Tuesday, September 16, 2014

አባተ ኪሾና የጭቃ ፖለቲካ( አርአያ ተስፋማሪያም)

ቦታው ወህኒ ቤት ነው፤ የቀድሞ ደቡብ ክልል ፕ/ት አባተ ኪሾ፣ ስዬ አብርሃ፣ ዶ/ር ታዬ ወ/ሰማያትና ታምራት ላይኔ በእስር እያሉ ያወጋሉ። አባተ ኪሾ እንዲህ አሉ፥ « መለስ ዜናዊ የተናገረኝን መቼም አልረሳውም፤.. እንዲህ ነበር ያለኝ፤ “አባተ አንተና የአዲስ አበባ ቆሻሻ ማፍሰሻ ቱቦ አንድ ናችሁ። የተቀበለውን ሳያስተላልፍ ውጦ የሚያስቀር፤…አንተም ለሕዝብ እንድትናገር የነገርንህን ውጠህ የምታስቀር (የማታስተላልፍ) የዚህ ከተማ ቱቦ አይነትህ ነህ።…አባተ ኪሾም ሆነ ሌሎቻችሁ የውሸት እያለቀሳችሁም ቢሆን ካድሬና ህዝቡን ማሳመን አለባችሁ!”..ማለታቸውን አንደኛው እስረኛ ነግረውኝ ነበር።…አሰፋ ጫቦ ደግሞ በስብሰባ ላይ ስድብ ስለበዛ « እባክህ አቶ መለስ ስድቡን አስቁም?» በማለት በግል ሲጠይቋቸው « ዝም በል..ፊዳል» ብለዋቸዋል መለስ። “አቃጣሪ” ማለታቸው ነው።..መስከረም 2000ዓ.ም ፓርላማው ሲከፈት ስለ ሱማሊያ ጦርነት ከክቡር ዶ/ር ነጋሶ ጥያቄ የቀረበላቸው መለስ ዜናዊ « የሱማሊያን ጦርነት በኮንደም አልተዋጋነውም» ብለው አረፉት። በዛው አመት « ወራዳ ..እደግመዋለሁ ወራዳ…» እያሉ ብዙ ተናገሩ። መለስ «ትምክህተኛ፣ ጠባብ፣ ጐጠኛ፣ ጦርነት ናፋቂ..» የሚሉ ቃላቶች ከአፋቸው አይጠፉም። « እስከአንገታችን በስብሰናል፣ ገምተናል..» ብለዋል። በምርጫ 97 « ጣት እንቆርጣለን» ሲሉ በቲቪ መስኮት የዛቱት መለስ ዜናዊ ለፈፀሙት የጅምላ ግድያ በአጣሪነት ለተቋቋመው ኮሚቴ ሰብሳቢ ዳኛ ወ/ሚካኤል መሸሻ ሲናገሩ « ይህን ሪፖርት ብታቀርብ በቦዘኔ መንገድ ላይ አስገድልሃለሁ» እንዳሏቸው አጋልጠው ነበር። ክቡር ደ/ች ዶ/ር ዘውዴ ገ/ስላሴ (ነፍሳቸውን ይማር) መለስና ስብሃት ሲያናግሯቸው « አንተ በአንድነት አስታከህ የፊውዳል ስርአት ለመመለስ የምትፈልግ የፊውዳል ርዝራዥ ነህ፤.» ብለዋቸው እንደነበረ በሃዘን አጫውተውኛል። መለስ ዜናዊ ለገዛ የትግል ጓደኞቻቸው አልተመለሱም፤ የመጀመሪያዋን የሴት ታጋይ አረጋሽ አዳነ ስቅስቅ ብላ እስክታለቅስ ተናግረዋታል፤ እንዲሁም በ2002 የካቲት ወር መቀሌ አደባባይ በትግርኛ ቋንቋ ንግግር ያደረጉት መለስ ዜናዊ በፖለቲካ የተለይዋቸውን (አረና ፓርቲ) ሲሳደቡ « ባህር ውስጥ ሽንትህን ብትሸና ለውጥ አያመጣም። እነዚህ ሰገራ (ፍታን) ናቸው። ጭቃ (ኩርሲ ) ናቸው…» በማለት እንደተናገሩ የሚታወስና የአቶ ገብሩ አስራት መፅሐፍ ጭምር ቃል በቃል የሚገልፀው ነው። ይህ ነው የመለስ “ራዕይ”!?.. “ ከአፀያፊ የስድብ ጐተራ” በጥቂቱ የተቀነጨበ። አፀያፊ!!


No comments:

Post a Comment