ ከህወአት በላይ አደጋ የለም መውደቅ አለበት ብሎ የሚሰራ ነው፡፡ኤርትራ ለዚህ አስተሳሰብ ገዢ መሬት ብቻ ሳይሆን ሙሉ የአሰራርና የትግል ነጸነት መስጠት ካልቻለች ሰዎች በሆነ ባልሆነ ቢጠረጥሯትም አይፈረድባቸውም፡፡በግሌ ግን ሙሉ ተባባሪ መሆኗን ነው የምረዳው፡፡በሂደትም ብዙ የሀሜት ቀዳዳዎች እንደሚደፈኑ ነው የምንጠብቀው፡፡

—–ግንቦት7 እና ትግሉ—–

ግንቦት7 ገና ከመመስረቱ በፊት፣ዶ/ርብርሀኑ ነጋ ሀገር ቤት እያለ አንድ ነገር እናይ ነበር፡፡ብርሀነ መዋ በየቦታው እየሄደ ንግግር ሲያደርግ የሆነ ጠመንጃ ነገር እየታጠቀ ፡፡ከሀገር ቤት ውጪ ያለው ቅንጅት መሰንጠቅ ውስጥ የገባው ያኔ አካባቢ ነው፡፡ሻለቃ ማናቸው የሚባሉት ሰው የራሳቸው ቡድን መሰረቱ የእነ ብርሀነ መዋም እንዲሁ ሌላ፡፡ይህ የእነ ብርሀነ መዋ ቡድን በሀገርቤቱ ነገር ተስፋ የቆረጠና ካሁን በኋላ በቃ በመሳሪያ እንጂ በካርድ ትግል የለም ብሎ የተነሳሳው መስሎ ነበር የሚታየው፡፡አሁን አሁን ያ ሰብስብ የአነ ብርሀነ መዋ ስብስብ የእነአንዳርጋቸው ቡድን ነበር ብዬ እንዳስብ አደረገኝ፡፡ ብርሀኑ ነጋ ከእስር እንደተፈታ በቁምጣ ሜክሲኮ አካባቢ እየሄደ የህዝቡን ስሜት ሲፈትሽ፣ነገሮችን ሲቃኝ አንድ ቀን ከሌሎች ልጆች ጋር ሆነን አይተነው ፣አይ አሁን የዚች ሀገር ነገር ያዋጣኛል ወይንስ አያዋጣኝም ብሎ የሆነ ውሳኔ ሊወስን ነው ብለን ነበር፡፡መጽሀፉን አንብበን እንደተረዳነው አንድም የትጥቅ ትግል የሚያበረታታ ነገር አላገኘንም፡፡በፍቅር እናሸንፋቸዋለን ብቻ ነው የሚለው፡፡ከሀገር ቤት በወጣ በስንተኛ ጊዜው ሀሳቡን ለወጠ፡፡በመጡበት መንገድ እናነጋግራቸዋለን አለ፡፡የዚህ ሀሳብ አመንጪ አንዳርጋቸው ጽጌ ነው ተብሎ በብዙዎች ይታሰባል፡፡ቢሆንም ብርሀኑ ነጋ እንዴት አመነው ነው ጥያቄው፡፡ስላመነበት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡አሁንም እያለ ነው፡፡አሁንም ያምንበታል፡፡ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ለምን አመነ? እንዴት ሊሆን ቻለ? ይህ ጥያቄ ስለግንቦት7 ታሪክ ሳይሆን አሁን ስላለው የግንቦት7 አቋም ነው፡፡እውነት ለመናገር ግንቦት7 ለመጀመሪያ ጊዜ የህወአትን እድሜ ለማሳጠር ወጥመዱን ያጠመደው ከኤርትራ ሆኖ ሳይሆን እዚሁ አገር ቤት ሆኖ ነበር፡፡በጣም ሰርቶ ነበር፡፡የውጪ ጠላት ባያስቸግረው ኖሮ ያኔ የታሰበው ነገር ሆኖ ቢሆን ኖሮ ህወአት ለ2002 ምርጫ አይደርስም ነበር፡፡ያንን ወጥመድ ያከሸፈው በብዙዎች እምነት ሲአይኤ ነው፡፡ወደዝርዝሩ አልገባም፡፡ግን ግንቦት7 ገና ሲመሰረት ኤርትራን ብቻ አስቦ ነው ወይ ቢባል መልሱ ወደ አይደለም ያደላል፡፡አሁንም ድረስ ብዙዎች እንደሚሉት ግንቦት 7 ወደ ኤርትራ የሄደው ሲአይኤ የሀገርቤቱን ስራውን ገና ከጅምሩ ስላፈረሰበት ነው እየተባለ ያለው፡፡ወደ ኤርትራ እንዴት ሊሄድ ቻለ፡፡ አሁንም ብዙዎች እንደሚሉት ለሚመጣው ሁሉ ሀላፊነቱን እኔ እወስዳለሁ ብሎ በፊት ውራሪነት ነገሩን የመራው አንድአርጋቸው ጽጌ ነው በብዙዎች አስተሳሰብ፡፡ በወቅቱ ኢሳያስ አፈወርቂ የእነስዬ አብርሀ ፎቶ ያለበት በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ባቆጠቆጠች አንዲት መጽሄት አማካኝነት ….ኑ ሀገራችሁን ነጻ አውጡ፣ ኤርትራም ትተባበራችዋለች…ብሎ ነበር፡፡ግንቦት 7 ያሀገር ቤት ሁሉን አቀፍ ያለው ትግሉን ይዞ ወደ ኤርታራ ለመሄድ ቆረጠ፡፡ሄደ፡፡ ታዲያ ምን አደረገ?

በአሁኑ ሰአት በኤርትራ ውስጥ ለግንቦት7 አላማ ተባባሪ የሆኑ በጣም ብዙ እድሎች አሉ፣ተፈጠትረዋል፡፡ እዚህም ሀገር ቤት ውስጥ እጅግ በጣም ብዙ እድሎች አሉ፡፡እንደ ቀጠናም ከወሰድነው ምስራቅ አፍሪካ ለግንቦት7 አላማ መደላደል የሚፈጥሩ ብዙ እድሎች አሉ፡፡የሆነው ነገር ልናገር፡፡ግንቦት7 የምር የሰራው ነገር ቢኖር በአካባቢው ፣በሁሉም አቅጣጫ በዚህ መንግስት ላይ ያኮረፉና የታጠቁ ሀይሎች የጋራ ጠላታችን ህወአት/ኢህአዴግ ነው መጀመሪያ መውደቅ ያለበት እሱ ነው ብለው ማመን የሚችሉበት ሁኔታ ላይ ደርሰዋል፡፡ማመን ብቻ ሳይሆን ያለትብብርም ማሸነፍ እንደማይችሉ አውቀዋል፡፡ማወቅ ብቻ ሳይሆን ወደ ትብብርም ጉዞ ጀምረዋል፡፡በጣም አስደሳቹ ነገር ደግሞ ይህ ትብብር የኤርትራ መንግስትም ፍላጎት መሆኑ ነው፡፡ከብዙ ነገሮች አንጻር ቢተነተን የእነዚህ ሀይሎች ትብብር በኤርትራ መንግስት ላይ ስጋት ፈጣሪ፣ደግሞ አዙረው ቢተኩሱብኝስ የሚያስብልም አይደለም፡፡

ለዚህ ማሳያ ምሳሌ ብንወስድ አንድ ግንቦት7 ከሌሎች ጋር እያደረገ ያለው የውህደትና የትብብር እንቅስቃሴ መጥቀስ ይቻላል፡ትብብር አንፈልግም የሚሉ ሀይሎች ደግሞ ቦታ የላችሁም ኤርትራን ልቀቁ መባላቸው ደግሞ በነኮለ.አለሁበል አማረ ላይ ከደረሰው ነገር መረዳት ይቻላል፡፡ሌላው አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ እንዳሉት ከኤርትራ እስከ ሱዳን ብሎ እስከ ሶማሊያ አደገኛ ኔትወርክ ተዘርግቷል ያነገር መበጣጠስ አለበት ማለታቸውን እናስታውሳለን፡፡ ያም ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት የደቡብ ሱዳን ሀይሎችን በማስፈራራት ጭምር ችግር ሊፈታ ሞክሯል፡ከሰሜን ሱዳንም ጋር በድንበር አካባቢ አብሮ ለመስራት ስምምነት ተደርጓል፡፡ ትልቁ ነገር በዚህ ሰሞን በአልሻባብ ላይ የደረሰው የአሜሪካ የአውሮፕላን ድብደባ ነው፡፡አልሻባብ ለምን ተደበደበ? አልሻባብ በምስራቅ አፍሪካ የአሜሪካን ጥቅም የሚነካ ነገር ምን አደረገ? በሶማሊያ ላለው የአፍሪካ ህብረት ትብብሯን ለማሳየት ነው እንዳይባል ተባበሪን ብሎ ያቀረበላት የለም፡፡በኬኒያ በተለያየ ጊዜ የተፈጸሙ የሽብር ጥቃቶች ምክንያት ናቸው እንዳንል ጊዜውን ያገናዘበ አይደለም፡፡ቦከሀራም ከ200 በላይ ልጅገረዶችን አፍኖ ወስዶ የወሲብ ባሪያ ሲያደርግ ፣ናይጄሪያ የድረሺልኝ ጥሪ ስታደርግላት አሜሪካ አልደረሰችም፣ ልጆቹ አሁንም ባሪያዎች ናቸው፡፡ኢስላሚክ እስቴት የተባለው በኢራቅና በሶሪያ መንግስት ለመመስረት እየተጋ ያለው እስላማዊ ሀይል በአደባባይ ዜጎችሽን አረድኩልሽ ቢላትም ኢራን እንዳለችው የአሜሪካ ምልሽ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ታዲያ አልሻባብ ምን አሜሪካንን የሚያስፈራራ፣ የሚያሰጋ ነገር ስላለ ነው የተደበደበው?

መልሱ ቀላል ነው፡፡በኢትዮጵያ ጥያቄ ነው፡፡ አቶ ሀይለማሪያም እንዳሉት መረቡ እስከ ሰማሊያ የተዘረጋ ከሆነሶማሊያ በሚለው ቃል ውስጥ ያለው አልሻባብ ነው፡፡ በመሆኑም በምስራቅ አፍሪካ በአሁኑ ሰአት ለአሜሪካ ትልቁ ጥቅሟ ከቻለች የኢትዮጵያን መንግስት ማዳን ነው፡፡ኢትዮጵያ ማለት ለአሜሪካ አንድ በተላላኪነት ወታደር በማሰማራት ሌሎች የአሜሪካንን ጥቅም ለማስከበር የምትዋጋ ናት፣ሩሲያ በኤርትራ ልታቋቁመው ያሰበችውን የጦር ሰፈር እንዳይሳካ እንድታደርግላት ትፈልጋለች፡፡በተለይ ብሪክስ የእነቻይና የትብብር ማህበር ስራ ከጀመረ ለኤርትራ ማምለጫ ነው፣ያ ደግሞ ለአሜሪካ አካባቢያዊ ስጋት ይፈጥርባታል፡፡የአባይ ግድብ ግንባታ የእስራኤልን ህልውና ታሳቢ ያደረገ እንዲሆን ይፈለጋል፡፡ብዙ ነገሮች መጥቀስ ይቻላል፡፡ስለዘህ ህወአት ለአሜሪካ ከፍተኛ የጥቅም አጋር ነው፡፡በአልሻባብ ላይ የተደረገው ድብደባም ይህንን ጥቅም፣ህወአትን፣ ከስጋት የመታደግ ተልእኮ ያለው ነው፡፡ነገሩ እውነት መሆኑን የምትረዱት ደግሞ በቅርቡ በተደረገው የቦምብ ድብደባ በተገደለው የአልሻባብ መሪ ምትክ የተመረጠው ኢትዮጵያዊ መሆኑ ነው፡፡ኔቶርኩን መበጠስ አልተቻለም ማለት ነው እንደዚህ አስልቶ የወጣውን ነገር መልሶ የሚያስገባ ሀይል ካለ፡፡ታዲያ አልሻባብ ከግንቦት7 ጋር ምን አገኛኘው ትሉ ይሆናል፡፡ መቼም ጦርነት ቢነሳ ህወአትን በአንድ ብቻ ፣በስተሰሜን ብቻ ፣ለመግጠም የሚያስብ የለም፡፡ከህውአትጋር በትጥቅ ትግል መፋለም እንደአማራጭ ከተወሰደ የአልሻባብ ምሽግ አንድ ግንባር ነው፡፡አልሻባብ አንድ አጋር ነው፡፡

እኔ በግሌ አልሻባብ የሚከተለውን አይዲዮሎጂ አልደግፍም፡፡ቢሆንም የማይጠቅመኝን ነገሩ ላጥ አድርጌ እጥልና በሚሆነኝ ነገሩ እጠቀማለሁ፡፡ አልሻባብ የታጠቀ ሀይል ነው ፡፡በአይዲዮሎጂው ባልስማማም ህወአት/ኢህአዴግን አብረን እንውጋ ስለው እሺ ካለኝ የጋራ ጠላታችንን አብረን በመውጋት አላማችን ግን አንድ እንሆናለን፡፡አሁንም በትክክል ሊታሰብ የሚገባው ነገር በምስራቅ አፍሪካ በሽታ የሆነው ህወአት የሚያራምደው አስተሳሰብ ነው፡፡እኔ በግሌ ግንቦት7 አልሻባብን የልብ ወዳጅ ባያደርገውም የትግል ወዳጅ ቢያደርገው አይከፋኝም፡፡ሩጫው ለማሸነፍ ከሆነ ከአራጮቹ አንዱ አልሻባብ መሆን እንዳለበት አምናለሁ፡፡ዋናው ጥያቄ በየትኛውም መንገድ ግን በአሯሯጮቼ እንዳልቀደም ምን ላድርግ ብሎ ማሰብ ነው፡፡አሁን ግንቦት7 አካባቢ እየሆነ ያለውም ይህ ይመስለኛል፡፡ነውም፡፡በዚህም ሯጩም አሯሯጩም የሚጎዳ አይመስለኝም፡፡ለማነኛውም ግንቦት 7 ወደ ኤርትራ በመሄዱ ብዙ የትግል እድሎችን በመፍጠር በህወአት ላይ ከውስጥም ሆነ ከውጪ የሚታይ የሚጨበጥ ከፍተኛ ውጥረትና አለመረጋጋትን ፈጥሯል፣ከዛም አልፎ ከአቅሙ በላይ ስለሆነም የውጪ መንግስታት ጣልቃ ገብነት ሁሉ ያስተናገደበት ሁኔታ አለ፡፡የአንዳርጋቸው በምእራባዊያንና በየመን ትብብር አለም አቀፍ ህግን በተላለፈ መልኩ ተላልፎ መሰጠቱ ስርአቱ ላይ ያፈጠጡት ስጋቶች ከበድ ያሉና የሌሎችም እገዛ የሚፈልጉ መሆናቸውን የሚያመለክቱ ናቸው፡፡ህወአት/ኢህአዴግ በኤርትራ ጉዳይ ላይ የሚከተለው ፖሊሲ እንዲለውጥና የጦርነት አማራጭ እንዲይዝ ያደረገው ግንቦት7 የፈጠረው የትግልእድል ከበድ ያለ መሆኑን ያሳያል፡፡ በቅርቡ በአልሻባብ ላይ የተደረገው የአሜሪካ ድብደባ ዋና ስሌትና ኢላማው ህወአትን የመታደግ፣የመርዳት ተልእኮ ያለውና እነግንቦት 7 ያጠመዱትን ወጥመድ ከማክሸፍ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ከዚህ ጋር በተያያዘ ብዙ ማለት ይቻላል፡፡

—–የኤልያስ ክፍሌ የሰሞኑ ተረትተረት መነሻዎችና ግባቸው——

ታዲያ ይህ ሁሉ እስካሁን የተነሳው ነገር ከኤልያስ ክፍሌ ወይም ከምንሊክ ሳልሳዊ ጋር ምን አገኛኘው ይባል ይሆናል፡፡ ይገናኛል፡፡የሚገኛቸው ኤልያስ ክፍሌ ሰዎች ዋጋ እየከፈሉለት ባለው ትግል ላይ ድንጋይ መወርወሩ ነው፡፡ኤልያስ አንዳርጋቸው ጽጌን አሳልፎ የሰጠው የኤርትራ መንግስት ነው የሚለው አባባል በጣም የትግል ምቀኝነት የሞላበት ነው፡፡የሚገርመው ነገር ግንቦት7 የአንዳርጋቸው ጽጌ መታገት በተናገረ በሳምንቱ ምንሊክ ሳልሳዊ ይህንኑ ሀሳብ ጽፎት ነበር፡፡ አሁን ፌስቡክ ገጹ ላይ ፈልጌ ስላላገኘሁት ነው፡፡…..አንዳርጋቸውን ለወያኔዎች አሳልፎ የሰጠው የኤርትራ መንግስት ነው አይደለሁም የሚል ከሆነ በስራ ያሳየን…የሚል ነገር ነበር ጽፎ የለጠፈው፡፡ሄኖክ የሺጥላ የሚባል ኢሳት ላይ የማየው ገጣሚ ነው አንድ በኖርዌ ነዋሪ ከሆነ ሰው በፌስቡክ ላይ የተጻጻፍኩት ነው ብሎ እንዳጋራን አሁን ኤልያስ ክፍሌ ተመራምሬ አገኘሁት የሚለው ሀሳብ አይነት ነው፡፡እንዳውም ያኔ ሄኖክ አንድ የወያኔ ሰላይ እንዳለኝ ብሎ ነበር የለጠፈው፡፡የሱንም ብፈልገው አጣሁት፡፡እሱ ካገኘው ጀባ ቢለን እንደ ኤልያስ ያሉትን ለመታዘብ ያመቸናል፡፡በነገራችን ላይ ሄኖክን እንደዛ ያለው ሰውዬ የሰማያዊ ፓርቲ አርማ ነው ፕሮፋይል ስእሉ፡፡ስሙን መጥቀስ አያስፈልግም እንጂ አሁንም ድረስ አውቀዋለሁ፡፡በአሉ ግርማን ማን ገደለው በሚለው ክርክር ሰውጥ ሀሳቡን ይሰጥ ነበር፡በረጃጅም ጽሁፍ፡፡አንድ ቀን ኖርዌ ውስጥ ያለው የግንቦት 7 አመራር እዛ ጥገኝነት ለሚጠይቁ ኢትዮጵያዊያን አልተባበርም አለ፡፡ ድሮስ ከነዘህ ምን ይጠበቃል መሪያቸውን አሳስረው ገንዘብ ብቻ የሚሰበስቡ ብሎ ጽሁፍ ለጥፎ ነበር፡፡ አባባሉ ስላደደኝ ግንቦት 7 ክፍት ጭንቅላት ያለው እንጂ ክፍት አፍ አይፈልግም ከማውራትህ በፊት አስብ ብዬ አሰጠያየት ሳጥኑ ላይ ጻፍኩለት፡፡ወዲያው ተናዶ ብሎክ አደረገኝ፡፡እቺን ዛሬ ኤሌያስ ያላት ነገር ከሄኖክ ጋር ሲነጋር ቁጭ ነው ያደረጋት፡፡ ምንሊክ ሳልሳዊም እንደዚህ አይነት ሀሳብ ያለው ጽሁፍ ለጥፎ ነበር፡፡ በጣም የሚገርመው ግን እነምንሊክ ሳልሳዊም እንደዛ ብለው በኤርትራ መንግስት ላይ ጥርጣሬ በበዛበት ወቅት ..ኤርትራ አየር ክልሏን አቋርጠው ወደ የመን የሚበሩ አውሮፕላኖችን ከለከለች….የሚባል ወሬ በብዛት ተለቀቀ፡፡ ያኔ ኤልያስ ክፍል ደግሞ ምን ይላል ….ኢሳያስ የእኔ ፕሬዝዳንት ቢሆን ተመኘሁ ብሎ ጻፈ፡፡ይህ ጽሁፍ መረጃ .ኮም፣ኢትዪጵያን ኒውስፎረም በሚባሉት ገጾቹ ላይ ለቆት ነበር፡፡ልል የፈለኩት አሁን እነ ምንሊክ ሳልሳዊና ኤልያስ ክፍሌ ያሏት ነገር ስትባል የነበረች ናት፡፡ ከወር በፊት ምንሊክ ሳልሳዊን በተቃወምኩበት ጽሁፍ …..የከዱ ሰዎች….የሚል ነገር በማስገባት ግንቦት 7ን ሊያሳጣ በሚችል መልኩ ወሬ ማቅረቡን አመልክቻለሁ፡፡እነዛ ሰዎች አንዳርጋቸው ጽጌን መደብደባቸውን ነግሮናል፡፡ ዛሬም ኤልያስ ልዩ ዘገባ ብሎ ባቀረበው ጽሁፍ ውስጥ ..ኤርትራ በረሀ ላይ አንዳርጋቸው ጽጌ በገዛ ሰልጣኞቹ መደብደቡን ነግሮናል፡፡በዚህ ሰሞን ፕሮፌሰር ሙሴ ተገኘ የተባለ ሰው ያወራው የነበረ ሀሳብን በጽሁፍ መልክ በማቅረብ እገሌ የሚባል ነበረ፣ እንዲህ ሆነ፣ እገሌ የሚባል ነበረ እንዲያ ሆነ ብሎ መናገር የሁለት ወር የሚስጥር ፍለፈላ ሊያደርገው አይችልም፡፡

ሀሳቡ ከመጀመሪያም እንደተከታተልኩት ልቃወመውም እንደሞከርኩት የምንሊክ ሳልሳዊ ነው፡፡ኤልያስ ሀላፊነት ወስዶ የእኔ ነው ሊል የቻለው ምንሊክ ሳልሳዊ የሚለው ስም በብዙዎች ዘንድ ውሸት ፈብራኪ ተደርጎ እየተወሰደ ስለሆነ ነው፡፡ገና ከመነሻ እንዳልኩት ምንሊክ ሳልሳዊ አንድ ከዚህ በፊት የኢህአፓ የወጣቶች ክንፍ ነኝ በሚል በማህበራዊ ገጽ ላይ ሲንቀሳቀስ የነበረ ሰው ነው፡፡ኤልያስ ክፍሌ እራሱ ይህንን ስም በብእር ስምነት እየተገለገለበት ፣የፈጠራ ጽሁፎቹን ከሀገር ቤት የተገኙ በማስመሰል በምንሊክ ሳልሳዊ ስም ይለቃል፡፡በተለይ መረጃ.ኮም ላይ፡፡የምንሊክ ሳልሳዊ የኤልያስ ክፍሌ ብቻ ሳይሆን ለእነመረጃ.ኮም በዘጋቢነት የሚሰሩ ሰዎችም የሚጠቀሙበት ነው፡፡ምንሊክ ሳልሳዊዎች ስንት ናቸው ለማለት ኤልያስ ክፍሌ ዘጋቢዎች ስንት ናቸው ማለት ይሻላል፡፡የኤልያስ ክፍሌ ዘጋቢዎች አንዳንዴ እሱ እራሱን ጨምሮ የሚጠሩት ምንሊክ ሳልሳዊ ተብለው ነው፡፡ከምንሊክ ሳልሳዊዎቹ አንዱ አዲስ አበባ የሚገኝ ነው፣ብዙም ምስጢር የማያውቅ የደህንነት ዘመድ ይኖረው ይሆናል እንጂ እሱ ግን ደህንነት አይመስልም፡፡ይህንን ነገር ከአጻጻፉ መረዳት ይቻላል ወይ ማታ ማታ ነው የሚጽፈውና የሚለጥፈው አልያ ደግሞ ጧት ላይ ነው፣ወይ ከስራ ውሎ ከመጣ አልያም ስራ ላይ ካደረ ሰው እየጠየቀ ይመስላል፡፡ ካላመናችሁኝ ካሁን በኋላ ልብ ብላችሁ ተከታተሉት፡፡ይህንን አንብቦ ደግሞ እንዳይለውጥ፡፡ለማነኛውም ሶስት ሰዎች ለግንቦት 7በጣም የተመሳሰለ አስተሳብ አላቸው፡ ፕሮፌሰር ሙሴ ተገኝ፣ ኤልያስ ክፍሌ፣ምንሊክ ሳልሳዊ(ዎች)፡፡ የታወቀ ነው ኤልያስ ክፍሌ የቀድሞ የሙሴ ተገኝ ጓደኛ ነው እስከ ኤርትራ የሄደው የያኔዎቹ የእሱን ወታደሮች ለመርዳት ነበር፡፡አሁን ኤርትራ ባለው አርበኞች ግንባር ላይ በግልጽ ባያነሳም ልክ እንደ ሙሴ ተገኝ ኤልያስም ክፍሌም ስንት ወጪ አውጥቼበት እንዳልነበረ ዛሬ እንዴት ከግንቦት7 ጋር ሲዋሀዱ ዝም ብዬ አያለሁ የሚል የቅናት መንፈስ አለበት፡፡መቼም እቺ ሁለት ወር ፈጀች የተባለች ልዮ ምስጢር ቁጭ ብሎ ለመጻፍ አንድ ሰአትም አትፈጅም፡፡ፎቶ የለው፣ሌላ ዶክመንት የለው ምን የለው ስም ብቻ ሪፖርት የሚባል ትልቅ ስም አሸክሞ ለማውጣት ጊዜ አይበላም፡፡ማንም ሰው ዞርዞር ብሎ ማየት ይችላል ኤልያስ ክፍሌም ሆነ ምንሊክ ሳልሳዊ አንድም ቦታ ላይ ስለነግንቦት7 የእንዋሀዳለን ስምምነት አልዘገቡም፡፡ከዚህ መረዳት የሚቻለው በነገሩ ምቀኝነት እንዳደረባቸው ነው፡፡ በተለይ ኤልያስ ይህንን ጊዜ የፈለገው በግንቦት 7 ስኬታማ ስብሰባም ምቀኝነት ስላደረበት ነው፡፡

የኤርትራ መንግስት አሳልፎ አልሰጠውም ነው የምትለው ትሉኝ ይሆናል፡፡እኔ ለኤርትራ መንግስት ጥብቅና ለመቆም ባልችልም ኤልያስ ክፍሌ ያቀረባቸው ነገሮች፣ ያቀረበበት ጊዜ፣ሲታይ በግንቦት7 ላይ ኪሳራ የማስከተል ስሌት በማሰብ የተደረገ እንጂ ለአንዳርጋቸው ጽጌ ቀናኢ ሆኖ አይመስልም፡፡ እውነት እንነጋገር ከተባለ በኤርትራ መንግስት ስሌት ከህውአት ጋር ሊደረግ ባለው በማይቀረው ጦርነት የአንዳርጋቸው ጽጌ ሚና አሁን ባለው ሁኔታ በእስር ላይ ቢሆን ይሻላል ብሎ የእሱ መኖር ጉዳት አለው ካለ እኛ እንዲያደርግ ባንፈቅድለትም የትግሉ ሂደት ከፈቀደ አይደለም መታሰር መጥይትም ተደብድቦ መሞት እንዳለ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ግን አንዳርጋቸው ጽጌ አሁን ባለበት ደረጃ በመሆኑ የኤርትራ መንግስት ያገኘው የትግል ጥቅም የሚያሳይ ትንታኔ የለም፡፡ የኤርትራና የአንዳርጋቸው ግንኙነት ምክንያቱ ትግል ነው፡፡በትግል ግንኙነታቸው መካከል የገባ ነፋስ በግልጽ የሚያሳዩ መረጃዎች የሉም፣ከአንዳርጋቸው ጽጌ ጋር የተያዙ አንዳንድ መረጃዎችም ለኤርትራ መንግሰት በኪሳራ እንጂ በትርፍ ሊወራረዱ አይችሉም፡፡ ታዲያ ኤልያስ ክፍሌ ኤርትራ አንዳርጋቸው ጽጌን አሳልፎ ሰጠ ሲል ምን ለማለት ነው? ስለዘህ ኤርትራ ውስጥ የሉት የትጥቅ ትግል ለማድረግ የተደራጁ ሀይሎች በቃን ብለው ፈርተው ይውጡ ነው? የግንቦት7 ደጋፊዎች ድርጅቱ ለትግል እያለ የሚሰበስበው ገንዘብ የማጭበርበር ስራ ነው አቁሙ አትስጡ እያለ ነው? አንዳርጋቸው በኤርትራ ተላልፎ ነው የተሰጠው ሲባል ምን ማለት ነው? ወይንስ ኤርትራ አውቃ ነው ወያኔ እንዲወድቅ አትፈልግም ማለት ነው? ምን ማለት ነው?በቃ ምቀኝነት ነው፡፡ኤልያስ ክፍሌ በግንቦት 7 ስኬትና እንቅስቃሴ ስለቀና ነው፡፡

እስካሁን በቀረበው ሀሳብ መሰረት የእነ ኤልያስ ክፍሌ በአንዳርጋቸው ጽጌ መታፈን ዙሪያ የተሰጠው ዘገባ ከእውነት የራቀ ነው፡

1. በዘገባው ውስጥ የተካተቱት ፍሬ ሀሳቦች አንዳርጋቸው ጽጌን አሁን ላለበት ደረጃ ሊያደርሱት የሚችሉ አማራጮችን ሁሉ የዳሰሰ አይደልም፡፡እንዳውም ዋናዎቹን የጥርጣሪ ምንጮችን ገሸሽ ያደረገ ነው፡፡የእንግሊዝና የሲአይኤ ሚና አልተገለጸም፡፡እስካሁንም እነዚህ ሀይሎች እያሳዩ ያሉት ነገር ከመጀመሪያውም ከህውአትና ከየመን አድራጎት ጋር አንዳርጋቸው ጽጌን አሳልፎ በመስጠት ተግባር ተባባሪ አለመሆናቸውን የሚያሳይ ሀሳብ አላቀረበም፡፡

2. የኤልያስ ቅድመታሪክ ሲታይ በብዛት ያልተረጋገጡ መረጃዎች የማቅረብ ሁኔታ አለበት፡፡በብዛት የሎ ጆርናሊዝም ወይም ሴንሴሽናል ጆርናሊዝም የሚባለው ብዙ ለአሉባልታና ላልተረጋገጠ መረጃ የተጋለጠ አቀራረብ የሚያዘወትር ሰው ነው፡፡

3. የኤልያስ ዘገባዎች የሌሎች መጠቀሚያም ናቸው፡፡የህወአትና እስካሁንም በሸር እያሰቡ ላሉ ምቀኛ ኢህአፓዎች፡፡ለዚህ ዋናው ምክንያት ደግሞ ምንሊክ ሰልሳዊ ነው፡፡ይህ ስም ከአንድ ሰው በላይ የሚጠቀምበት መጠሪያ ቢሆንም በዚህ ስም ከሚጠሩት ውስጥ አንዱ ግን አንድ የግንቦት7 ገናናነት በሰፋ ቁጥር የገቢ ምንጫችን ይጠፋል ብለው የሚያስቡ በአውሮፓና አሜሪካ ያሉ በገቢ ማሰባሰብ የሚተዳደሩ የትግል ምቀኞችን ወክሎ ያለ ሰው ነው፡፡ይህ ሰው ህወአት መውደቅ እንዳለበት የሚያትቱ የተጭበረበሩ ትግል ቀስቃሽ ጽሁፎችን ቢያቀርብም የግንቦት 7 እጣ ፈንታ በተመለከተ ከኢህአዴግ/ህወአት ጋር የሚመሳሰል አቋም ያለው ነው፡፡በኢቲቪ ዶክመንተሪና በተለያየ መንገድ የቀረቡ ለግንቦት 7 ውድቀት የሚመኙና ደጋፊዎችና አባላትን ሊያሸሹ የሚችሉ በስርአቱ የተዘጋጁ የተሳሳቱ መረጃዎችን የተቃዋሚ ጭምብል በመልበስ የሚያሰራጭ ነው፡፡ እንደዚህ አይነት ዘገባዎችም በተለያየ ጊዜ ኤልያስ ክፍሌ በሚያስተዳድራቸው ዌብሳይቶች ላይ ተጋርተው ታይተዋል፡፡ስለዚህ እንዲህ አይነት አቋም ከሚያራምድ ሰው ስለግንቦት 7 ጥሩ ምኞት አይጠበቅም፡፡

4. የዘገባው ርእስ ..አንዳርጋቸውን የከዳው ማን ነው..የሚል ቢሆንም ወደዝርዝር ሲገባ ያሉት ሀሳቦች ግን ከተባለው ነገር ጋር አብረው የማይሄዱ ሌላ ድብቅ አጀንዳ እንዳለ የሚያሳብቁ ናቸው፡፡ምሳሌ ለመጥቀስ ያህል….አንዳርጋቸው ጽጌ በኤርትራ በረሀ በገዛ ሰልጣኞቹ ስለመደብደቡ ..የሰፈረው ነገር፡፡ይህ አባባል ከዚህም በፊት አንዳርጋቸው ጽጌ ከተያዘ በኋላ ከድተው በመጡ አሳሩን እየበላ ነው፣ያኔ የነገርከን ነገር ምድንነው አውጣ እየተባለ…ተብሎ የተጻፈ የምንሊክ ሳልሳዊ ጽሁፍን ያስታውሳል፡፡ይህ አባባል ኤርትራ አሳልፋ ሰጠችው ከሚለው ነገር ጋር ግንኙነት የለውም እግረ መንገድ የግንቦት 7 አባላትና ደጋፊዎችን ለማስነከስና ህዝቡ በግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል ላይ የጥርጣሬ መንፈስ እንዲኖረውና ለዛም ብሎ ገንዘብ እንዳያዋጣ የተሸረበ ምቀኝነት ነው፡፡ሌላው ከዚህ በፊት ኤርትራ ውስጥ ትግል ላይ የነበሩ ሰዎች ደረሰባቸው ስለተባለው ነገር ነው፡የዘገባው ቁም ነገር ምስጢር መንገር እንጂ ህዝብ የሚያውቀው በተለያየ ጊዜ በተለያየ ሚዲያ የቀረቡ ትረካዎችን ማቅረብ አይደልም፡፡የትህዴን መሪ መገደል ከዚህ በፊት የታወቀ ቢሆንም የዋህዎች የኤርትራ መንግስት ልማድ አለው ብለው እንዲሳሳቱ ለማድረግ ካልሆነ በስተቀር የትም ቦታ ተበትኖ ያለ መረጃን ለማግኘት ሁለት ወር ሊፈጅ አይችልም፡፡የተገደሉትም ሆነ የት እንዳሉ የማይታወቁት ሰዎች በኤርትራ መንግስት ስለመገደላቸው ወይም ስለመሰወራቸው በሰነድ የተረጋገጠ መረጃ አልቀረበም፡፡እዛው ይታገሉ ነበር እዛ አካባቢ እንዲህ ሆኑ ከማለት በስተቀር፡፡የነገሮቹን መሆን በመረጃ ባልተረጋገጠበት ሁኔ ታ የኤርትራ መንገስት አንዳርጋቸው ጽጌን አሳልፎ ሰጥቶታል ለሚለው ሀሳብ እንዴት አጋዥ ሆኖ ቀረበ የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡ባይሆን እነዚህ ጉዳት ደረሰባቸው የተባሉ ሰዎች በእንደዛ አይነት መካተታቸው በየግንባሩ ያሉ ሀይሎች ተስፋ እንዲቆርጡና ከኤርትራ መንግስት ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማበላሸት ነው፡፡የግብጽ፣የኳታርና የኢሳት ስም መነሳት ጉዳይም ሌላ ነገር መው፡፡ የኢቲቪ ዶክመንተሪ አይነት አዘጋገብ፡፡ኢሳት የግንቦት7 ነው አይነት አገላለጽ ነው አንድምታው፡፡ደግሞም ወደ ኤርትራ ለትጥቅ ትግል ይመላለስ የነበረ ሰው ግብጽና ኳታር የኤርትራ የልብ ወዳጆች መሆናቸውን ለመረዳት አያቅተውም፡፡ይህንን ለማወቅ ሁለት ወር አይፈጅም፡፡ በአንዳርጋቸው ጽጌ ላይ አፈና የተደረገበት የመን ነው፡፡ ከመነሻ እስከ መድረሻው የአፈና ሁኔታውና የኤርትራ ደህንነቶች እንዴትና በማን እንደተቀነባበረ ተልአኮውን ለማሳየት አንድ ፍንጭ እንኳን ሳይሰጥ፣ለአንዳርጋቸው ጽጌ መታገት ማሳመኛ አድረጎ ያቀረበው የአንዳርጋቸው ያለ ኢሳያስ ፈቃድ ከግብጽ ጋር መነጋገሩን ነው፡፡ኢሳያስም በዚህ ቂም ይዞ አንዳርጋቸውን ለዚህ እንደዳረገው፡፡ይህ ያለው ነገር በመረጃ አላረጋገጠም ፡፡የጠቀሰው አንድ ጊዜ ዳዊት ከበደ የለቀቀው የብርሀኑ ነጋ የተጠለፈ ድምጽ ነው፡፡ኤልያስ ክፍሌ ኤርትራ አንዳርጋቸው ጽጌ አያስፈልግም ብላ ለወያኔ አሳልፋ እንድትሰጠው ሊያደርጉ የሚችሉ የተረጋገጡ መረጃዎችና ትንተናዎች የሉም፡

፡ሌላው የዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ስም መጠቀስ ነው፡፡against Dr Berhanu Nega’s advise ምን ማለት ነው ? ተው አትሂድ እያለው…አንዳርጋቸው የመጣው ይምጣ ብሎ ሄደ፡፡ይህም ሪስክ የወሰደው ለአላማ ብሎ ስለ ሆነ ልናከብረው ይገባል ይላል;;ምን ማለት ነው፣ ነው ጥያቄው፡፡እውነት ለመናገር ይቺን ሀሳብ ሄኖክ የሺጥላ የወያኔ ሰላይ እንዲህ አለኝ ብሎ ለጥፎት ከነበረው ጽሁፍ ላይ አይቼዋለሁ፡፡ያ ጽሁፍ ደግሞ የነበረው ግንቦት7 አንዳርጋቸው መያዙን በነገረን ሰሞን ነው፡፡ከአባባሉ ግን አንድ አንድ ነገር ጨብጦ መውጣት ይቻላል፡፡አንድ በኤርትራ ውስጥ የነበረው የማደራጀት ስራ በብርሀኑ ነጋ እየቆየ እምነት እንዳጣ፣አንዳርጋቸው ጽጌም በቃ ያ አያዋጣንም ተወው አትሂድ ብሎ ብርሀኑ ነጋ ከዚህ በፊት ለትግል አጋሩ የፈለገ ፈተና ቢመጣ አብረን ነን ካንተ ጋር ነኝ የሚለውን ቃል ኪዳኑን እንዳጠፈበት፣ እንደ ከዳው ፣አንዳርጋቸው ጽጌም ፣የፈራ ይመለስ በሚል ስሜት ብቻ ይዞ ስለጉዞው በቂ ጥናትና ትንተና ሳያደረግ ጉዞ ማድረጉን ያረገዘ ሀሳብ ይዟል፡፡በሌላ አባባል ብርሀኑ አትሂድ ብሎት ከሄደ ቢሄድ ችግር እንደሚገጥመው ያውቅ ነበር ማለት ነው፡፡ዶ/ር ብርሀኑ ቢሄድ ችግር እንደሚያጋጥመው እንዴት አወቀ? ወይንስ ብርሀኑ ነጋ ከኤርትራና ከሌሎች ደህንነቶች ጋር በመሆን አንዳርጋቸውን ይከታተለው ነበር?ደግሞስ ብርሀኑ ነጋ አንዳርጋቸው ጽጌን ..ሂድ አትሂድ ብሎ..በዚህ ጉዳይ የሚመለከታቸው ሌሎች ወሳኝ የአመራር ሀይሎችን ሳያማክር መመሪያ መስጠት ይችላል?የግንቦት 7 ድርጅታዊ አሰራር እንዲህ ከላይ ወደታች የማውረድ የመለስ ጊዜው አይነት የኢህአዴግ ውስጥ አሰራር ነው?ሌሎቹ አሻንጉሊቶች ናቸው? በቃ ግንቦት 7 የሚታገለው እንዲህ አይነት በአንድ ሰው ፈላጭ ቆራጭነት ሀገሪቷን እንድትመራ ነው? ኤልያ ክፍሌ አይደለም በኤርትራ በረሀ የተደረጉት ነገሮች፣አይደለም አንዳርጋቸው ጽጌ ከግብጽና ኳታር ጋር ምን አይነት ግንኙነት እንደነበረው፣አይደለም አንዳርጋቸው ጽጌን እንዴትና በማን ተላልፎ እንደተሰጠ ሊያውቅ ይቅርና አጠገቡ ያለው የግንቦት7 ድርግት ውሳኔ እንዴት እንደሜሰጥ አያውቅም፡፡ቢያውቅ ኖሮ ብርሀኑ ነጋ አትሂድ ብሎት ነበር በቃ የመጣው ይምጣ ብሎ አያወራም ነበር፡፡ብርሀኑም አይልም ፣አንዳርጋቸውም አያደርግም፣


No comments:

Post a Comment