Thursday, September 11, 2014

ጋዜጠኛ እና መምህርት ርዕዮት ዓለሙ ደህንነት አደጋ ላይ ነው፡፡ 



እህታችን እስከዳር ይህንን ማስታወሻ ከጻፈሽው አመት ሆነው አሁንም የርእዮት ጉዳይ አልተለወጠም አልተሻሻለም።

ማስታወሻ፦እነሆ ይህንን ማስታወሻ ከፃፍኩ ዛሬ አመት ሆነ፤ ካየኋት አመት ሞላኝሉሉዬ ምንም ባላይሽም ያጠንካራ መንፈስሽ አብሮኝ ነዉ!!መልካም በአል መልካም ዘመን ይሁንልሽ የኔ ሁሉነገር!! ጳጉሚ 2006

እኔ ባልፍም እንኩዋን ሺህ ርዕዮቶች ስላሉ በርቱ” !
==============
"የማልጨርሰዉን ነገር አልጀምርም እኔን ለማንበርከክ እና ለማሸማቀቅ ክሆነ መቼም አላረገዉም ትገይኝም ከሆነ ነይ ተኩሺ " ስትል ጎትተዉ ወሰዱዋት፡፡ እኛንም ከጊቢዉ አዋክበዉ አስወጡን፡፡ በማለት እህቷን ለመጠየቅ ቃሊቲ የሄደችው Eskedar Alemu የጋጣማትን ነገር በማህበራዊ ድረ-ገፅ አሳውቃናለች፡፡

በርዕዮት ላይ እየደረሰባት ያለው ህገወጥ ተግባር ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ባልሆነ መንግድ የሚፈፀም መሆኑ ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ፤እየደረሰባት ላለው ህገወጥ ተግባር በመቃወም በአሁን ሰዓት ርዕዮት የርሃብ አድማ ላይ ትገኛላች፡፡
በተለይ አሚናዘር የምትባል የወያኔ ቀንደኛ አገልጋይ በርዕዮት ላይ ከፍተኛ ተፅኖ እያደረሰችበት እንደምትገኝ እንዲሁም ኮ/ል ሐይማኖት የገብሩዋድ ባለቤት በመኝቷ ክፍል ማስፈራሪያ እና ዛቻ እንደምታደርስባት ርዕዮት ለቤተሰቦቻ ገልፃለች፡፡

ሁኔታው ይበልጣ አሳሳቢ የሚያደርገው ርዕዮት ለቤተሰቧቻ እና ለአድናቂዋቻ ያስተላለፈችው መልዕክት ነው “ህይወቴ አደጋ ላይ መሆኑን አንድ ነገር ቢፈጠር በህመም እንዳልሆነ እንድታዉቁት እኔ ባልፍም እንኩዋን ሺህ ርዕዮቶች ስላሉ በርቱ አትደናገጡ” ማለቷ የመንፈስ ጥንካሬዋን ቢያመላክትም እየደረሰባት ያለው በደል ከመጠን ያለፈ መሆኑ አመላካች ነው፡፡
ውድ እህቴ ርዕዮት ! ፈጣሪ ብርታቱን አብዝቶ ይስጥሽ፣ከምትወጂያቸው ቤተሰቡ እና ወዳጅ ዘመዶችሽ የምትገናኚበት ቀን እሩቁ አይሆንም!!! ይህም እውነት እንዲሆን የእውነት አምላክ ከጎናችን ነው፡፡
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!


Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

No comments:

Post a Comment