Thursday, September 18, 2014

የጊፍት ሪል ስቴት ባለቤት ታሰሩ

የጊፍት ሪል ስቴት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ባለቤትና ዋና ሥራአስኪያጅ አቶ ገብረየሱስ ኢተጋ በአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር የሊዝ ቦርድ ከተፈቀደላቸው መሬት በላይ ይዘው በመገኘታቸው ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ዋሉ
አቶ ገብረየሱስ በቀድሞ ወረዳ 28 ልዩ ስሙ የካ አባጣፎ ተብሎ በሚታወቅ አካባቢ ከተረከቡት መሬት በተጨማሪ ከ30ሺ ካሬሜትር በላይ ይዘው በመገኘታቸውና እንዲያስረክቡም በተደጋጋሚ ቢጠየቁም ፈቃደኛ ሆነው ባለመገኘታቸው ከትላንት በስቲያ ሰኞ ዕለት በቁጥጥር ሥር ውለው ትላንት ፍ/ቤት መቅረባቸውን ምንጮቻችን ጠቁመዋል።ምንጮቻችን እንዳመለከቱት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሊዝ ቦርድ ለጊፍት ሪል ስቴት በቀድሞ ወረዳ 28 የካ ለገጣፎ አካባቢ የሚገኝ 13 ሄክታር መሬት ቦታ 21 ባለ 3 ፎቅ ኮንዶሚኒየም፣ 81 ቪላ ቤቶች፣ በመጀመሪያ ፌዝ ለመገንባት፣ 20 ኮንዶሚኒየም ሕንጻ እና 130 ቪላ ቤቶች መዝናኛ ሱቆችና ቢዝነስ ሴንተር ያለው ግንባታ በሁለተኛው ፌዝ ለመሥራት በሪል ስቴት መመሪያው መሠረት የሊዝ ዋጋውን ከፍሎ ይህንን ጉዳይ በቀድሞ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ የሚመራው አስተዳደር ጥቆማ ቀርቦለት የካቲት 17 ቀን 2004 ዓ.ም በቃለ ጉባዔ ቁጥር 18/2004 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ጊፍት ሪል ስቴት በሕገወጥ መንገድ የወሰደውን መሬት እንዲመልስ ወስኖ ክፍለ ከተማውም በእጁ የሚገኘውንም ካርታ እንዲያመክን ማዘዙን ምንጮቻችን አስታውሰዋል።ሊዝ ቦርድ ቃለጉባዔ ቁጥር 4/97 በቀን 2/2/1997 እንዲወስዱ ተወስኗል። ሆኖም ጊፍት ሪል ስቴት የውል ማሻሻያ አድርገናል በማለት የመሬት መጠኑን አሳድጎ በሕገወጥ መንገድ ትርፍ መሬት መያዙን አስተዳደሩ አረጋግጧል።

No comments:

Post a Comment