Tuesday, March 6, 2018

የመከላከያ እና የፖሊስ አባላት “መላ በሉን” እያሉ ነው

(ኢሳት ዜና የካቲት 27 ቀን 2010 ዓ/ም) በመካሄድ ላይ ያለውን ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊት አባላትና የፖሊስ አባላት ምን ማድረግ እንዳለባቸው እንደማያውቁ እየገለጹ ነው። ከዚህ ቀደም ባልታዬ መልኩ የጸጥታ ሃይሎች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ግራ መጋባታቸውን፣ የተደራጀ ሃይል ውስጥ ተቀላቅለው ትግሉን ማካሄድ ቢፈልጉም የመረጃ እጥረት እንደገጠማቸውና በከፍተኛ ግራ መጋባት ውስጥ እንደሚገኙ ፎቶግራፋቸውን ሳይቀር በማስረጃነት በመላክ እየገለጹ ነው። የመከላከያ አባላቱ የህዝቡን ትግል የሚደግፉ መሆናቸውን በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ በመናገር ላይ ናቸው። አንዳንዶች በፍተሻ ወቅትና ወጣቶችን ሲያገኙ እባካችሁ “ለእኛም ጸልዩልን በማለት እስከመናገር መድረሳቸውን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። መቱ ከተማን እዲቆጣጠሩ የተላኩት መከላከያዎች ‘እኛ ወንድሞቻችንን
ልንገድል አልመጣንም፣ ከቤት ባለመውጣት በምታሳዩት ተቃውሞ ምንም ልናስገድዳችሁ አንሞክርም፣ እኛም ከጎናችሁ ነን፣ ንብረት ብቻ እንዳይጠፋ አብረን ሰላም እናስከብር’እያሉን ለወጣቶች መልዕክት እያስተላለፉ ነው። ከዚህ በተጨማሪ እስከ ሙሉ ትጥቃቸው የሚሰወሩ የፖሊስና የመከላከያ አባላት ቁጥራቸው እየጨመረ መሆኑንም መረጃዎች ያመለክታሉ። የአዲስ አበባ ፖሊሶችም እንዲሁ በቡድን ሆነው ስለትግሉ ሃሳቦችን እየተለዋወጡ ነው። “ፖሊሶች ነጻ የወጡ ይመስላሉ” የሚለው ምንጫችን፣ በአሁኑ ሰዓት የአዲስ አበባ ፖሊሶች በስራ ሰዓት ሳይቀር ጥለው በመውጣት ስለ ለውጡ እርስ በርስ እየተነጋገሩ ነው። የደህንነት ሰራተኞችና የቀበሌ ሰራተኞችም እንዲሁ ስራ መስራት ማቆማቸውን ምንጮች የገልጻሉ። የቀበሌ ሰራተኞች

No comments:

Post a Comment