Monday, October 13, 2014

ሰልጣኝ ተማሪዎች በፌደራል መደብደባቸው ታወቀ

ተቃውሞ አስነስተዋል የተባሉት ተማሪዎች ታስረዋል
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና ወስደው የውሎ አበል ያልተከፈላቸው የመጀመሪያ አመትና ነባር ሶስተኛ ዙር ሰልጣኞች ‹‹የውሎ አበላችን ይሰጠን›› በሚል ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣታቸው በትናንትናው ዕለት በፌደራል ፖሊስ መደብደባቸውን ተማሪዎቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ሰላማዊ ሰልፉን አደራጅታችኋል የተባሉ በርከት ያሉ ተማሪዎች መታሰራቸውንም ታውቋል፡፡
ስልጠናውን አርብ መስከረም 30/2007 ዓ.ም የጨረሱ ሲሆን መጀመሪያ ላይ እንደሚከፈላቸው ቃል ተገብቶላቸው የነበረው የውሎ አበል አይከፈላችሁም በመባላቸው በትናንትናው ዕለት ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል፡፡ ተማሪዎቹ አበሉ አይከፈላችሁም ቢባሉም አሰልጣኞቻቸው ‹‹ገንዘቡ መጥቷል፡፡ አንከፍልም የሚሉት ዝም ብለው ነው›› ማለታቸው ተማሪዎቹ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲወጡ ገፋፍቷል ተብሏል፡፡ የፌደራል ፖሊስ ሴት ተማሪዎች ከግቢው እንዳይወጡ የከለከለ ሲሆን ወንድ ተማሪዎች ከግቢው እንዲወጡ ከተደረጉ በኋላ መደብደባቸውንና መታሰራቸውን ተማሪዎቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
የደኢህዴን 22 አመት ምስረታን ተከትሎ በሀዋሳ በርከት ያለ ፌደራል ፖሊስ እንደነበርና ተማሪዎቹ አበላቸው እንዲከፈላቸው በጠየቁበት ወቅት ‹‹ከተማው ውስጥ ፌደራል ሞልቷል፡፡ እናስደበደባችኋለን›› እያሉ ያስፈራሯቸው እንደነበር ታውቋል፡፡


No comments:

Post a Comment