Wednesday, May 2, 2018

የወልዋሎ ቡድን ተጫዋቾች ከፈጸሙባቸው ድብደባ ይልቅ የሰደቧቸው ዘር ላይ ያነጣጠረ ስድብ ይበልጥ እንዳመማቸው ኢንተርናሽናል አልቢትር ኢያሱ ፈንቴ ተናገሩ።

 (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 24 ቀን 2010 ዓ/ም) የዳኞችና ታዛቢዎች ማህበር ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ዳኛ ኢያሱ ፈንቴ ባደረጉት ንግግር ተጫዋቾቹ ሲደበድቧቸው ከአፋቸው ይወጣ የነበረውን ዘር ላይ ያነጣጠር ስድብ ለመግለጽ እንደማይፈልጉ በመጥቀስ “በምን ቋንቋ መናገር እንደምችል አልገባኝም። በእግርኳስ ቋንቋ ላውራ ብል ፖለቲካ ይባልብኛል” ብለዋል። “እኔ በወቅቱ ብቸኝነት ነው የተሰማኝ፤ ሁኔታው ሲፈጠር ሁሉም ቆሞ ከመመልከት ውጪ ሊገላግል የመጣ አንድም ሰው የለም።” ያሉት ዳኛ ኢያሱ ፋንታ፣ እገዛ ለማድረግ ሲጥር የነበረው አቶ ፍጹም ገብረማርያም ብቻ ነው”ሲሉ ተናግረዋል። “ኢትዮጵያዊ የሆነ ሰው እንዴት ስደበደብ ቆሞ ይመለከታል?”ያሉት አርቢትሩ፣ ሰው የሰው መደብደብ የማይሰማው ከሆነ በጣም የሚያሳዝን ጊዜ ላይ ደርሰናል ማለት ነው ብለዋል። ” በብሔሬ ምክንያት ጨዋታውን ማጫወት የለበትም ከተባለ መነሳት ነበረብኝ” ያሉት አርቢትር ኢያሱ፣ ከጨዋታው አስቀድሞ ምንም ነገር ሳይነሳ ሜዳ ውስጥ ሢሰሙ የነበሩት ነገሮች በሙሉ ግን ዘግናኝ ነበሩ” ሲሉ ገልጸዋል። አክለውም፦”ጨዋተው በሰላም እንዲያልቅ በሚል ብዙ ነገር ተቋቁሜ ነበር እስከ ድብደባው ድረስ የዘለቅኩት” ሲሉ በዙ ስድብና ዘለፋ እንደደረሰባቸውም ጠቁመዋል። አርቢትር ኢያሱ በመጨረሻም “ከዚህ በኋላ በዳኝነት እቀጥላለሁ›ወይስ አልቀጥልም? የሚለውን ፈጣሪ ነው የሚያውቀው ” ማለታቸውን የሶከር ኢትዮጵያ ዘገባ ያመለክታል። የወልዋሎ ቡድን ጠጫዋቾች እና የቡድን መሪ የዳኛን ውሳኔ በመቃወም አርቢትርን እስከመደብደብ የደረሱበት አሳፋሪ ድርጊት በቢቢሲ እና በሌሎች ዓለማቀፍ ሚዲያዎችም ሰፊ ሽፋን አግኝቷል።

No comments:

Post a Comment