Friday, May 22, 2015

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ለአማራው መፈናቀል ምክንያት የሆነው ክልሉ የፈረመበት ደብዳቤ ኢሳት እጅ ውስጥ ገባ

ሚያዝያ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በ2005 ዓም ቁጥራቸው ከ20 ሺ ያላነሰ በአብዛኛው ከመስራቅና ምእራብ ጎጃም የመጡ ዜጎች፣ ክልሉን ለቀው እንዲወጡ በመታዘዛቸው ቁጥራቸው በውል ያልተወቁት መንገድ ላይ ሲሞቱ፣ ሌሎች ደግሞ ቤት ንብረታቸውን አጥተዋል።
በጊዜው ኢሳትና ሌሎች የመገናኛ ብዙሃን ባደረሱት ተጽኖ መንግስት ተፈናቃዮች እንዲመለሱ ቢያደርግም፣ አጥፊዎችን ለፍርድ የማቅረቡ ጉዳይ ለረጅም ጊዜ ሲጓተት ቆይቶ በመጨረሻ መንግስት የተወሰኑ የወረዳ ባለስልጣናትን ለፍርድ አቅርቧል።

ይሁን እንጅ ኢሳት ውስጥ የገባው ሰነድ እንደሚያሳየው የማፈናቀሉ ትእዛዝ የመጣው በቀጥታ ከክልሉ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ሲሆን፣ ትእዛዙ በመን መንገድ መፈጸም እንዳለበት እቅዱ በግልጽ ተቀምጧል።
የማፈናቀሉን ደብዳቤ የጻፉት የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አብዱልናስር ሲሆኑ ድርጊቱን በዋናነት እንዲያስፈጽሙ ሃላፊነት የተሰጣቸው ደግሞ ምክትልዩ አምባሳደር ምስጋናው አድማሱ ናቸው። የክልሉ ፕሬዚዳንት በወቅቱ ትእዛዝ አለመስጠታቸውን ተናግረው ነበር።



በቁጥር 2110/ከ-12/እር-0021 በቀን 14/06/2005 ዓም ” በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መስተዳደር ጸጥታ ምክር ቤት የ2005 የካቲት ወር የወጣ የአንድ ወር የጸጥታ እቅድ” በሚል ርእስ የተጻፈው ደብዳቤ በዋና ዋና ተግባራት በሚለው እቅድ ስር ” ከአማራ ክልል መስራቅ ጎጃምና ምእራብ ጎጃም በህገወት መንገድ ፈልሶ በካማሽ ዞን በሎ ጅጋንፎይና አሶ ወረዳ የሰፈሩትን በመፈተሽ በአስቸኳይ ወደመጡበት መመለስ” የሚል መስፈሩን ለማየት ይቻላል።
ለእነዚህ ሰዎች በህገወጥ መንገድ መታወቂያ ደብተር በሚሰጡ የቀበሌ አመራሮችም ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ሰነዱ ያመለክታል።

ዝርዝር ተግባር በሚለው ስር ደግሞ ” በህገወጥ የገቡ በተለይም በምእራብ ጎጃምና በመስራቅ ጎጃም ባሉበት ተከታትሎ ወደ መጡበት መመለስና እነዚህን ፍለሰው የመጡ ሰዎች ቤታቸው ያስቀመጡትን አርሶ አደሮች፣ ባለሃብቶች በመለየት የማስተካካያ እርምጃ መውሰድ” የሚል ውሳኔ ሰፍሯል።
ይህንን ድርጊት የሚፈጽሙት ደግሞ የክልል መስተዳደር፣ ክልል አስተዳደር ጸጥታ ጉዳኢ ማስተባባሪያ ቢሮ፣ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ክልል ፍትህ ቢሮ፣ ክልል ሚሊሺያ ጽ/ቤት ና የመሳሰሉት ናቸው። ውሳኔውን ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ አምባሳደር ምስጋናው አድማሱ እና የክልሉ ትምህርት ቤሮ ሃላፊ አሰፋ ብራቱ በመሪነት እንዲያስፈጽሙ በውሳኔው ሃሳብ ላይ ተቀምጧል።

ተመስገን ድሳሳ፣ አስፋው ጅለታ፣ ሃብታሙ ታየ ከያሶ ወረዳ፣ ጋዎ ጃኔ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ እና ዚያድ አብዱላሂ የክልሉ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት በሎ ጅጋንፎይ ወርዳ እንደሚያስፈጽሙ ሰነዱ ያሳያል።
እነዚህ ሁሉ የክልል ባለስልጣናት እስካሁን አልተጠየቁም። ገዢው ፓርቲ ለይስሙላ የተወሰኑ የወረዳ ባላስልጣናትን ተጠያቂ ማድረጉ ያበሳጫው ክልሉ ጽ/ቤት ውስጥ የሚሰሩ የኢሳት ምንጮች፣ ይባስ ብሎ ከምርጫው ጋር በተያያዘ ክልሉን የሚመራውን የኢህአዴግ አጋር ድርጅት የሆነ ፓርቲ አንመርጥም የሚል አቋም በብዛት በመታየቱ ረብሻ ይነሳል በሚል ፣ ገጠር ውስጥ ያሉ ዜጎች ወደ አሶሳ እና ሌሎች ቦታዎች እየተሰደዱ ነው። በክልሉ የሚታየው ውጥረት አስፈሪ መሆኑንም ምንጮች አክለው ይናገራሉ።


No comments:

Post a Comment