Tuesday, May 12, 2015

ወጣት ስንታየሁ ቸኮል ተፈረደበት



በህወሃት/ኢህአዴግ ትእዛዝ እና በምርጫ ቦርድ አስፈፃሚነት የፈረሰው አንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን የወጣቶች ጉዳይ ሀላፊ እንዲሁም አንድነት ለህገወጦች ከተሰጠ በኋላ አሁን የወያኔ እግር እሳት ወደሆነው ሰማያዊ ፓርቲ የተቀላቀለው ወጣት ስንታየሁ ቸኮል መንግስት በISIS በግፍ የተጨፉትን ወገኖች ለማሰብ እና አረመኔውን ቡድን ለማውገዝ በተጠራው ሰልፍ ላይ በመገኘቱ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ካዋለው በኋላ በዛሬው እለት ፍርድ ቤት ቀርቦ የሀሰት ምስክሮች ተሰምተው በ6 ወር እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል። ስንታየሁ ቸኮል የገዢው ፓርቲ በትር ሲያርፍበት ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በዚህም ምክንያት ባለቤቱ እና ሁለት ልጆቹ ችግር ላይ እንደወደቁ ለማወቅ ተችሏል።

No comments:

Post a Comment