Tuesday, May 12, 2015

EBC ስለ ደቡብ ኦሞ ህዝብ የሰራዉ ዶክመንታሪ ለፖለቲካ ፍጆታ ወይስ ከልብ መቆርቆር

የወንበዴዉ መንግስታችን ልሳን የሆነዉ EBC በሙያተኞች እይታ ለፖለቲካ፡ ለትምህርት፡ለመዝናኞ፡ ለልማት ተብሎ የተቋቋመ ሚዲያ አለመሆኑን ማንም ያዉቀዋል፡፡ ግንቦት 2/2007 ዓ.ም ከሁለት ሰዓት ዜና በኋላ በደቡብ ኦሞ ዞን በሚኖረዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ( ይቅርታ ህዝቦች አላልኩም) የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት የሆኑት ዶ/ር ዬሴፍ ማሞ እና የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ዶ/ር ሽፈራዉ ተክለማሪያም ከሌሎች የደቡብ ክልል አገር ገንጣዩና ወንበዴዉ ህዉሀት እንደፈለገ የሚያሽከረክራቸዉ ቡችል ባለስልጣናት ጋር በመሆን በደቡብ ኦሞ ህዝብ ላይ ሲቀልዱበት ተመልክቸ ይህን አጭር መልእክት ልፅፍላቸዉ ወደድኩ፡፡በእኔ እይታ ለማህበረሰቡ የተቆረቆራችሁት Human Right Watch በህዝቡ ዘንድ እያደረሳችሁት ያለዉን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለማስተባበል ፈልጋችሁ እንጂ የማህበረሰቡ ችግር አሳስቧችሁ አይደለም ፡፡ የማህበረሰቡ ማህበራዊ፡ኢኮኖሚያዊ፡ ፓለቲካዊና ሰነ ልቦናዊ ችግር አሳስቧችሁ ከሆነ ለምትጠየቁት መልስ እየተንገሸገሻችሁ መልስ የምትሰጡት ማሰብ ጀምራችኋል ብየ ትርጉም ልስጠዉ ግን አይመስለኝም ለፓለቲካ ጠቀሚታ ይመስለኛል፡፡ ግን እስከመቸ ነዉ በህዝብ ላይ የምትቀልዱት ?…….. እስኪ ልጠይቃችሁ መልስ ካላችሁ?

1. እነዚህን ምስኪኖች በየዓመቱ ህዳር ወር በምታከብሩት የብሄር ብሄረሰብ በዓል ራቁታቸዉን እያስጨፈራችሁ እናንተ ከዉጭ ከደሀዉ ህዝብ ጉሮሮ በነጠቃችሁት ገንዘብ የሸመታችሁትን ዉድ ሱፍ ልበሳችሁና በጠባቂዎቻችሁ ተከባችሁ የምትዝናኑባቸዉና ለአለም ህዝብ የቱሪዝም የ Bussiness Promotion የምትሰሩባቸዉ ከሌላዉ ዓለም የመጣ ነጭ ሳይሆን እናንተ ናችሁ፡፡ 23 ዓመት በህዉነት ጥላ ስር ሁናችሁ እናንተ እና ልጆቻችሁ የለበሳችሁትን ልብስ እና እናንተ የምትከተሉትን የአኗኗር ዘየ እንዲከተሉ እንኳን ማድረግ አልቻላችሁም፡፡ እናንተ አይደላችሁ እንዴ በብሄር ብሄረሰብ ስም ባህላችሁን ጠብቁ እያላችሁ የምትጫወቱባቸዉ፡፡ ባህል እኮ ከጊዜ አኳያ የሚለወጥ እንጂ የማይለወጥ ግዑዝ ነገር አይደለም፡፡
2. አሁን ነዉ እንዴ በመንደር ማሰባሰብ ለልማት ጥሩ መንገድ መሆኑን የተገነዘባችሁ?:: ህዉሀት/ወያኔ እኮ በደርግ ጊዜ የተጀመረዉን በመንደር ማሰባሰብ/መንደር ምስረታ/ግንቦት 20 መላዉ ኢትዮጵያን በተቆጣጠረ ማግስት በታትኖ ወደ ነበረበት ኋላ ቀር አኗኗር የመለሰ የወንበዴ ስብስብ ነዉ፡፡ለነገሩ ህዉሀት የወንበዴ ስብስብ ስለሁነ ያልበታተነዉ ነገር የለም ( መሰረተ ትምህር በትኗል፤የገበሬወች ህብረት ስራ መሀበራትን በትኗል፤ ሲቪክ ማህበራትን በትኗል፤ አልቻለም እንጂ ኢትዮጵያዊነትን ለመበተን ሞክሯል)
3. ዶ/ር ዮሴፍ እስኪ ተጠየቅ የሌሎች አገሮች Anthropologist ትኮንናለህ፡፡ አንተ የምትመራዉ ዩኒቨርስቲ ለደቡብ ኦም ህዝብ ችግራቸዉን አጥንቶ ቢያንስ እኮ ልብስ እንዲለብሱና ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶችን እንዳያከናዉኑ ምን ሰራህ?……. ለ እኔ አሁንም አንትን የሚያክል ትልቅ ዩኒቨርስቲ የሚመራ ሰዉ እየቀልድክ ነዉ፡፡ አሁንም ሰፊ ጊዜ አለህ ማህበረሰቡን ለመለወጥ
4. ሌላዉ ማንነታቸዉን ያልለቀቁ ህዝቦች አሉ እያላችሁ ለቱሪዝም ልማታችሁ እንደ አንድ ቅርስ የምትጠቀሙባቸዉና ከገቢዉ የሚገኘዉን ገንዘብ ለግል ጥቅማችሁ የምትጠቀሙ እናንተ እና የ TPLF ዱርየዎች አይደላችሁም?:: በሰብዓዊ ፍጡር መጫወት እኮ አላማችሁ መሆኑን ማንም ያዉቀዋል፡፡እስኪ ያልተጫወታችሁበት ህዝብ ካለ ንገሩን፡፡አብሯቸዉ ለነፃነቱ የታገለዉን የትግራይን ህዝብ ችንኳን እንዴት እንደሚጫወቱበት የሚያዎቅ ያዉቀዋል፡፡
5. Human Right Watch ባይኖርና የምትሰሩትን እግፍ ባያጋልጥ እንደ አኙዋክ ህዝብ ጨፍጭፋችሁ መሬቱን ለዉጭ ባለሀብት ትቸበችቡት ነበር፡፡ ለነገሩ አሁንም አያሳደዳችሁ እየቸበቸባችሁት አይደል?
እባካችሁ አሁንም አልረፈደም ቢያንስ ሌላኛዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ( ይቅርታ ህዝቦች አላልኩም)የሚኖርበትን የባህል አኗኗር እንዲኖሩ የተጠናከረ ስራ ስሩ፡፡ ካልሰራችሁም ትንሽ ጊዜ ነዉ እኛ እንደርስላቸዋለን፡፡
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር፡፡


No comments:

Post a Comment