Wednesday, October 15, 2014

ማህበረቅዱሳንን ለማፍረስ ከመነሳት በፊት የራሳቸውን ካድሬያዊ ጵጵስና ያፍርሱ !!!

ጳጳሳት ከመንግስታት ጋር ተዋህደው ህዝብን ከማስጨቆን ውጪ እንደማህበረ ቅዱሳን በጎ የሆነ ስራ አልሰሩም።

ከአሁን ቀደም ለዜጎች የማይበጁ የሃይማኖት መሪዎች ለሼጎች የማይበጁ ከሆነ ቆባቸውን እንዲያወልቁ ተናግሬ ነበር። (http://minilik-salsawi.blogspot.com/2014/06/blog-post_18.html) ወደደም ጠላም ቄስም ሆነ ጳጳስ እያንዳንዱ በመንፈሳዊም ይሁን በስጋዊ ሕይወቱ እመራዋለው የሚለውን ምእመን ሁሉ የማገልገል ግዴታ አለበት። ይህ ካልሆነ የማይገባ አንቱታ የስድብ ያህል ይቆጠራል ነውና የሚሰራቸውን እኩይ ተግባራት እንዲያቆም ይነገርዋል።

ባለፈው እንደ መግቢያ የተተቀምኩትን ለመጥቀስ ያህል ቤተክርስቲያን እና መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ እጅና ጓንት ሆነው በኢትዮጵያውያን ላይ የማያባራ ጭቆና ማካሄድ ከጀመሩ ረዥም ዘመናት ተቆጥረዋል። ይብልጡኑ የመንግስቶች ጎህ ከቀደደ ጀምሮ በተለይ የተዋህዶ ሃይማኖት መሪዎች  አስፈሪ እና አስደንጋጭ እንዲሁም አሳዛኝ ደግሞም አሳፋሪ ቃላቶችን በመጠቀም ስጋዊ እና ምድራዊ ስልጣኖችን ለገዢዎች ለማደላደል ይህ ነው የማይባል ግፍ በምእመናኖቻቸው እን በሌሎች አማኞች ላይ ፈጽመዋል አስፈጽመዋል፤ እየፈጸሙ ነው፤ እያስፈጸሙ ነው። ይህ የማይዋጥለት አሊያም የሚክድ ካለ እውነት የማይደላው ብቻ ነው።

በዚህ ሰሞን ከበፊት ጀምሮ እየተቀጣጠለ የመጣ እና የተጋጋለ የማህበረ
ቅዱሳን ጉዳይ ቤተክህነትን ሲያምስ ሰንብቷል። እያመሰም ነው። በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የማይደሉትን እና የተማሩ ሰዎች ስብስብ የሆኑትን ቡድኖች ባገኘበት ሁሉ እየፈረጀ መበተን ከተያያዘ 20 አመታት አስቆጠረ፤ በአሸባሪነት እና በአክራሪነት ማስፋፋት ስም ከዘመተባቸው ማህበራት አንዱ እና ንብረቱን ወርሶ ለመቅበር ካሰፈሰበት ማህበር ዋነኛው እና በመንፈሳዊ አገልግሎት ታላቅ አስታውጾ ያበረከተው ማህበረቅዱሳን ተጠቃሽ እና የዚህ ሳምንት በስፋት ተዘምቶበት ይገኛል።

ማህበረ ቅዱሳን ባለፉት አመታቶቹ በሃገሪቱ ውስጥ በተለያዩ ክፍለ ሃገራት በመዘዋወር በተለያየ መስኩ ዘር ቀለም እና ሃይማኖት ሳይለይ በስፋት ኢትዮጵያውያንን በመርዳት የልማት አስታውጾ በማበርከት መንፈሳዊነትን በማስረጽ እና በማስተማር ወዘተ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በታሪክ ውስጥ በጉልህ ሊጠቀስ የሚችል ከፍተኛ የሆነ አስታውጾ አበርክቷል። ማህበረ ቅዱሳን ነዳያንን ከመርዳት አንስቶ እስከ ማቋቛም አስተምሮ ለወግ ማእረግ እስከማብቃት ድረስ ለውገን እና ለሃገር ተቃሚ ተግባራትን አበርክቷል። (ድህረገጹን http://eotcmk.org/site/ መጎብኘት ይቻላል)

የኢሕአዴግ መንግስት እና ጥቂት ለሆዳቸው ያደሩ ጳጳሳት ሲኖዶሱን በመጠምዘዝ ማህበረ ቅዱሳንን በአሸባሪነት እና በአክራሪነት ለማገድ ያደረጉት ሙከራ ይሁንታ በማጣቱ እስከዛሬ ሳይሳካ ቀርቷል።በእግዚአብሔር ፈቃድ በቅዱስ ሲኖዶስ ይሁንታ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለመደገፍና ለማጠናከር የተመሠረተው ማኅበረ ቅዱሳን ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ አያሌ ፈተናዎችን እያሳለፈ 22 ዓመታት ተጉዟል፡፡ማኅበረ ቅዱሳን በዓመታት ጉዞው ባከናወናቸው መልካም ተግባራት ታላላቅ የቤተክርስቲያን አባቶችን ጨምሮ እጅግ በርካታ ወዳጆችን እንዳፈራ ሁሉ ጥቂት በተቃራኒው የቆሙ ስሙን በየጊዜው በክፉ የሚያነሱ ቡድኖችም ተነሥተውበታል፡፡ወዳጆቹ የቤተ ክርስቲያን ወዳጆች ናቸውና በአገልግሎቱ ተማርከው በሚሠራቸው መልካም ሥራዎች ተስበው ቤተ ክርስቲያን ያለባትን የአገልግሎት ክፍተት ለመሙላት በጋራ ከማኅበሩ ጋር በመሥራት ሲተባበሩ፤ በአንጻሩ ጠላቶቹ ደግሞ የተለያዩ አጋጣሚዎችን እያስታከኩ ማኅበሩን ለመወንጀል እየተጣጣሩ ይገኛሉ፡፡

ማንኛውም አካል እንዲያውቅ የሚፈለገው ሐቅ ማኅበረ ቅዱሳን ቅዱስ ሲኖዶስ ለሰጠው ሓላፊነትና አባላቱም ለገቡለት ቃል ኪዳን ሃይማኖታቸው የሚፈቅደውን መስዋዕትነት ለቤተ ክርስቲያን ልዕልናና ክብር ለመክፈል የተዘጋጁ እንጂ በተዛባ አመለካከት ወደ ኋላ የሚያፈገፍጉ አለመሆናቸውን ማሳወቅ ግድ ይላል፡፡ማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎቱ የሚታይ አሠራሩም ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህም የመናፍቃኑ ተላላኪዎች መሠረተ ቢስ ውንጀላ ከአገልግሎታቸው አንዲት ጋት ወደ ኋላ እንደማይመልሳቸው ሊታወቅ ይገባል፡፡

No comments:

Post a Comment