Saturday, October 4, 2014

አቶ አንዳርጋቸውን ለማስፈታት እንግሊዝ ለመንግስት መጮህ የዋህነት ነው::

ከቢላል አበጋዝ

ዋሽግተን ዲ ሲ

ለአጭር ግዜ ተጕዠ ካለሁት ቦታ ከመምጣቴ ቀደም ብሎ ከወድሞቼ አንዱ White Gold ትርጉም “ነጭ ወርቅ” የሚለውን በእንግሊዝኛ የተጻፈ መጽሀፍ አውሶኝ ነበር:: ሙሉ ርእሱ “አስገራሚው የቶማስ ፔሎ ታሪክና የእስላም አንድ ሚሊዮን ባሮች። ደራሲው ጋይልስ ሚልቶን የተባለ እንግሊዛዊ ነው::

 የተሰኘው ታሪካዊ መጽሀፍ ቶማስ ፔሎ ይባል የነበር በአስራ አንድ ዓመቱ በባሪያ ፈንጋዮች ታግቶ ሞሮኮ ተዋስዶ ሃያ ሶስት ዓመታት በባርነት ኖሮ ለማምለጥ ችሎ አገሩ የተመሰ ንግሊዛዊ ታሪክ ነው።  ቶማስ ፔሎ የተያዘው 1716 ዓ መ፡እ አ አ በዚህ ዘመን አልጀርስ ቱኒስ ሞሮኮ የባርያ ንግድ ማከሎች ነበሩ። ላነዴም ለሁሌም ሰሜን አፍሪካውያኑ ባሪያ ፈንጋዮች የተሸነፉት በ 1816 እ አ አ ነበር።በሰሜን አፍሪካ ይገኙ የነበሩት እስላም ባሪያ ፈንጋዮች በባህር ላይ ውጊያ ያየሉ ነበሩ። የንግሊዝ፡ፈረንሳይ፡እስፓኝና ጣሊያን ዜጎች ተባህር ተይዘው በባርነት ከገበያ ላይ ለጨረታ ይቀርቡ ነበር:: ቶማስ ከአምሳ አንድ ወገኖቹ ጋር ከተያዘ በኋላ ለሞሮኮው ሱልጣን ሙሌይ እማኢል ይሸጣል። ሙሌይ እማኢል በባሮች ጉልበት ታላላቅ  ቤተመንገስታት ሰርቶ በሺ የሚቆጠሩ ቁባቶች የነበሩት ጨካኝና አረመኔ ነበር። ሌሎች በአስር ሺህ የሚቆጠሩ አፍሪካውያንም ባሮች ነበሩት። ቶማስ ፔሎ ቀልጣፋ ደፋርና ቆራጥ ነበር። በዚህም ሱልጣን ሙሌይ እማኢል የግል አገልጋይ ሆኖ በቤተ መንግስት ውስጥ ይሆን የነበረው ግፍ ለማየት ችሎአል። የሰቆቃ ታሪክ ነው። ባርነት ቆዳ ቀለም የማይል የኢኮኖሚ ስርዓት እንደነበ ለማሰተማር የሚረዳ መጽሀፍ ነው::



ሱልጣን ሙሌይ እማኢልን የሚመስሉ ሟቹ መለስ ዜናዊን ያሉ ናቸው። ሙሌይ እማኢል ሁሉን በስጋትና ፍርሃት ሸብቦ ይገዛ ነበር። እሾም ይሆን? እሻር ይሆን? ስጋት የባለሟሎቹ የለት ተለት ኑሮ ነበር። ሱልጣን ሙሌይ እማኢል ቢያስር ቢገል በቃኝን የማያቅ ጨካኝና ጠርጣራ ስለነበረ ነው ከመለስ ማመሳሰሌ። ወደፊትም መለስ የሚታወሰው እንደ ሙሌይ እማኢልእንጂ  ከሞተም በኋላ “ባለራዕይ” ሊያደርጉት እንደሚሞክሩት  ግብዞችና የሰው ትንሾች እንደሚሉት አይደለም::

የቶማስ ፔሎን ታሪክ ሳነብ ዛሬ የእንግሊዝ መንግስት በአዳርጋቸው መታገት ላይ እያሳየ ያለ ቸልተኝነት ያስገርመኝ ነበር። በመጨረሻ ባሎቻቸው ለባርነት የተዳረጉባቸው  እንግሊዛውያን ሴቶች ድምጻቸውን አበክረው ሲያሰሙና የእንግሊዝ መንግስት እፍረት ላይ ሲወድቅ ይህን አሳፋሪ ጥቃት ለመከላክል ይዘምታል። ይህ እስተሜሆን ግን ዘመናት ያልፋሉ። የእንግሊዝ መንግስት ምንም አላደረገም ነበር::

የአቶ አንዳርጋቸውም መታገት ቶማስ ፔሎን ታሪክ መሰል ነው። ትርፍ ፈላጊ አረቦች ካገቱት በኌላ ለወያኔ ሸጡት። ለስቃይ ዳረጉት:: ዜግነነት ለሱና ለበተሰቡ የሰጠው የንግሊዝ መንግስት አይሟገትለትም:: የንግሊዝ መንግስት ከህወሀት መሩ መንግስት ጋር ወጅነቱን መርጧል። ይህን የንግሊዝ መንግስት ቸልተኝነት ለማስገንዘብ ነው ሰለ  የሰው ዘር መሆናችንን እንዳንጠላ የሚያደርጉን  ለሰው መብትና ነጻነት፡ ለሰላም፡ ለፍትህ የቆሙ ግለሰቦችና ድርጅቶት አሉ። ጩኅታች ወደነዚህና ከነዚህ ጋር ሊሆን ይገባል። የዝሆን ጆሮ ብሎ የተቀመጠውን የእንግሊዝ መንግስት መወትወት እርባና የለውም። በዘረኝነት የተተበተበ ስንኩል መንግስት ነው::  ነጭ ወርቅ እንኳ ቢሆን የሚጨነቅ አይደለም።እየጎመራ የመጣው የኢትዮጵያውያን የዲሞክራሲ ትግል የአንዳርጋቸው ጽጌ መታገት ወደአዲስ ምእራፍ እንዲሻገር አድርጎታል:: ወደፊት እንዲራመድ ገፍቶታል። ይህ ነው ትልቁ ውጤት::   ካፈለገው አገራችንን ከሚያካልል ስፍራ ዛሬ ሊወግነን ካለ ከማንም ወዳጅ ጋር ሆነን ህወሃት መሩን መንግስት ማስወገድ የትግላችን ምርጥ መንገድ ነው:: አንዳርጋቸው ጽጌ ህይወቱን የግል ነጻነቱን የከፈለበት እውነት ይሄው ነው::

ለሰው መብትና ነጻነት፡ ለሰላም፡ ለፍትህ የቆሙ ግለሰቦችና ድርጅቶች ጋር ሆነን ለአንዳርጋቸው ጽጌ፡ ለእክንድር ነጋ ለርዮት ዓለሙ ውብሸት ታየ ኦልባና ሌሊሳ ለጀግኖች የፖለቲካ መሪዎችና የሃይማኖት መሪዎች፡ ጋዜጠኞች መፈታት መታገላችን ይቀጥላል። በኢትዮጵያም ውስጥም በውጭም ያለን ይህ የየቀን ተግባራችን ከሆነ ህወሃት መሩ መንግስት እድሜው አጭር ነው።

ህወሃት መሩ መንግስት ዛሬ ተጠመዶ ያለው እያስተዳደረ ያለ መንግስት መስሎ ለመታየት ነው። ለወትዝሮው “ምርጫ” መሰል ግር ግር ነው። ያለፈ የህወሃትን ጅል ጫዋታ ታዝቦ ያሳለፈው ኩሩውና ምስጉኑ ህዝብ በትዝብ እየጠበቀ ነው። ባዶ ድርጅቶች ልብወለድ የመንግስት ተቀናቃኝ የፖለቲካ ድርጅቶች ይፈጠራሉ። ህወሃት መሩ መንግስት “ምርጫ” “ህግ” “ህገ መንግስት” ሁሉም እንዳቃዡት ይሰናበታል። ይህ አይቀርም::

የእንግሊዝ መንግስት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የጀርመኑ ሂትለር ሲያስፈራው  የሂትለር ወዳጅ ለነበረው ሙሶሊኒ አገራችንን እንዳሻህ አድርጋት ብሎ አሳልፎ የሰጠ ነበር:: ኋላ የሀይል አሰላለፍ ሲቀየር ሂትለርና ሙሶሊኒንን ማቸነፍ እንጂ ሌላ አማራጭ ሳይኖር ሲቀር የአገራችንን አርበኞች ረድቷል። መንግስታዊ ታሪኩ ይህ ቢሆንም አገራችን ለእንሊዝ ህዝብ ባለውለታ ናት:: ጄኔራል ኦርድ ዊንጌት ወይዘሮ ሲልቪ ፓንክኅርስት ሌሎችም ለነጻነት ኢትዮጵያን ካደረግነው ትግል ጋር ታሪካቸው ይኖራል።

አንድ አሙስ የቀረው የየመን መንግስት በታሪክ ከምናነበው ሰውን ለባርነት ከዳረጉት የተለየ አይደለም:: የእንሊዝ መንግስትም የሰለጠነ ዓለም ያደርገዋል ከሚባለው እጂግ ዝቅ ያለውን አድርጎ ለመገኘት መርጧል። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለማስፈታት፡ የዲሞክራሲ ትግላችንን ለማበርታት ትኩረታችን ዘወር ብሎ አጋር የሚሆኑንን አሰተውሎ መሄድ ይኖርበታል። በዚህ አጋጣሚ በአውሮፓ ህብረት ስለ አቶ አንዳርጋቸውና ሌሎች ስለታሰሩብን ወገኖቻችን የተደረው ክርክር ክዲፕሎማሲ ትግሉ አንጻር መልካም ውጤት ነው። ባሜሪካ፡ካናዳ እና አውስትራሊያ የሚደጋገም ይሁን። የንግሊዝ መንግስት ከተኛበት የሚነቃው ህወሃት መሩ መንግስት ሲሰናበት ነው እላለሁ:: ለአንዳርጋቸው ለሌሎችም እስረኞች በተሰቦች ኢትዮጵያ አምላክ ይታደገቸው።

ለዲሞክራሲ ለፍትህ ለኩልነት የምናደርገው ትግል ያቸንፋል!

እንቅፋቱን ህወሃት መሩን መንግት በቁርጠኛ ትግላችን እናስወግዳለን!!!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!


No comments:

Post a Comment