Saturday, May 24, 2014

እግዚአብሄር የኢትዮጵያውያንን ጸሎት ለምን አልሰማም አለ? (ኪሩቤል በቀለ)

እንደምታውቁት እምነት አልባ የሆነውና በዲያብሎስ ሓይል ተደግፎ ኢትዮጵያን እያፈራረሰ ያለው ሕወሃት በዚህ እኩይ ተግባሩ 23ተኛ ዓመቱን እያገባደደ ነው:: ሕወሃትን በመሰለ አረመኔ መዳፍ ሥር የኢትዮጵያ ሕዝብ ተረግጦ መከራውን ሲገፋ አምላክ ለምን ዝም አለ?

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንና ምእመናን ከሃያ ዓመት በላይ  አምላካችን ኢትዮጵያን እንዲታደጋት በጸሎት ተማጽነናል:: ግን እግዚሃብሔር አልሰማንም:: ለምን?

ለቡዙዎች ግራ የሚያጋባ ጥያቄ ነው:: አንዳንዶቹ እግዚአብሄር ስለመኖሩም ሳይጠራጠሩ አይቀሩም:: ጥቂቶች ደግሞ እግዚአብሄር ፊቱን አዙሮብናል ይላሉ:: ምክንያቱን ግን ማወቅ ተስኖአቸዋል:: እግዚአብሔር ለምን ጸሎታችንን አይሰማም የሚለው ጥያቄ በኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ዘንድ የጊዜአችን አንገብጋቢ ርዕስ ነው::


መልሱ ከባድ ይመስላል:: ግን የእግዚአብሄርን ቃል ላነበበና የህይወቱ መመሪያ ላደረገ ክርስቲያን መልሱ ቀላል ነው:: በኢሳይያስ 58: 1-9 የተጻፈውን የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብ በቂ ነው:: አምላክ በግልጽ ያስቀመጠው ነገር ነው::

 ድምፅ :: እንደመለከት ድምጻችሁን አርጋችሁ እንደአመጹብኝ :: ለያዕቆብም ዝርያዎች ስለሃጢአታቸው :: እኔን የእኔን የአምላካቸውን መንገድ  የሚሹ ሀቀኛውን መንገድ  ትዕዛዝ ያከበሩ ለማስመሰል ሽር ፍትህን ከእኔ :: ወደ እኔም ለመቅረብ የሚፈልጉ ጾመናል ግን ጾማችንን አላየህም ራሳችንንም ዝቅ አርገናል ግን አምላክ  የፈለጋችሁትን እርስ በርሳችሁም :: :: እንደዚህ ጸሎታችን ይሰማል ብላችሁ እንደዚህ ዓይነቱን አንገታችሁን ደፍታችሁ እየዋሻችሁና ያሻችሁን እያረጋችሁ ነው ? እንዲህ ዓይነት ጾም ነው በጌታ ፊት ተቀባይነት  የምመርጠው ጾም የክፋትን ሰንሰለት የሚበጥስና የጭቆናን ቀንበር ? እኔ የምመርጠው ጾም የተራበውን የሚያበላ ማደሪያ የሌለውን ቤት የተራቆተውንም የሚያለብስ  እነዚህን ብትፈጽሙ ግን  አሳያችኋለሁምህረቴም በቶሎ ይደርስ እኔ የምመርጠውን ጾም ብታደርጉ ሃቅንና ፍትህን የናንተ ደጀን ሆኖ ከኋላ ከእዚህ በኋላ እግዚአብሄርን እርዳን ብላችሁ ብትማጸኑት አለሁ :: ጸሎታችሁንም ::“እግዚአብሄር ጸሎታችንን ለምን እንድማይሰማ ከዚህ በላይ የተጠቀሰው በቂ መልስ ነው::

ይህ አሳዛኝ ሁኔታ በእስራኤላውያን ላይም ተከስቷል:: ናቡከደነጾር የሚባለው የባቢሎን ንጉሥ እስራኤልን ወርሮ አሰቃቂ ጭፍጨፋ ማካሄዱ ሳያንሰው በእሱ ስም እንዲያመልኩ አስገድዷቸው ነበር:: ለጊዜውም ቢሆን አምላክ ዝም ብሎ ተመልክቶ ነበር::በኋላ ግን እግዚአብሄር ናቡከደነጾርን ሕሊናውን እንዲስት አርጎ እንደ አውሬ በዱር ወድቆ ሳር እንዲበላ አደረገው:: አምላክ የእስራኤላውያንን ምልጃና ጸሎት ተቀብሎ እንባቸውን አበሰ:: ይህም የሆነው እስራኤላውያን ወደ ልባቸው ተመልሰው አምላካቸውን በቅንነት ማምለክ ሲጀምሩ ነው::

ልባችን ንጹህ እስከአልሆነ ድረስና ወደ ቤተክርስቲያን እየተመላለስን ብቻ ወይም እንደአብዛኞቹ ቀሳውስትና መነኮሳት አምላክን እናገልግላለን እያልን በማስመሰል በእግዚአብሄር ቃል የምንነግድ ከሆነ እግዚሃብሄር በፍጹም ጸሎታችንን አይሰማም:: በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናት፤ በኢትዮጵያም ሆነ በዲያስፖራ ምን እንደሚካሄድ ተመልከቱ :: አንዱ አንዱን ሲያማ፤ይባስ ብሎ ዓለም ፍርድ ቤት ሲከስ፤ ሲያወግዝ ፤በቤተክርስቲያን ገንዘብ አዲስ አበባ ውስጥ ቤት ሲሰራ፤ዲያቆን ሲደበድብ፤ ከቤተ ክህነት ዲያቆንና ቄስ ሲያባርር  ነው የምንመለከተው::

በፍትወተ ሥጋና ከልክ ባለፈ ፍቅረ ንዋይ ተቃጥለን አምላክን ወደ ጎን ትተነዋል:: እግዚአብሄርን መፍራት ረስተናል:: ግብረ ሰዶም በጠራራ ፀሃይ እንደ ሰደድ እሳት በኢትዮጵያ ውስጥ ሲስፋፋ ዝም ብለን እንመለከታለን:: ቤተሰባችን፤ ቤተክርስቲያናችንና አገራችን በማያቋርጥ ሁኔታ ላለፉት 40 ዓመታት እየታመሱ  ነው::በረብሻና በእርስ በርስ ጦርነት ያልተጠመደ ቤተሰብ ወይም ቤተክርስቲያን ወይም የኢትዮጵያ ክፍለ ሃገር ከቶ አይገኝም::ለገንዘብና ለሥልጣን የሚደረገው አሳፋሪ ግብግብ ሳያንስ፤ በቤተክርስቲያናችን ውስጥ የሰው ሚስት ሲዳፈሩ የተያዙ መነኮሳት ቁጥር እየጨመረ መጥቷል::

በቅርቡ በኦክላንድ ካሊፎርኒያ ውስጥ የተከሰተው አጸያፊና ዘግናኝ ድርጊት በቂ ማስረጃ ነው:: አንድ መነኩሴ የሰው ሚስት ሲያባልግ እጅ ከፍንጅ ተይዞ ተባረረ:: የሚገርመው ከዚህ ተግባሩ በፊት በዚሁ መነኩሴ መሪነት ቤተክርስቲያኑንን በጥብጦ ለሁለት ክፍሎ ነው የራሱን ቤተክርስቲያን የክፈተው:: በጣም አሳዛኝ የሆነው ነገር ደግሞ ከተባረረ በኋላ የተፈጸመው ነገር ነው:: መነኩሴው ሥራ ፈት ሁኖ ግን ለጥቂት ጊዜ ታክሲ ሲነዳ ከከረመ በኋላ ኢትዮጵያ ይገባል:: ለትንሽ ጊዜ ድምጹ ከጠፋ በኋላ ድንገት አሜሪካ ከተፍ ይላል:: ምነው ሲባል ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሲኖዶስ ሹመት ሰጥቶ ነው የሕወሃት ደጋፊ ቤተክርስቲያኖችን እንዲያገለግል ወደ አሜሪካ እንደገና የላከው ተባለና ቁጭ:: እንዲህ ዓይነት የድፍረት ሃጢያት ውስጥ ነው ቤተክርስቲያንም ምዕመናንም የምንመላለሰው! እንዴት ብሎ ነው አምላክ ጸሎታችንን የሚሰማው:: አይሰማም:: ብንጾምም ጾማችን የረሃብ ዓድማ፤ ስግደታችንም ጅምናስቲክ  ሆኖ ነው የሚቀየረው::

እግዚአብሄር መስዋዕትነትን ከማቅረብ ይልቅ ከልባችን አምነነው ትእዛዙን ብናከብር ነው ጸሎታችንን የሚሰማው:: የዕለት ተለት ሕይወታችን በክፋት: በውሸት: በጸብ: በማጭበርበር: በሃሜት: በክስ: በተንኮል: በእብሪትና በሌሎችም ሓጢያቶች እስከተሞላ ድረስ አምላክ ጸሎታችንን አይሰማም:: እሁድ እሁድ ቤተክርስቲያን ብንመመላለስ መስዋታችንን ብናቀርብና እንዲሁም አሥራታችንን ብንሰጥ ግን ከሰኞ እስክ ቅዳሜ ቃሉን ሳናከብር በዓመፅ ብንኖር አምላክ ጸሎታችንን በፍጹም አይሰማም::ስለዚህ በመጀመሪያ ማስመሰሉን አቁመን ልባችንን ወደ አምላክ መልሰን በቃሉ መኖር መጀመር አለብን:: ከዚያ በኋላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ንስሓ ለመግባት አለም አቀፍ ኑዛዜ (International Confession)ማካሄድ ይኖርባታል:: ይህ ሲሆን ብቻ ነው እግዚሃብሄር ጸሎታችንን ሰምቶ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን የሚታደገው:: ኢትዮጵያና ሕዝቦቿ ወደ ቀደመ ክብራቸው የሚመለሱት ይህንን ስናደርግ ብቻ ነው::

አምላክ ለኑዛዜና ለንስሃ ያብቃን!

ከመከራና ከስደት አውጥቶ ፍጹም ሰላማችንንና አገራችንን እንዲመልስልን አምላካችንን በንጹህ ልብና በቃሉ በመኖር እንማጸነው::ያኔ አምላክ ጸሎታችንን ይሰማል::


No comments:

Post a Comment