Monday, October 20, 2014

ኢትዮ ቴሌኮም ያወጣውን የአለባበስ ህገ ደንብ ከታህሳስ ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ገለፀ።

በ2006 ዓመተ ልደት መጨረሻ ላይ አመታዊ የስራ ክንውኖችንና ቀጣይ የማሻሻያ ግምገማና ውይይት የመንግስት ትልቁ ተቋም የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኞችን ጨምሮ የመስሪያ ቤቱ ትልልቅ ባለስልጣናት የተሳተፉበት ስብሰባ ተካሄዶ የነበረ ሲሆን በስብሰባውም ላይ በቴሌኮሙ ቀጣይ መሻሻልና መደራጀት ያለባቸው አሰራሮች ከስራተኞቹ የቀረቡ ሲሆን መሻሻል እንዳላባቸውና ከውጪ ሃገር(foreign country) አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን(New technologies) በማምጣት የተቀላጠፈ አሰራር በያዝነው አዲስ አመት አሻሽለን እንቀጥላለን በማለትም ስብሰባው የተቋጨ ቢሆንም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የኢኮኖሚ ዘርፍ አስተባባሪና የኮሙዩኒኬሽንና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በአ/ቶ ደብረ ፂዮን ገብረ ሚካኤል የሚመራው የቀድሞው የኢትዮጲያ ቴሌኮሚኒኬሽን ኮርፕሬሽን የአሁኑ (ኢትዮ ቴሌኮም) በአመታዊ የስራ ውይይት ላይ ማሻሻያዎች ሊደረጉ ይገባል ተብለው ከቀረቡትና በጭራሽ ሰራተኞቹ ችግር ነው ያላነሱትን ሙስሊም የቴሌኮሙን ሰራተኞችን በቀጥታና በተዘዋዋሪ የሚጨቁንና ስራህን ወይም እምነትህን ምረጥ የሚል አባዛ የተጠናወተበትን የአለባበስ ህገ ደንብ በያዝነው አዲስ አመት እንዳወጣ ይታወሳል።

በአዲስ አወቃቀር ኢትዮ- ቴሌኮም ከተባለ ወዲህ አዲስ ማኅበር ያቋቋመው የቀድሞ የኢትዮጵያ የቴሌ-ኮምንኬሽን ኮርፕሪሽን ባወጣው ህገ ደንቡ ላይም ማንኛውም የኮርፖሬሽኑ ሰራተኞችና አስተዳደር ፂማቸውን ማሳደግ እንደማይችሉ፣ ሱሪያውን ማሳጠር እንደማይችሉ፣ ለሴቶች ደግሞ አባያ፣ ጅልባብ፣ ኒቃብ፣ አባያ መልበስ እንደማይችሉ ና ጉርድ ቀሚስ ና ሸሚዝ እንዲያደርጉ የተገለፀ ሲሆን ሙስሊሞችን ብቻ አላማ ያላደረገ ለማስመሰል በደንቡ ላይ ፀጉር ማሳደግ፣ ፀጉር መፈረዝ፣ ሲኪኒ ሱሪ መልበስ ወ.ዘ.ተ እንዳይደረግ የተገለፀ መሆኑ ተገልፆል። ይህ በኢትዮ ቴሌኮሙ የሚሰሩ ሙስሊም የሃገሪቱ ዜጎችን በቀጥታ የሚያሸማቅቀውም ህገ ደንብ ከጥቅምት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልፆ እንደነበር ይታወሳል።

ይሁንና የቂሊንጦ ልሳን ምንጮቻችን ሙስሊም የቴሌኮም ሰራተኞችን የሚያሸማቅቀው የአለባበስ ህገ ደንብ ተግባራዊ ይደረጋል የተባለው ከያዝነው ከጥቅምት ወር ጀምሮ ነው ቢሉም በድጋሚ ለታህሳስ ወር ተግባራዊ ይደረጋል በማለት ማሻሻያ እንደተደረገበት ዘግበዋል።

በወርሃ ጥቅምት ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ የአላባበስ ህገ ደንብ ያወጣው ኢትዮ ቴሌኮም ህገ ደንቡን ለሰራተኞቹ በኢሜል ልኮ አስተያየትም እንዲሰጡት የጠየቀ ሲሆን በቴሌኮሙ የሚሰሩ ካድሬዎችን በኢንተርኔት መረብ በማደራጀት አሪፍ ህግ ነው፣ ይቀጥል፣ መሳጭ ህግ ነው፣ ይበረታታል…(fantastic,­ intersting, it sound’s nice etc) በማለት የሃሳብ መስጫው ላይ አስተያየት (comment) እንዲሰጡ አድርገው ድጋፍ እንዳገኙ አድርገው ለማቅረብ እንደሞከሩ ምንጮቻችን ዘግበዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም ህገ መንግስቱንና አለም አቀፍ ስምምነቶችን በግልፅ የሚንደውን ህገ ደንብ ከወርሃ ጥቅምት ለታህሳስ ወር ያሸጋገረበትም ምክንያትም የወጣው ህገ ደንብ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲደረግ ቅድመ ዝግጅት ይልስፈልገዋል የሚል ሃሳብ እንደተነሳና የኢትዮ ቴሌኮም ማህበርም ሃሳቡን ስላመነበት ሁሉም ሰራተኞች ቅድመ ዝግጅት ሊያደርግ ይገባል ብለው ለሰራተኞች ኢሜል እንዳደረጉላቸው ተገልፆል።

ፍትህ ለኢትዮጲያ ሙስሊም!
ፍትህ ለክርስቲያን ወገኖቻችን!


No comments:

Post a Comment