Monday, May 25, 2015

እርምጃችሁ ትክክል መንገዳችሁ የድል መዳረሻ ነው

ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ዘመኑን የዋጀ የፖለቲካ መሪ

መጪው ጊዜ ከወያኔ ጋር ድቅድቅ ጨለማ መሆኑን በመገንዘብ በ1997 ዓ.ም ከምርጫ ማግስት ይህን አንባገነን መንግስት ሁሉን አቀፍ በሆነ  የሀይል ትግል ካልሆነ በሰላማዊ መንገድ ስልጣኑን በህዝብ ለተመረጠ የህዝብ ተወካይ እንደማያስረክቡ ከበቂ ትንታቴ ጋር አቅርቦ ስርዓቱ  ይወገድ ዘንድ ከሌሎች የለውጥ ሀይሎች ጋር ሌት  ከቀን የተቻለውን ብቻ ሳይሆን አይቻልም አይሞከርም የተባለውን ሁሉ እየሞከሩ በርካታ ለውጦችን በሚመሩት ንቅናቄ ዙራያ አስመዝግበዋል፡፡እያስመዘገቡም ይገኛሉ፡፡


ወያኔ ለይስሙላ በየ5 ዓመቱ የሚያካሂደውን የይስሙላ ምርጫም አስመልክቶ ለኢትዮጵያ ህዝቦች ባሰተላለፈው መልክቱ እኔን ጨምሮ ብዙወቻችን ግራ ተጋብተን ነበር፡፡ደ/ር ብርሀኑ የምርጫ ካርዱን ቀዳችሁ ጣሉ ሲሉን ምን ነካቸው ዶ/ር ብለን ጋራ ተጋብተን ነበር፡፡ዛሬ ላይ ቆሜ ትናንት የተደረገውን አሳፋሪ እና ቅስም ሰባሪ ነገር ስሰማ  እና  በቪዲዮ የተቀረጹ ምስሎችን ስመለከት ግን ምን ያክል ትክክል እንደነበሩ እረዳለሁ፡፡ያኔ መልክታቸውን ሲያስተላልፉ ለምን ከወያኔ ውጪ ላሉ ለመድረክ ወይም ለሰማያዊ ፓርቲ ድምጽ ስጡ ብለው አላሉም በየ ነበር፡፡ነገር ግን አሳቸው ወያኔዎች  የሰሩትን ሳይሆን ሊሰሩ ያሰቡትን ነገር ቀድመው መተንበይ የቻሉ ነብያ ሊባሉ የሚችሉ ሰው ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ህዝቦች ምናልባት በእምነት ተኮትኩተን ያደግን እና የፈጣሪን ታምር ሰሪነት  ባለመጠራጠር  በዚህ ምርጫ በሆነ ታምር ወያኔ ስልጣኑን ሊያስረክብ ይችላል ብላችሁ ተስፋ አድርጋችሁ ከነበረ በፈጣሪ ያላችሁ እምነት እንደተጠበቀ ሁኖ የእናንተም ድርሻ አላቸሁ እና ይህ አይን ያወጣ ወሮበላ ስርዓት ሊለወጥ የሚችለው በጠቀናጀ ሁሉን ዘቀፍ ትግል ብቻ  መሆኑን ዛሬም በድጋሜ  እንድታረጋግጡ እድል ያገኛችሁበት በመሆኑ ትግላችሁ እስከ ነጻነት አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ማሳሰብ አያስፈልግም፡፡ አያት ቅማንቶቻችሁ ምን ሰርተው በነጻነት እንደኖሩ ታውቃላችሁ፡፡

በሰላማዊ መንገድ ለውጥ እናመጣለን ብላችሁ እስራቱን ግርፋቱን ክትትሉን ተቋቁማችሁ በተዘጋው በር ውስጥ ድምጻችሁን ለህዝቡ አሰምታችሁ በርካታ አንገታቸውን ለሰይፍ ሊሰጡ የሚችሉ የቆረጡ ወጣቶችን ማፍራት በመቻላችሁ ኩራት ይሰማችኋል፡፡በግሌም ያለኝ አድናቆት ከፍ ያለ ነው፡፡በተለይ የሰማያዊ ፓርቲ እና የመድረክ አመራሮች በተሰጣችሁ 6 ደቂቃ የአየር ሰዓት ይህን የበሰበሰ ስርዓት ራቁቱን አቁማችሁ ለህዝብ መሳቂያ ለደጋፊዎቹ መሳቀቂያ በማድረጋችሁ ኩራት ይሰማችሁዋል፡፡ወያኔ ጊዜ ለመጋዛት እና የህዝቡን ቁጣ በመፍራት በተወሰኑ አካባቢዎች የምርጫውን አዘግይቶ ቁጣውን ለማብረድ ይሞክር ይሆናል ነገር ግን አስቀድመን ከህዝቡ እንደተረዳነው ከ1997 ምርጫ በበለጠ ህዝቡ ለስርዓቱ ያለውን ጥላቻ በቅድመ-ምርጫው ወቅት አሳይቱዋል፡፡በትክክል የሚቆጥረው ከተገኘም የህዝቡ ድምጽ ለተቃዋሚ እንደሚሰጥ ጥርጥር የለውም ፡፡ሰጥቷልም፡፡አሁን መሆን ያለበት እንዴት ነው የተሰጠውን ድምጽ ማስከበር የሚቻለው የሚለው ነው፡፡ለዚህም ከህዝባችሁ ጋር በመሆን በህዝብ ማስከበር ግዴታችሁ ነው፡፡ከዚያ ውጪ ወያኔ ፈቅዶ የሚሰጠው አንድም ወንበር አትገኝም፡፡እርግጥ የወንበር ጥም እንደሌለባቸሁ ባውቅም በጣምራ መንግስት እስከመመስረት የሚያስችላችሁን ድምጽ እንዳገኛችሁ በበኩሌ ጥርጥር የለኝም፡፡

“ሞት ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም” እንደሚባለው በሀይል ትግል የምታምኑ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሮም በአንድ ቀን እንዳልተገነባች ሁሉ ወያኔን ባንዴ የሚጣልበት መንገድን ከመፈለግ በተገኘው አጋጥሚ ሁሉ ከስርዓቱ ጋር የሚደገር ትግል ተፋፍሞ መቀጠል አለበት፡፡የህዝቡ ቁጣ እና ምሬት ክፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት ልቡ በሸፈተበት ሰእት አለንልህ ብለን መከታነታችንን ካላሳየነው በኋላ ከህዝቡ ልብ እንዳንወጣ መጠንቀቅ እና ወቅታዊ ምልሽ መስጠት ያስፈልጋል፡፡በተለይ ከመግለጫ እና ተቀላቀሉን ከሚል ጥሪ በዘለለ በትንሹም ቢሆን የወያኔን ቅስም ሰብሮ የተጎዳውን ወገናችንን ሞራል የሚጠግን ተግባር ማሳየት ይጠበቅባችኋል፡፡በሰራዊቱ ውስጥም ያለውን ድጋፍ እና መሳሪያውን በስርዓቱ ላይ ማዞር የሚችለው ጸጥ ባለው አየር ሳይሆን የጥይት ድምጽ ሲሰማ  ነው፡፡እግራችን መንቀሳቀስ ሲጀምር ነው ብዮ አምናለሁ፡፡ማናልባት የጦር ባለሞያ ባለመሆኔ ግምቴ  ስህተት ሊሆን ይችላል፡፡ግን የሀገሩን ጉዳይ እንደሚከታተል እና በየጊዜው ከህዝብ የሚሰጠውን አስተያየት እንደሚከታተል እንድ ዜጋ ስመለከተው እርምጃ የመውሰጃው ጊዜ በጣም ዘግይቷል፡፡

ሌለው ደግሞ እንዳንዴ የምሰማቸው መረጃዎች ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው ያመዘኑ እነ እገሌ ተብለው ስማቸው ተጠርቶ የትጥቅ ትግሉን ተቀላቀሉ እየተባለ ባደባባይ የሚነገረው ምናልባትም ያሰብነው በህዝቡ ዘንድ የሚፈጥረው መነሳሳት ሊሆን ይችላል ፡፡በተቃራኒው ግን ለይስሙላ በተሰየመ ፓርላማ ጸረ-ሽብር ህግ  የሚል ዜጋውን በጅምላ የሚያስር ወረበላ መንግስት ባለበት ሀገር ከግለሰቡጋር  ግንኙነት የነበራቸው ቤተሰቡ ጓደኞቹ የስራባለደረቦቹ ሁሉ ጥርጣሬ ውስጥ ወድቀው ክትትል እና ስቃይ እንዲቀበሉ የሚያደርግ ለትግሉም ወደመሬት ድርጂታዊ መሰረቱን እንዳይዘረጋ የሚያደርግ ትግባር በመሆኑ ሊታብበት የሚገባው ተግባር ነው፡፡

በመጨረሻ በዶ/ር ብርሀኑ የሚመራው ንቅናቄም ሆነ ሌሎች በትጥቅ ትግል ለውጥ ለማምጣት መሳሪያ ያነሱ ሀይሎች የወሰዳችሁት እርምጃ ተገቢ መሆኑን መንገዳችሁም ወደ ድል መድረሻ ትክክልኛው መንገድ መሆኑን በመረዳት በወያኔ ተስፋው ለጨለመበት ህዝባችሁ ባስቸኩዋይ ካለደረሳችሁለት ብዙዎች የነጻነት ብርሀን ሳያዩ በሰው ሰራሽም በተፈጥሮ ሞትም ይህን ዓለም ጥለው እየተሰናበቱ ነው፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ህዝቦች!


No comments:

Post a Comment