Tuesday, September 9, 2014

በቀጣዮቹ የግንቦት 7 ህዝባዊ ስብሰባዎች ኢትዮጵያውያን በነቂስ በመውጣት እንደሚሳተፉባቸው ይጠበቃል

ግንቦት 7 የፍትህ፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ባሳለፍነው ቅዳሜ፤ እሁድና ሰኞ በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች የተካሄዱትን ጨምሮ በደ.አፍሪካ፣ በኖርዌይ፡ በጀርመን፤ በካናዳ፡ በአውስትራሊያ፡ ፊንላንድ፡ በኒውዝላንድና በደ. ኮርያ ስኬታማ ህዝባዊ ስብሰባዎችን ማካሄዱን መዘገባችን ይታወሳል። ላንች ነው ኢትዮጵያ! የሚል ስያሜ በተሰጠው በዚህ ህዝባዊ ስብሰባ ኢትዮጵያውያኑ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮችና ንቅናቄው ወደ ፊት ሊወስድ ባሰባቸው ዕቅዶች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን ተዘግቧል። በየመድረኩም ለወጣቶች፡ ለሴቶች ባጠቃላይ ለኢትዮጵያ ህዝብና ለመከላከያ ሰራዊቱ የተቀላቀሉን ጥሪ ቀርቧል። በቀጣይ ቀናት በሚካሄዱት ህዝባዊ ስብሰባዎችም በሌሎች አገራት እንደታየው ሁሉ በየ አገራቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በነቂስ በመውጣት እንደሚታደሙባቸውና ከንቅናቄው ከፍተኛ አመራሮች ጋር በአገራቸው ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ሰፊ ምክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። በዚህ በያዝነው ሳምንት በሴፕቴንበር 6 በአሜሪካ በሎሳንጀለስ ግዛት፤ በአውሮጳ በእንግሊዟ ለንደንና በስዊድን እስቶኮልም እንዲሁም በሴፕቴንበር 7 በሳንቲያጎ አሜሪካና በሜልቦርን አውስትራሊያ ህዝባዊ ስብሰባዎች በድምቀት እንደሚካሄዱ ይጠበቃል። የህዝባዊ ስብሰባዎች ቅድመ ዝግጅት ተጠናቆ ኢትዮጵያውያን እየተጠበቁ እንደሚገኙም ከየ አገራቱ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ግንቦት 7 የፍትህ፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በያዝነው ሳምንት መጨረሻ በሚካሄዱት ህዝባዊ ስብሰባዎች ላይ በየ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንዲገኙ በድጋሚ ጥሪውን ያቀርባል።


No comments:

Post a Comment