Friday, March 2, 2018

የኢትዮጵያው ፓርላማ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማጽደቁን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አወገዘ።

No automatic alt text available.አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ተቋም አምነስቲ ኢንተርናሽናል እንዳለው ፓርላማው የሕዝቡን ድምጽ ከመስማት ይልቅ አፈናን ለማራመድ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማጽደቁ እጅግ የሚያበሳጭና ሃላፊነት የጎደለው ነው። የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዋና ጸሐፊ ሳሊል ሸቲ የኢትዮጵያ ፓርላማ በዚህ አስቸጋሪና የፖለቲካ ቀውስ በተፈጠረበት ሁኔታ የሕዝቡን ድምጽ ሊሰማ ይገባ ነበር ብለዋል። አሁን የሚያስፈልገው የሕዝቡን ሰብአዊ መብት ማክበር እንጂ አፈና የሚያመጣው መፍትሄ የለምም ነው ያሉት። እንደ ዋና ጸሃፊው ሳሊል ሻቲ ገለጻ በኢትዮጵያ ባለፉት ጊዜያት ተደንግገው በነበሩ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጆች ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ተፈጽመዋል። እነዚህም ግድያዎች ጅምላ እስሮችና በሃይል መፈናቀልን እንደሚጨምርም ነው የገለጹት። እናም አሁን ሌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ማጽደቅ ተመሳሳይ ሕገወጥና በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት የሌላቸውን የሰብአዊ መብት ረገጣዎች እንዲፈጸሙ መስማማት ነው ባይ ናቸው። የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዋና ጸሃፊዋ ፓርላማው የሕዝቡን ድምጽ ከመስማት ይልቅ አፈናን መምረጡ እጅግ የሚያበሳጭና ሃላፊነት የጎደለው ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ የፓርላማ አባላት አዋጁን እንዳያጸድቁ በሕዝብም ሆነ በአምነስቲ ኢንተርናሽናል በኩል ቢጠየቁም በጉዳዩ ላይ 88ቱ አባላት ቢቃወሙም 346ቱ የድጋፍ ድምጽ ሰጥተዋል። ይህ ቁጥር ግን ከፓርላማው ጠቅላላ አባላት 2/3ኛ ድምጽ እንዳልሆነ ይታወቃል። ስለሆነም ፓርላማው ቁጥሩን አስተካክሎ የ395 ድምጽ ድጋፍ ተገኝቷል ማለቱ ሁኔታውን አወዛጋቢ አድርጎታል።

No comments:

Post a Comment