Wednesday, May 13, 2015

Hiber Radio የቀድሞ የመኢአድ የሕዝብ ግኑኙነት ሀላፊን ጨምሮ በርካታ ወጣቶች ኤርትራ ለትጥቅ ትግል መግባታቸውን ገለጹ

ወጣት ተስፋሁን አለምነህ

የቀድሞ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበረው ወጣት ተስፋሁን አለምነህ በአገር ቤት የወያኔን አገዛዝ በሰላማዊ ትግል ታግሎ መጣል አይቻልም ብሎ በመወሰን እሱና ሌላው የመኢአድ አባል ደሳለኝ ሲሳይ ከበርካታ ወጣቶች ጋር ኤርትራ የትጥቅ ትግሉን ለመቀላቀል ሰሞኑን መግባታቸውን ለህብር ሬዲዮ ከስፍራው በሰጠው አጠር ያለ ቃለ ምልልስ ገለጸ።

<<በአስቸጋሪ ሁኔታ አልፈን የቀድሞው መኢአድ ግማሹ ክንፍ ኤርትራ ገብተናል>> በሚል አርዕስት ለህብር የላከውን ማስታወሻ እውነተኛነት ለማጣራት ባቀረብነው ጥያቄ የኤርትራ ስልኩን ልኮልን እሱም ሆነ ሌሎቹ በትጥቅ ትግል ስርዓቱን ለመጣል ኤርትራ የገቡ ወጣቶች መኖራቸውንና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ አልፈው በአማራ ዲሞክራሲ ሀይል ንቅናቄ ታጋዮች ተጋድሎ ጭምር ወደ ኤርትራ መግባታቸውን ጠቁሟል።

በአገር ቤት በሰላማዊ ትግዩ አምንን በተደጋጋሚ ስንታሰርና መከራ ሲደርስብን ነበር ያለው ተስፋሁን ሰላማዊ ትግሉ መሪያችን ፕሮፌሰር አስራትን ጨምሮ ብዙዎችን ከማስበላት ያለፈ ስርዓቱን ለማዳከም ባለመቻሉ የትጥቅ ትግሉን ለመቀላቀል ኤርትራ መግባታቸውን አረጋግጦልናል ።

<<ወያኔን በሰላማዊ ትግል አይወድቅም ከውጭም ሆነ ከአገር ውስጥ በትጥቅ ትግል መታገል ነው>> ያለው ወጣት ተስፋሁን አለምነህ ስርኣቱን በሰላማዊ መንገድ ብቻ ታግሎ መጣል አለመቻሉን ጠቅሷል።

ከወጣት ተስፋሁን አለምንህ ጋር ያደረግነውን አጠር ያለ ቃለ ምልልስ ዘግይተን እናቀርባለን።


No comments:

Post a Comment