Tuesday, February 6, 2018

ጣና ሃይቅ ላይ አዞላና ኢፓማ የተባሉ አረሞች በተጨማሪ ጉዳት እያደረሱ ነው ተባለ።

 እምቦጭ አረም ሃይቁ ላይ እያደረሰ ያለው አደጋም አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል። በባህርዳር ዩኒቨርስቲ የውሃ ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ተባባሪ ፕሮፌሰር አያሌው ወንዴ የጣና ሃይቅ ባለፉት አመታት የተለያዩ የህልውና ፈተናዎች ገጥመውታል ሲሉ ለቢቢሲ የአማርኛው ክፍል ተናግረዋል። ፈተናዎቹን የአፈር መከላት፣የደለል ክምችት፣ተገቢ ያልሆነ የስነ-ሕይወት አጠቃቀም፣ልቅ ግጦሽና የባህር ሸሽ እርሻ ናቸው ሲሉ ረዳት ፕሮፌሰሩ ይገልጿቸዋል። በጣና ዙሪያ የተወለዱትና በሃይቁ ላይ የተለያዩ ምርምሮችን እንዳደረጉ የሚገልጹት ተባባሪ ፕሮፌሰር አያሌው ወንዴ በተለይም ከጥቂት አመታት ወዲህ በሰሜናዊ ምስራቅ የሃይቁ ክፍል የተከሰተው የእምቦጭ አረም ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረ ይገኛል። ይሄ ስጋት ሳይቀረፍ ከእምቦጭ አረም በተጨማሪ አዞላና ኢፓማ የተሰኙ አረሞች በሃይቁ ላይ መከሰታቸውን ተመራማሪው ገልጸዋል። ችግሩን ለመቅረፍ በሰው ጉልበት የሚደረገው ስራ በማሽን ካልታገዘ በጣና ሃይቅ ላይ የተጋረጠው አስጊ ሁኔታ እንደማይወገድ ተመራማሪው አሳስበዋል። አረሙን ለማስወገድ በተደረገ ጥረት የሰው ህይወት መጥፋቱንና በእባብ ተነድፈው ጉዳት የደረሰባቸው እንዳሉም ነው የተናገሩት። ፕሮፌሰር አያሌው አረሙን ለማስወገድ በቅንጅት እየተሰራ አይደለም ሲሉም ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment