Thursday, September 18, 2014

በሽብርተኝነት የተከሰሱት አርባ ምንጭ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ወደ ማእከላዊ እስር ቤት ተወሰዱ

ኢሳት ዜና :-የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ሆነው ለግንቦት7 የአርባ ምንጭና አካባቢው ወጣቶችን በመመልመል ወደ ኤርትራ ይልካሉ በሚል ጥርጣሬ ተይዘው ለሳምንታት በአርባ ምንጭ እስር ቤት ታስረው የቆዩት የፓርቲው የአርባ ማንጭ ምክትል ሰብሳቢ በፍቃዱ አበበ እንዲሁም የድርጅት ጉዳይ ሃላፊው ኢንጂነር ጌታሁን  ወደ ማእከላዊ እስር ቤት መወሰዳቸውን የፓርቲው ድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ ለኢሳት ገልጸዋል።ኢንጂነር ጌታሁን በየነ ቀደም ብሎ ተፈትቶ የነበረ ቢሆንም፣ በድጋሜ በሌሎች ላይ ትመሰክራለህ ተብሎ በድጋሜ መያዙን አቶ ብርሃኑ ተናግረዋል።መንግስት የወሰደው እርምጃ ሰማያዊ ፓርቲን ለማዳከም መሆኑንም ሃላፊው አክለዋል

No comments:

Post a Comment