Friday, May 1, 2015

በሊቢያ ለደረሰብን ውርደት ምላሽ መንግስት የበቀል አርምጃ መውስድ አለበት በማለታቸው የጦር አዛዦች እየታሰሩ ነው

(የምዕራብ እዝ 7ኛ ሜካናይዝድ የሬጅመንት ምክትል አዛዥ ሻለቃ ሙሉአለም ባህርዳር ታስሯል)
ሊቢያ ውስጥ አይ ኤስ በተባለው አሸባሪ ቡድን በዜጎች ላይ የተፈፀመውን ግፍ የተሞላበት ግድያ መንግስት ፈጣን ግብረ መልስ መስጠት አለበት በማለት የጠየቁ የሰራዊት አዛዦች እየታሰሩ መሆናቸውን ምንጮች ገለፁ፣የደረሰን መረጃ እንደሚያመልክተው- የምዕራብ እዝ 7ኛ ሜካናይዝድ የሬጅመንት ምክትል አዛዥ ሻለቃ ሙሉአለም የተባለ መኮነን የኢህአዴግ ገዥው መንግስት በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ እንዲሁም በየመን በኢትዮጵያውያን ዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ላለው አስቃቂ ግፍ መንግስት ፈጣን ግብረ መልስ መስጠት አለበት ብሎ ስለጠየቀ ብቻ ፀረ ሰላም ነህ ተብሎ ባህር ዳር መኮድ በተባለ ቦታ እንደታሰረ ምንጮቻችን አስታወቁ፣
ስርዓቱ በአይ ኤስ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ፍላጎት ስለሌለው የዜጎቻችንን ደም መመለስ አለብን የሚል ጥያቄ ለሚያነሱ ሰዎች እንደ ጠላት እያዬ ወደ እስር ቤት እያስገባቸው እንደሚገኝ የገለፀው ይህ መረጃ የመከላከያ ሰራዊትም በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ላለው የሚያሳዝን ተግባር ዋነኛ ተጠያቂው በስልጣን ላይ ያለው የኢህአዴግ ስርዓት መሆኑን በተደጋጋሚ እየገለፁ እንደሚገኙ ምንጮቻችን ያደረሱን መረጃ ገልጿል፣


No comments:

Post a Comment