Sunday, October 19, 2014

ህወሃት በአማራ ነገድ ሕዝብ ላይ የሚያካሂደውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ የሚያስቆመው ማን ነው? (አንተነህ ገብረየ )

አንተነህ ገብረየ

(ከዚህ ቀደም ከጉራ ፈረዳ የተፈናቀሉ አማሮች፡ ፎቶ ፋይል)

መግቢያ፦ የዛሬ ጹሑፌን ከሰሞኑ ክስተቶች እጀምራለሁ-በዋሽንግተን ዲሲ ከአሜሪካው ፕረዘደንት ጋር ልዩ ውይይት ያደረገው በደሳለኝ ኃይለማርያም የተመራው የህወሃት ቡድን ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ማደጓንና በምግብ ራሷን መቻሏን ከአሜሪካው ፕረዝደንት ምስክርነት በማግኘቱና በመሞካሸቱ ጮቤ እንደረገጠና ስለወደፊቱ የህወሃት መንግሥትና አሜሪካ ወዳጃሞች ሆነው በጋራ ስለሚቀጥሉበት በየተራ የተደረጉት ንግግሮች ሁለቱንም ትእዝብት ውስጥ የሚከትና ነገ ቁጭትን የሚግት መሆኑ ባይዘነጋም ከሁለቱም ዘንድ በጣም ጽንፍ የሆኑትን ነጥሎ መጥቀስ አስፈላጊ ነው።አሜሪካ ብቻ ሳትሆን ሁሉም የበለፀጉ አገሮች ለሦስተኛው ዓለም አገሮች በተለይም በሕዝብ ላልተመረጡ ጨካኝ የአፍሪካ መሪዎች (un elected dictator african leaders) እርዳታ የሚሰጡት ዲያስፖራውን ጨምሮ የየአገራቸው ሕዝብ የሚከፍለውን የታክስ ገንዘብ መሆኑ ይታወቃል።


ገንዘቡ በምንም ይምጣ በምን የራሳቸው ነው ይስጡ።አስገራሚው ጉዳይ ግን ከምስረታው ጀምሮ በቅጥፈት ያደገው የህወሃት ቡድን ውሸትን እንደ አንድ የገቢ ምንጭ በመቁጠር ከብቅለቱ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ የእርዳታ ገንዘብ ሲያጋብና ብድር ሲበደር ነገ ያን ብድር ማን እንደሚከፍለው ግልጽ ነው።እንደ አለመታደል ሆኖ ኢትዮጵያ በብድር ወገቧን የሚያጎብጥ ሕዝቧን እንደ እርጉዝ አስጨንቆ እንደ ሞፈር አርቆ የሚገድልና የሚያስር የሚያሰድድ እንጅ በመልካም አስተዳደር የሚመሩ መሪዎች አግኝታ አታውቅም።በእርዳታ ብዙ ገንዘብ ተሰጥቷል ይህ ገንዘብ ለሕዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት እንዲገነቡበትና አገልግሎ እንዲሰጡ ለሀገር ልማትና ብልጽግና የሚል ሽፋን ይኑረው እንጅ እርዳታውም ሆነ ብድሩ የሚውለው የኢትዮጵያን ህዝብ አፍኖ ለመያዝ የሚያፈነግጥ ከሆነም በኃይል አስገድዶ ለመግዛት በሌላ አነጋገር ማሰር፤ መግደል፤ማሰደድ፤ ማስራብ፤በበሽታ የሚያልቅበት ስልት መንደፍ እንደሆነ አይተነዋል። ብድሩም ሆነ እርዳታው ለመሪዎች የሚሰጠው ድጎማ ሁሉም ለምን ጉዳይ እንደሚውል አሜሪካ በሚገባ ታውቃለች በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ በግፍ መገደላቸውን፤ መሰደዳቸውን፤መታሰራቸውን፤በርሃብ እንዲያልቁ መደረጋቸውንም አሜሪካም ሆነ ሌሎች አበዳሪና እርዳታ ለጋሽ አገሮች ጠንቅቀው ያውቃሉ። ይህን እያወቁ ተዲያ ለምን እርዳታ ወይም ብድር ይሰጣሉ የሚል ጥያቄ የመነሳቱ ጉዳይ አይቀሬ ነው?

እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ በአንደኛውና ሁለተኛው የዓለም ጦርነት አውሮፓውያን አፍሪካን እንደ ሥጋ ተቃርጠው(ተከፋፍለው) ለመግዛት ወረራ ሲጀምሩ ከላይቤሪያ በስተቀር አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች በቀጥታ ቅኝ አገዛዝ ሥር ሲወድቁ የተወሰኑት በእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ሥር ነበሩ።ኢትዮጵያን ለመውረር የተሰለፈችው ጣሊያን በዘመናዊ የአየርና የምድር የማጥቂያ መሣሪያ ታጅባ የጀመረችውን ወረራ ጀግኖች ወላጆቻችን በእምነትና በአንድነት በገናናው”በእምየ ምኒልክና በባለቤታቸው ጣይቱ” መሪነት ፋሽስቱን የኢጣሊያ ወራሪ ጦር ኃይል ከአፈርና ቅጠሉ ከግንዱ ጋር በመደባለቅ ድባቅ መትታ በድል አድራጊነት የነጭን ትኩሳት የበረደች የጥቁር አገር መሆንዋን በዓለም ታሪክ አስመዝግባ ወጥታለች።ይህ ለእኛ የሚያኮራ ታሪክ የተመዘገበበት ለምዕራባውያንና ለነዳጅ ዘይት ባለቤቶች (የዓረብ ቱጃሮች) ደግሞ ውርደት ሆኖ የሚታወቅበት ሲሆን በቀልተኞች ጠላቶቻችን ጊዜ ከተገኘ ይህን እዳ የሚከፍለው የአማራው ነገድ ሕዝብና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን እንደሚሆኑ መደረጉም ግልጽ ነው።

በተለያዩ አጋጣሚዎችና ሁኔታዎች ይህን የአፀፋ ርምጃ ለመውሰድ ወይም ለመበቀል የልተፈነቀለ ድንጋይ አልነበረም።ኋላ ላይ ግን አንድ ጥሩ አጋጣሚ ተገኝቷል። ይኸውም የዘውዳዊ አገዛዝ ያስከተለው ችግር የፈጠራቸው ክስተቶች ነበሩ።በሊግ ኦፍ ኔሽን የተሸረበውን ሴራ ሁሉ በጣጥሶ ኤርትራ በኢትዮጵያ ሥር የራስ ገዝ አስተዳደር ሆና እንድትቆይና በሂደትም ወደ እናት ሀገሯ እንድትቀላቀል የተደረገውን ውል ገፋፍቶ በማፍረስ የአፄ ኃይለሥላሴ መንግሥት ትልቅ የሕግ ጥሰት በመፈፀሙና የሚያስከትለውን አደጋም ለመስማት ፈቃደኛ ሆኖ ባለመገኘቱ ስህተቱ የኤርትራ ተፋላሚዎችን ሻእብያና ጀበሃን ወለደ፤ በትግራይ ህወሃትን ወለደ፤በሌሎች የኢትዮጵያ ግዛቶች ደግሞ የየካቲቱ ሕዝባዊ ንቅናቄ ሥርአቱን ሲጥለው በኋላ ላይ በኢሰፓ የተጠቃለሉ ድርጅቶችን፤መኢሶንን፤ኢህአፓን ወለደ እነዚህ ሁሉ በጣሊያንና እንግሊዝ ለተቀበረው ቦንብ ለም መሬት ነበሩ። ሻእብያና ህወሃት በጣሊያንና እንግሊዝ ፤በዐረብ የተቃኙ ሲሆን በርካታዎቹ ደግሞ መታጠፊያ በሌለው መንገድ መሄድ ጀመሩ በሩ ክፍት ሆነ ኢላማቸውን በአማራውና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን ላይ ያደረጉት የውጭና የውስጥ ጠላቶች ጊዜ እየጠበቁ ሰይፋቸውን(ጐራዴያቸውን) በክርስትና ሃይማኖትና በአማራ ነገድ ሕዝብ ላይ መምዘዝ ጀመሩ እልቂቱ እንደቀጠለ ነው።

ህወሃት ከተመሠረተበት ዕለት ጀምሮ ዋና ዓላማው አድርጎ የሚፈጽመው ተግባርም ይህ ነው።የአማራው ጠላት አማራው ነው እንድንል የሚያስገድድ አጣብቂኝ ውስጥም ገብተናል።ከቅድመ አብዮት በፊትና ድኅረ አብዮት በኋላ የተመለከትናቸው ከአማራው ነገድ ሕዝብ የተፈጠሩ ፖለቲከኞችም ሆኑ ምሁሩ ጣቱን የሚቀስረው በራሱ ነገድ ሕዝብ ላይ መሆኑ በግልጽ ይታወቃል።ራሱን ጨምሮ ሊያርዱት ሰይፍ የመዘዙ ጠላቶቹን ወግኖ በራስ ሕዝብ ላይ የእልቂት ናዳ የሚገፋና በመሪነት ተሰልፎ በጭፍጨፋ የሚተባበረው ትውልደ አማራ ሁኔታዎች ሲለዋወጡ አንድም ወንዝ የሚያሻግረው አይኖርም ራሱ የፈጠረውን ችግር ራሱ ይጋተዋል።ሁለት ነገሮችን ላንሳና ላሳይ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም አማራ የሚባል ነገድ የለም ብለው ሟቹን ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊን ሲያስደስቱና አሁንም ይለይላችሁ ብለው አሁንም የአማራ ጉዳይ አለ ወይ? በሚል ለንባብ ያበቁትን ተመልከቸ አዘንኩ ምሁሩም አሳዘኑኝ፤ዋለልኝ መኮንን ከአማራ ቤተሰብ የተፈጠረ ሲሆን ጣቱን ቀስሮ የነበረው ግን በአማራው ነገድ ሕዝብ ላይ ነበር።ከዚህ ወጣ ብሎ ደግሞ እውቁ የቀዶ-ጥገና ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ አማራውን ለመታደግ በመታገላቸው ህወሃትና ግብረ-በላዎች በሕመም ተሰቃይተው እንዲሞቱ አደረጉ።ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ቢሰነብቱ ለትግሉ ወይም አማራውን ከጥቃት ሰለባ ለመታደግ ከፈተኛ አስተዋጾ ያደርጉ ነበር። አልታደልንም አለኝታችን አጣን ይሁን እንጅ ፕሮፌሰሩ ትግሉን ገድለውት አልሞቱም አቀጣጥለውት እንጅ።ዛሬ ጎልቶ ባይወጣም የአስራትን ፈለግ እየተከተለ ያለ ትውልደ አማራ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ራሱን እያደረጀና በራሱ ዙሪያ ለተነጣጠረው አፈሙዝ ምላሹን ለመስጠት ምሽጉን እያዘጋጀ ይገኛል።ህወሃትና ግብረ-በላዎቹን ሊፋረዳቸው ተነስቷል። በተለይ የአማራው በሆነው ክልል በአማራው ስም የሚጠራውን ብአዴንን።

ክርስቲያኖች ከአንገታችሁ ማተብ አታድርጉ፤እስላሞች ኩፍታ አታድርጉ ተብሎ ሰሞኑን በዶክተር ሽፈራው የተነገሩ ፀያፍ ተግባር አባይ ፀሐየ የሚመራው ሲኖዶስ ፍቁድ ሆኖ በመታወጁ በብዙዎቹ ዘንድ አስገራሚ ሆኖ ስመለከት ወደ ኋላ ሄጀ እንዳስብ አድርጎኛል። ጣሊያን ጐንደር በገባበት ወቅት መሪ የፕሮፓጋንዳ አቅጣጫው ሕብረተሰቡን በተለያየ መንገድ መከፋፈል ነበር። እስላሙን ከክርስቲያኑ፤ሃብታሙን ከድኻው፤ የጐንደሩን አማራ በሸዋው አማራ ላይ እንዲነሳ ማድረግ ነበር። በወቅቱ ሕዝቡን ግራ ያጋባና እውነት ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት አሳድሮ እንደነበር ተገልጿል ውሎ አድሮ ግን ጣሊያን የመጣበት ዓላማ ነበረውና ሥራውን ሲጀምር ሕዝብ አንድ እየሆነ መጥቶ መፋለሙን ቀጥሎ ጣሊያንን አስወግዷል።አገር በቀል ጣሊያኖች ወይም ህወሃትና ግብረ-በላዎቹም የተጠቀሙበት መንገድ የጣሊያኑን መንገድ ነው።አማራውን ኢላማው ያደረግና ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት የተነሳ ድርጅት ኅይማኖተቢሶችና ኢትዮጵያዊነት የሚያሳፍራቸው የኢትዮጵያዊነትን ካባ ቢያጠልቁም ምንም አይነት የሀገር ፍቅርና እምነት እንዳልነበራቸው ግልጽ ነው በዚህ አገር ኦሪዮ ኩኪን አንዳንድ ወገኖች በምሳሌነት ይጠቀሙበታል በቆዳቸው ጥቁር ሆነው በተግባር ግን ነጩ በጥቁሮች ላይ የሚፈጽመውን ደባ የሚፈጽሙ እንደማለት ነው።ህወሃትና አጃቢዎቹም ትውልደ ኢትዮጵያዊ ቢሆኑም ተጠሪነታቸው ለውጭ ጌቶቻቸው መሆኑንና አሁንም በዚያው የጥፋት ጎዳና እየተጓዙ ባለበት ወቅት ኩፍታ አታድርጉ ማተብ አትሰሩ መባሉ የሚያስደንቀኝ አይደለም ሲኖዶሱ የፖለቲካ መሣሪያ ሲሆንና ከሀገር ቤት ወጥቶ በውጭው ዓለም የፖለቲካ ሥራና የገቢ ምንጭ ሆኖ እየሠራ እያየነው ለምን መገረም ያሻል መድኃኒቱን መፈለግ እንጅ።

እንደ ርእስ የተጠቀምኩበትን ጥያቄ ሌላ ወገን ይመልስልኛል ብየ አይደለም ምናልባት እያንጐላቸ ያለውንና እንደ አውዳ ዓመት በግ ተራ በተራ እየተጎተተ የሚታረደውን የአማራ ነገድ ሕዝብ ለማሰማት ነው።አማራው የፈራው ሞትን ከሆነ እየሞተ ነው የትኛውን ሞት እንደሚፈራ ግልጽ አይደለሁም በእውነቱ ከሆነ ሞትን የሚፈራው ንብረት ያካበተው አገር የወረረው የህወሃት ቡድን እንጅ አማራው መሆን የለበትም ምን አለውና ነው ሞትን የሚፈራው? በቁሙ የሞተ አይደለም ወይ?።የሚገድልህን ለመግደል ምን ትፈልጋለህ? እንዲያው የእናቴ ቀሚስ ጠለፈኝ ለማለት ካልሆነ በስተቀር መሣሪያ የሌለኝ ሆኖ ከኋላየ የሚከተል አጥቼ ማለት ምክንያት አይደለም።መሣሪያው 20ደቂቃ ጠብ በኋላ ማዛወር ይቻላል ጎራዴ መሣሪያ ነው፤ ገጀራ(ገጀሞ) መሣሪያ ነው፤ማጤ ወይም ፋስ መሣሪያ ነው፤ጦርም መሣሪያ ነው የህወሃትን ታጣቂ ዝም አሰኝቶ መሣሪያ መማረክ የማይቻልበት ምክንያት ምንድን ነው? ነፍጥ ይዘው ህወሃትን እየተፋለሙ ያሉ የተቃዋሚ ኃይሎችንስ ለመቀላቀል ምኑ ነው ያዳገተው?።የሚከተል ለማግኘት ደግሞ መጀገን ብቻውን በቂ ነው።””በላይ ዘለቀ ሽህ ጦር አልነበረውም፤መይሳው ካሣና ገብርየም እንዲሁ፤እነራስ አረጋይ፤ቢትወደድ አዳነ፤ራስ አሞራው ውብነህም እንዲሁ።ራስህን ነፃ ለማውጣት ራስህ መንቀሳቀስ እንጅ አንተን ነፃ ለማውጣት ግዥ የሚፈጽም ወይም ጀግና የሚበደር ያለ አይመስለኝም።በጊዚያቸው ጀግነው ጀግንነትን የፈፀሙና ታሪክ ሠርተው ያለፉ አባቶቻችን እናቶቻችን እኛን ነፃ ሊያወጡ ከመቃብር ሊነሱ አይችሉም። ትንሾች መስዕዋትነት ከፍለው ሽዎችን ቢታደጉ ምንም ክፋት የለውም። “”የዛሬን አብረኸኝ ቁም ከዚያ በኋላ እልሁ ያቆምሃል እንዳለችው””ጀምረው የሚጨርሰው ይመጣል።

“”የዚህ ጹሑፍ መነሻ ምንጮች ያትውልድ በክፍሉ ታደሰ፤ የኤርትራ ጉዳይ በአምባሳደር ዘውዴ ረታ ጣሊያን ጎንደር ሲገባ ከጎንደሬ በጋሻው ነው””


No comments:

Post a Comment