Thursday, May 22, 2014

(አባይ ሚዲያ)፡ የኢትዮጵያ መንግስት በጎረቤት ኤርትራ በኩል እየጠነከረ የመጣውን የነጻነት ሃይሎች እንቅስቃሴ ለመግታት ሲል ኤርትራውያን ስደተኞችን መስታጠቅ ሊጀምር ነው።



የኢትዮጵያ መንግስት በጎረቤት ኤርትራ በኩል እየጠነከረ የመጣውን የኢትዮጵያውያን የነጻነት ሃይሎች እንቅስቃሴ ለመግታት ያስችለው ዘንድ በኢትዮጵያ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞችን በማሰባሰብ የአስመራን መንግስት በሃይል በመገልበጥ ዴሞክራሲ በኤርትራ መፈንጠቅ አለበት የሚል አዲስ ዘዴ መጀመሩን ከአካባቢው ለመረዳት ችለናል።

አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ወጣት ኤርትራዊ ሲገልጽ፡- አካባቢው የእርስ በርስ የጦርነት ቀጠና መሆኑ ለወያኔ የትኩረት አቅጣጫን በኤርትራኖች የእርስ በርስ ጦርነት በመለወጥ በአካባቢው እየጠነከረ የመጣበትን ሃይል ወደ ህዝቡ እንዳይዳረስ ለማድረግ ለራሱ ጥቅም የጀመረው ሴራ እንጂ ለእኛ የኤርትራውያን ተቃዋሚዎች አስቦ በኤርትራ ዴሞክራሲ ይፈጠር በሚል ትላንት በድንገት ወደ ትግሉ ግቡ ሊለን አይችልም ሲል መረጃውን ሰጥቶናል።

በትላንታናው እለት የኤርትራውያን ስደተኞች 23ኛ የነጻነት አመታቸውን በሚያከብሩበት የስደተኞች መጠለያ የወያኔ ባለስልጣኖች ተገኝተው ስደተኞችን ወደ ተቃዋሚው ጎራ ገብተው እንዲታገሉና የኢሳያስን መንግስት እንዲገለብጡ በጥብቅ ያሳሰቡ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ይህን ተከትሎም ለተለያዩ የመገናኛ ብዙሃኖች “ በኢትዮጵያ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ትጥቅ አንስተው ለመታገል ተቃዋሚ ሃይሎችን ሊቀላቀሉ ነው” የሚል ዜና መላኩን ሱዳን ትሪቢውት የተባለው ድህረ ገጽ አስፍሮታል።

በአለፈው ሳምንት የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል 4ኛ ዙር በርካታ የነጻነት ታጋይ ወታደሮችን ማስመረቁን መዘገባችን ይታወሳል።


No comments:

Post a Comment