Wednesday, May 6, 2015

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት ማየሉ ተገለፀ፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ
ዜና
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት ማየሉ ተገለፀ፡፡
በአየር መንገዱ ውስጥ ጎሳንና የፖለቲካ አመለካከትን መሰረት ያደረገ የስራ መደብ፣ የስልጣን ድልድልና ትቅማጥቅም በመኖሩ፤ ሙስና በከፍተኛ ሁኔታ በመንሰራፋቱ፤ የአንድ ቋንቋ ተናጋሪዎች ብቻ የኢኮኖሚና ስልጣን የበላይነት በመግነኑ፤ እና ፍህታዊ የሆነ አስተዳደር ፈፅሞ በመጥፋቱ ምክንያት ሰራተኞች በተለያዩ ጥያቄዎች የአመራር አካላትን ማፋጠጥ በመጀመራቸው ነው የሰፈነው ከፍተኛ ውጥረት ሊከሰት የቻለው፡፡
ከዚህ ቀደም ግለሰቦች በፖለቲካ አመለካከታቸው ልዩነት ምክንያት ብቻ ከስራ ታግደዋል፤ አሁንም በርካቶች ከፍተኛ መንገላታትና የመብት ረገጣ እየደረሰባቸው እንዳለ ከውስጥ የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡
በህወሓታዊዩ ተወልደ ወ/መድህን የሚመራው አየር መንገድ ልክ እንደ ኤፈርት ሁሉ የህወሓት የግል ድርጅት እየሆነ መምጣቱን ብዙዎች ሠራተኞች ይመሰክራሉ፡፡
ይህ የአየር መንገዱ አመራር አካል በሰራተኞች ላይ የሚፈፅመው ግፍና በደል ያንገፈገፈው ረዳት አብራሪ ኃይለ መድን አበራ አውሮፕላን ይዞ በመጥፋት ስዊዘርላንድ-ጄኔቭ አሳርፎ ጥገኝነት በጠየቁና ተቃውሞውን ለዓለም ማሰማቱ የሁሉም የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment