Friday, February 2, 2018

የአዳማ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በአጋዚ ወታደር ተደበደበች

በአዳማ ዩኒቨርስቲ አንዲት የ4ኛ አመት የስነ ሕይወት ሳይንስ ተማሪ የመኝታ ክፍሏ ተሰብሮ በአንድ የአጋዚ ወታደር መደብደቧንና ጾታዊ ትንኮሳ እንደደረሰባት ዘገባዎች አረጋገጡ።
በዩኒቨርስቲው የሚገኙ ሴት ተማሪዎች በመከላከያ ወታደሮች በሃይል ተገደው እንደሚሳሙም በተቋሙ ጉዳዩን ያጣሩት አካላት አረጋግጠዋል።
በአዳማ ዩኒቨርስቲ የጾታ ጉዳዮች ዳይሬክተር ሃና ተፈራ ጉዳዩን አጣርተው ለቦርድ በማቅረባቸው በአንድ የመከላከያ ጄኔራል ትዕዛዝ ከስራ ተባረዋል።
በአዳማ ዩኒቨርስቲ በአጋዚ ወታደር በመደብደብ ጾታዊ ትንኮሳ የደረሰባት የ4ኛ አመት ተማሪ አሳዛኝ ታሪክን ይፋ ያደረጉት ሃና ተፈራ የተባሉ በተቋሙ የጾታ ጉዳዮች ዳይሬክተር መሆናቸውን የአዲስ ስታንዳርድ ዘገባ ያመለክታል።

ስሟ እንዲጠቀስ ያልተፈለገው ይህችው የአዳማ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ጾታዊ ትንኮሳ የደረሰባት በግቢው ውስጥ ጸጥታ በማስከበር ስም ተቋሙን ለመቆጣጠር በገባ የአጋዚ መከላከያ አባል አማካኝነት ነው።
ተማሪዋ የመኝታ ክፍሏ ተሰብሮ ከተደበደበች በኋላ በአዳማ ሃይለማርያም ማሞ ሆስፒታል ታክማ ጉዳቱ ስለከፋባት ወደ አዳማ አጠቃላይ ሆስፒታል ለከፍተኛ ሕክምና መላኳም ነው የተነገረው።
ይህንኑ አሰቃቂ ጉዳት ያጣሩት የአዳማ ዩኒቨርስቲ የጾታ ጉዳዮች ዳይሬክተር የሆኑት ሃና ተፈራ ሌሎችን ሴት ተማሪዎች ሲጠይቁ በግቢው ውስጥ ባሉ የአጋዚ መከላከያ ወታደሮች ተገደው እንደሚሳሙ አረጋግጠዋል።
የሴቶችን ጾታዊ ትንኮሳ ለዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት በደብዳቤ ያሳወቁት ዳይሬክተሯን ሃና ተፈራን ጉዳዩ ለቦርድ ደርሶ እልባት ከማስገኘት ይልቅ ከስራ እንዲባረሩ አድርጓቸዋል።
በአዳማ ዩኒቨርስቲ ቦርድ ውስጥ የተወከሉ የመከላከያ ከፍተኛ መኮንን ጉዳዩን ከሰሙ በኋላ በተቋሙ ፕሬዝዳንት የተመረጠውና 5 አባላት ያሉት አጣሪ ኮሚቴ ስራው እንዲቋረጥ ማዘዛቸው ታውቋል።
የአጣሪ ኮሚቴው ሰብሳቢ ሃና ተፈራም ባላወቁት ምክንያት ከስራ ሲባረሩ ወጣቷን ለመድፈር የሞከረው የአጋዚ ወታደር ግን ተጠያቂ አልተደረገም።
በአዳማ ዩኒቨርስቲ በተመሳሳይ ሁኔታ ተደፍራ ትምህርት ያቋረጠች ሌላ ተማሪ መኖሯንም የአዲስ ስታንዳርድ ዘገባ ያመለክታል።
በዩኒቨርስቲዎች ግጭት ከተቀሰቀሰ ወዲህ የተማሪዎችን ተቃውሞ ለማስቆም በሚል በግቢው ውስጥ የተሰማሩ የአጋዚ መከላከያ ሰራዊት አባላት በርካታ ተማሪዎችን እየደፈሩ መሆናቸውን የተለያዩ መረጃዎች ያሳያሉ።
በአምቦ ዩኒቨርስቲ ከፕሬዝዳንቱ ለትምህርት ሚኒስቴር በተጻፈ ደብዳቤ ሴት ተማሪዎች በአጋዚያን ወታደሮች እየተደፈሩ መሆናቸውን ያመለክታል።
ይህንኑ ተከትሎም እስካሁን በአቃቤ ህግ በኩል የተወሰደ ሕጋዊ ርምጃ የለም።

No comments:

Post a Comment