Monday, May 26, 2014

በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በተከሰተ የእሳት አደጋ አንድ የተማሪዎች ማደሪያ ህንጻ ከጥቅም ውጭ ሆነ

 May26/2014

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 18 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) ትላንት ሌሊት በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በተከሰተ የእሳት አደጋ አንድ የተማሪዎች ማደሪያ ህንጻ ከጥቅም ውጭ ሆነ ።
በአደጋው በተወሰኑ ተማሪዎች ላይም መጠነኛ የአካል ጉዳት ደረሷል ።
የዩኒቨርሰቲው  ፕሬዝዳንት ዶክተር አድማሱ ሽብሩ ለፋና ብሮድካስቲን ኮርፖሬት እንደተናገሩት ፤ አደጋው ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ የተነሳ ሲሆን ፤ መንስኤው ግን እስካሁን ድረስ አልታወቀም ።
እሳቱን በአካባቢው ህብረተሰብና በአዲስ አበባ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያና መቆጣጠሪ ኤጀንሲ ሰራተኞች ትብብር በቁጥጥር ስር ማዋል ተችላል ያሉት ዶክተር አድማሱ ፤ አደጋው በሰው ህይወት ላይ ምንም ዓይነት ጎዳት አለማድረሱን ተናግረዋል።
በቃጠሎው ወቅት ከህንጻው ለመውጣት በሚያደረጉት ግፊያ ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቁ ተማሪዎች ከግድግዳ ጋር በመጋጨትና በመውደቅ ቆስለዋል።
ተማሪዎቹም በአካባቢው በሚገኝው አጣጥ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል።

No comments:

Post a Comment